እንግሊዝ ከኢትዮጵያ ወደ አገሯ በሚገቡ የአበባ ምርቶች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ታሪፍ መጣል አቁማለች፡፡እንግሊዝ ዓለም ዓቀፉን በአበባ ንግድ ላይ የሚጣለዉን ታሪፍ ማንሳቷን አስታዉቃለች፡፡በምስራቅ…

እንግሊዝ ከኢትዮጵያ ወደ አገሯ በሚገቡ የአበባ ምርቶች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ታሪፍ መጣል አቁማለች፡፡

እንግሊዝ ዓለም ዓቀፉን በአበባ ንግድ ላይ የሚጣለዉን ታሪፍ ማንሳቷን አስታዉቃለች፡፡

በምስራቅ አፍሪካ ለሚገኙ የአበባ አምራቾች ዋጋዉን ለማርከስ እና ከእንግሊዝ ጋር የሚደረግ ግብይትም ቀላል እንዲሆን በማሰብ ለ2 ዓመታት ታሪፍ መጣል ማቆሟን ነዉ የገለጸችዉ፡፡

ከዚህ በኋላ ለሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ወደ እንግሊዝ በምትልካቸዉ የአበባ ምርቶች ላይ ምንም ዓይነት ታሪፍ አይጣልባትም፡፡

ይህ ዉሳኔ ከአበባ አምራቹ አገር ቀጥታ ወደ እንግሊዝ ሲላክ ብቻ ሳይሆን በሌላ ሶስተኛ አገር ጭምር አበባዉ ወደ እንግሊዝ ቢገባ ምንም ዓይነት ታሪፍ እንደማይኖረዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ይህም በምስራቅ አፍሪካ ለሚገኙ የአበባ ምርታቸዉን ቀጥታ ወደ እንግሊዝ ሳይሆን በሌላ ሶስተኛ አገር ወደ እንግሊዝ ለሚያስገቡ አገራት ከፍተኛ ጥቅም አለዉ ተብሏል፡፡

ይህ ዉሳኔ ከምስራቅ አፍሪካ አምራቾች ጋር ያላትን ግንኙነት በማጠናከር በክልሉ ያላትን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነዉ የተባለ ሲሆን፤ ከዛ ባሻገር ለተጠቃሚዎችም በዋጋም፣ በአበባ ልዩነትም ምርጫ እንዲኖራቸዉ ያደርጋል ተብሏል፡፡

የተነሳዉ የ8በመቶ ታሪፍ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚተገበር ቢሆንም ከፍተኛ አበባ አምራች ለሆኑት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛንያ እና ኡጋንዳ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ከፍተኛ አበባ አምራች አገር ስትሆን ከሰብ ሰሃራን አፍሪካ ከሚላኩ የአበባ ምርቶች 23 በመቶዉን ድርሻ የምትይዝ ናት፡፡

በ2023 ከኢትዮጵያ 12.6 ሚሊየን ዩሮ የሚገመት የአበባ ምርት ወደ እንግሊዝ እንደተላከ ይታወሳል፡፡

ይህ ዉሳኔ ለሁለት ዓመታት ቀጣይነት ያለዉ ሲሆን ከዛሬ ሚያዚያ 11 2024 ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 2026 ድረስ የሚተገበር ነዉ፡፡

እስከዳር ግርማ
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 03 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply