# እንድታውቁትበነገው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት የሚወስዱ መንገዶች በስራ ምክንያት ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ፡፡ ነገ ነሃሴ 15…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/r-PxypVjG2qN46TghRej3mYPjaRJElSjU9leKHSHbQpBnIiGqPSfCfwhhTxxRhnhKjOStlXi_QvEzEOGr7ZCLw1wZf5_ohb1wzSGPQhopRmhiHPf-xFR1Dh_q_20Q7z7vZLohjH_oLGa-DKV513HS1y81EEXI9W7ezyqSUFe4TE4XGrusd26eI0AdIECgWJRE5LmXT-alYvKg26THLhJEwiZDGSqDSI8xsRDLd6_V1_47r88-aZX7_Giofm4cAhcyMq92qQWc7vBP_WXjeeBXldpKSxuRSxfM8OfpiCKzRPtYW8EhLzCNN8rILXKz6mYtCOT5DuamBo3IIhZAcqqbw.jpg

# እንድታውቁት

በነገው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት የሚወስዱ መንገዶች በስራ ምክንያት ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ፡፡

ነገ ነሃሴ 15 ቀን 2014 ዓ/ም ከተለያዩ አቅጣጫዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምባሳደር አካባቢ አዲስ ወዳስገነባው ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ የሚወስዱ መንገዶች በስራ ምክንያት ከለሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት
• ከሴንጆሴፍ መብራት ወደ ሃራምቤ ሆቴል
• ከኢሚግሬሽን ወደ ፍልውሃ
• ከፍል ውሃ ወደ ኢትዮጵያ ሆቴል
• ከጤና ሚኒስቴር ወደ ፍልውሃ
• ከለገሃር ወደ ፍልውሃ
የሚወስዱት መንገዶች ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ በመገንዘብ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚያመላክቷቸው አቅጣጫ መሰረት ሌሎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

ነሐሴ 14 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply