
“እኛም አውቀናል፤ ጉድጓድ ምሰናል!!” ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃባው እና ኮሎኔል ሞገስ ዘገዬ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)… ሀምሌ 6/2015 ዓ/ም_ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ኮሎኔል ፈንታ ሙሃቤ እና ኮሎኔል ሞገስ ዘገየ መከላከያ ከፋኖ ጋር የሚዋጋበት ምንም አጀንዳ የለውም ሲል ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሀምሌ 5/2015 ላደረገው ንግግር “እኛም አውቀናል፤ ጉድጓድ ምሰናል!!” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የተጀመረው መራር ትግል መዳረሻው ግቡን ሳይመታ የሚቆም አይሆንም ብለዋል። ትግላችን እንደዚህ ቀደም ትግሎች መርህ አልባና መዳረሻውን የማያውቅ ስላልሆነ በጠላት ተራ አጀንዳ የሚጠለፍ አይሆንም ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ኮሎኔሎቹ “እኛ ሁሉንም እርምጃችንን አስበን በስክነትና በጥበብ እየተራመድን ነው ጠላት ሲፈልግ የሚሸብበን ሲፈልግ ጠላት የሚያደርገን ጅሎችም አይደለንም።” ብለዋል። “እኛ ወታደሮች ነን በጠላት የማዘናጊያ አጀንዳ ልባችን የትም የማይክለፈለፍ።” ያሉት ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃባው እና ሞገስ ዘገዬ “ህዝባችንም ይህንን አውቆ ጊዜውን በተራ አሉባልታ ባያባክን መልካም ነው።” ሲሉ መክረዋል። ምክንያቱም እኛ ገና ብዙ ቀድመን ያልሰራናቸው የቤት ስራዎች አሉብንና እነሱ ላይ ትኩረት ብንሰጥና ተጋግዘን መጨረስ ብንችል መልካም ነው ያሉ ሲሆን እነሱ የገመቱት አልቀረም ሀምሌ 6/2015 ከንጋት ጀምሮ ሙሉቀን በራያ ቆቦ እና አካባቢው የአገዛዙ ጦር ተኩስ ከፍቶ በሲሎች ላይ ጭምር ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።
Source: Link to the Post