እንግሊዝ ሺሻ በሃገሯ እንዳይጨስ አገደች፡፡ እገዳውን የተላለፈ 2 ሺህ 500 ፓውንድ ቅጣት ይጠብቀዋል፤የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ በሃገራቸው በየትኛውም ቦታ ሺሻ እንዳይጨስ አግደ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/CEyq6VtDDfg6RFLdCrofcTR3DNoOBxFQ6Ug19G3GxYc2dCpE7dFe2dOs5PCEsS2G4qOLKKob-tBoLtqSQ9ho8HpBLYyXTAhmS3yIG9BkmJt3qXgFVft0e9JOAA_6oBrerFJH_pBDXY89BCaAYkCHAqdekZJ7kKwla5KPhgahROCjefbOPYDeiC1fDkIrtPB0rOEOsBoRoFA68i9HNCBnQfFQ0iadPrMzzY70rv2t_4cTwcFMX5Iy8Ep_uR9b3Q48nu-GWCX43JtuPNvwwV5xvt36lvCcGEYyjRLcStgS1kIi-d9hd-a62KCk_bFgb3s9VD70Xz99t504Qv-sILhNig.jpg

እንግሊዝ ሺሻ በሃገሯ እንዳይጨስ አገደች፡፡

እገዳውን የተላለፈ 2 ሺህ 500 ፓውንድ ቅጣት ይጠብቀዋል፤
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ በሃገራቸው በየትኛውም ቦታ ሺሻ እንዳይጨስ አግደዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሺሻ እንዳይጬስ ያገዱት በዜጎች ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ያወጣውን መረጃ መሰረት በማድረግ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ሺሻን ማገድ ያስፈለገን ከሚያደርሰው የጤና እክል እና ማሕበራዊ ቀውስ አንፃር ነው” ሲሉ ሪሺ ሱናክ ተናግረዋል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት በቅርቡ ሺሻ ማጨስ ጤናን እንደሚጎዳ የሚጠቁም ጥናት ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

በአሁኑ ወቅት እንግሊዝን ጨምሮ ፓኪስታን፣ ዮርዳኖስ፣ ሲንጋፖርና ሳዑዲ አረቢያ ሺሻን ያገዱ ሃገራት መሆናቸውን ኒውስ ናው አስነብቧል፡፡

ሺሻ በእንግሊዝ በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን፣ ከውሳኔው በኋላ እንግሊዛዊያን ወደ ኤክስ(የቀድሞው ትዊተር) በማምራት በእገዳው ዙሪያ እየተወያዩ ይገኛሉ።

በሃገሪቱ በብዛት የሚዘወተረው ኤልክትሮኒክ ሺሻ ሲሆን ምርቱ በየትኛውም የሸቀጣሸቀጥ መደብር ውስጥ በብዛት እየቀረበ ይገኛል ተብሏል፡፡

ይህ ኤልክትሮኒክስ ሺሻ በካንሰር በሽታ የመጠቃት እድል ይፈጥራል የተባለ ሲሆን፣ ባሁኑ ሰአት ሆስፒታል ከሚገቡ እንግሊዛዊያን መካከል አብዛኛዎቹ በዚህ ምክንያት የተጠቁ ናቸው ሲል የሃገሪቱ የጤና ተቋም አስታውቋል፡፡

በእንግሊዝ ይህንን ህግ ተላልፎ የሚገኝ ነጋዴም ሆነ ተጠቃሚ እስከ 2ሺህ 500 ፓውንድ የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ይጠብቀዋል ተብሏል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply