“እኛ የህዝብ ልጆች ነን፤ የህዝብ አደራ ጠባቂዎች ነን፤ ሌላ አላማ የለንም።” ሻለቃ መሳፍንት ተስፉ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ…

“እኛ የህዝብ ልጆች ነን፤ የህዝብ አደራ ጠባቂዎች ነን፤ ሌላ አላማ የለንም።” ሻለቃ መሳፍንት ተስፉ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሻለቃ መሳፍንት ተስፉ_ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የጠቅላላ ጉባኤው ሰብሳቢ ሲሆኑ መጋቢት 11/2014 በጎንደር ከተማ ባደረገው ታሪካዊ መድረክ ከተናገሩት መካከል:_ ፋኖን አንድ ለማድረግ ጥረት ካደረግንበት ብዙ ጊዜ አልፏል። ጎንደር የመናገሻ ሀገር ነው፤ ፋኖም የአባቶቻችን ስም ነው። ጎንደር ለአማራ ምርኩዝ ቀኝ እጅ ነው! አማራ ክልል ለኢትዮጵያ የበኩር ልጅ ነው! ኢትዮጵያን ለመታደግ ከተፈለገ እኛ የህዝብ ልጆች ነን፤ የህዝብ አደራ ጠባቂዎች ነን፤ ሌላ አላማ የለንም። በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ሁሉም ይህን አደረጃጀት የፈጠሩትን አመሰግናለሁ ብለዋል። ተማምነን እንድንቀጥል በእግዚአብሔር ስም፣በፋኖ ስም እለምናችኋለሁ ብለዋል። በሰው ወሬ ታሪክን መርሳትና መጣላት የለብንም ሲሉም አክለዋል። ፋኖ ነጻ ያወጣውን መሬትን መንግስት እውቅና እንዲሰጥም እንፈልጋለን! አማራ ብሎም አፋር ብዙ መከራዎችን እንዲያዩ የተፈረደባቸው ናቸው። የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ጎጃምን በቀኛችን፣ ወሎን በግራችን እንዲሁም ሸዋን በግንባራችን አድርጎ አንድ ሆኖ እንደሚታገልም ገልጸዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply