#እንጥል ማስቆረጥእንጥል ምግብናፈሳሽ ነገሮችን በምንውጥበት ጊዜ ምግብ እና ፍሳሹ በአፍንጣችን ጀርባ ወደ ሰርን እንዳይሄድ እና ቀጥታ ወደ ጉሮሯችን እንዲሄድ የሚረዳ አካል መሆኑን ባለሙያዎ…

#እንጥል ማስቆረጥ

እንጥል ምግብናፈሳሽ ነገሮችን በምንውጥበት ጊዜ ምግብ እና ፍሳሹ በአፍንጣችን ጀርባ ወደ ሰርን እንዳይሄድ እና ቀጥታ ወደ ጉሮሯችን እንዲሄድ የሚረዳ አካል መሆኑን ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡

ነገር ግን ይህን ትልቅ ተግባር ያለዉን አካል በማወቅም ሆነ ባለማውቅ ሶዎች ሲያስቆርጡት በብዛት ይስተዋላል፡፡

እንጥል ማስቆረጥ ምን ሊያስከትል ይችላል ብለን ከአንገት በላይ ቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ሀኪም ከሆኑት ዶ/ር ብስራት ጌታቸው ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡

#እንጥል ምንድነው?

ባለሙያው በመጀመሪያ እንጥል እና ቶንሲል ልዩነት እንዳላቸው መገንዘብ ይገባል ይላሉ፡፡

ቶንሲል የሚባለዉ በግራና በቀኝ ከምላሳችን ጀርባ የራሳቸው ዋሻ መሳይ ነገር ያላቸው እና ውስጥ ቁጭ የሚሉ የሰውነት የመከላከል አቅም በተወሰነ መልኩ ይረዳሉ ተብለው የሚገመቱ አካል መሆናቸውን ይናገራሉ ፡፡

እንጥል የምንለው ደግሞ የላናንቃችን ቅጥያ የሆነና በውስጡ ጡንቻ እና ሽፋን የያዘ አካል መሆኑን ዶ/ር ብስራት ይናገራሉ፡፡

#እንጥል መቆረጥ ምንድነው ?

በዘመናዊ ህክምና እንጥል መቆረጥ የሚባል ነገር አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን እንጥልን ለማስቆረጥ በጣም ውስን የሚባሉ ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ

ለምሳሌ ፡- በጣምእረጅም እንጥ ያላቸው እና ወደ ምላሳቸው ጀርባ እያረፈ ልክ ባዕድ ነገር እንደተቀመጠ አይነት የሚሰማቸው ሰዎች ካሉ እንጥላቸው በጣም በረጅሙ ከወረደ ከውጪ ያለችውን ሽፋን የሚቆርጥበት ሁኔታ እንዳለ እና ይህም ከስንት አንዴ ሚደርግ መሆኑን አንስተዋል፡፡

አብዛኛው ሰው እንጥል ከተቆረጠ የቶንሲል ህመም እንዳይመጣ ማድረግ ይቻላል ብለው ያስባሉ ነገር ግን እንጥላቸውን የተቆረጡም ያልተቆረጡሙ ሰዎች የቶንሲል በሽታ ይገጥማቸዋል ስለዚህ መፍትሄ ተብሎ ይንደማታሰብ ተናግረዋል፡፡

#እንጥል መቆረጥ ለምን አይነት ችግሮች ሊዳርገን ይችላል?

-ለከፍተኛ ትንታ
-ለድምፅ መቀየር
-ለመዋጥ ችግር

-ማታ በሚተኙበት ግዜ ምግብ ወደ ጆሮ በመሄድ ለጆሮ ኢንፌክሽን እስከዳረግ፡፡
-ለአለርጂ እንዲሁም ለሳይነስ ሊዳርገን እደሚችል አንስተዋል፡፡

ከዚህ መረዳት እንደምንችለውም እንጥል መቆረት እንደሌለበት ሲሆን እንጥል መኖሩ በጣም ከፍተኛ ጥቅም አለው ፡፡

በተፈጥሮ እንጥል የተፈጠረው ዝም ብሎ አይደለም ስለዚህ እንጥል ሳይሆን መነካት ያለበት ቶንሲል የሚባለው በዘመናዊ ህክምና ከተደጋገመና ካስቸገረ ህክምና ቦታ ላይ በመሄድ ተገቢውን ህክምና ከባለሙያዎች ማግኘት እንደሚገባ ዶ/ር ብስራት ተናግረዋል ፡፡

ማህበረሰቡም ይህ ድርጊት ጎጂ ልማድ መሆኑን ተገንዝቦ ከእንደዚህ አይነት ድርጊት መቆጠብ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply