‘እኛ የሥልጣን ፖለቲካ ወይስ ፖለቲካ ውስጥ ነን?’ – ፀጋዝአብ ለምለም ተስፋይ (ሸክም የበዛበት ትውልድ፡2009 እና የምሰራቃዊት ኮከብ፡ 2010 መጻሕፍት አዘጋጅ)

 

የሀገራችን ወቅታዊ ኹለንተናዊ ነባራዊ ኹኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ የሚያሳዝንና የሚያስጨንቅ መኾኑ አያጠያይቅም፡፡ ከሰው ልጅ የታሪክ ሂደት አንጻር ከዚህ በላይ እጅግ የከፉ ጊዜያት አልፈዋልና ይህም የሂደት ውጤት ነው ካላልን በቀር እውነታውን (reality) ና እውነቱን (truth) የምናይበት መንገድ መለያየት ካልኾነ በቀር መሬት ላይ ያለው ጥሬ ሃቅ ብዙ አያከራክርም፡፡ የዕይታው ልዩነት ግን ብዙ ያነጋግራል፣ ያወያያል፣ ያጨቃጭቃል ብሎም ያለያያል፡፡

በዚህ ውስጥ ጎልተው ከሚታዩ ድምጾች መሐከል ብዙዎች በሀገራችን መልካም የኾኑ ነገሮች እንዲኖሩ እንመኛለን፣ እንጥራለን ብሎም እንገልጻለን፡፡ እኛ የተመኘነው፣ የምንጥርለት እና የምንገልጸውን ማግኘት የምንችልበት ምቹ ኹኔታ ላይ ነን ወይ? በዕምነት፣ በዕውቀትና በድርጊት ደረጃ ያን ለማምጣት የሚያስችል ዝግጁነት አለን ወይ? በአስተሳሰብና በአመለካከት ደረጃ አበልጽገነዋል ወይ? የአ‘‘ር ዘይቤያችን አካል አድርገነዋል ወይ? ብለን መጠየቅ ላይ እጅግ ከፍ ያለ ክፍተት አለፍ ሲልም ዝቅጠት በሰፊው እናገኛለን፡፡

ብዙዎች በሀገራችን የፖለቲካ ፍሬ የኾኑ ዲሞክራሲያዊነት፣ የሀሳብ ልዩነት መከበር፣ መደማመጥ፣ በሀሳብ የበላይነት ማመን፣ ፍትህ፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት፣ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የእኩልነት፣ የነጻነት፣ ከጠላትነት ነጻ የሆነ – – – ወዘተ ትላልቅ ጽንሰ ሀሳቦች በተግባር ተተርጉመው ማየት እንሻለን፡፡ መሻቱ መልካም ነው – ግን ይህን መሻት መሬት ላይ ለማግኘት የመሬቱ አይነት፣ የመሬቱ ባለቤትና ተጠቃሚ አይነት፣ የመሬቱ ተመልካች የአስተሳሰብና አመለካከት ኹለንተናዊ ደረጃ እጅግ ወሳኝ መኾኑን ብዙዎች ዘንግተናል፡፡

እኛ ዕውን የሥልጣን ፖለቲካ ወይስ ፖለቲካ ውስጥ ነው ያለነው? ያለንበት የትላንትም ኾነ የዛሬ ኹለንተናዊ ነባራዊ ኹኔታ ያለንበትንና የምንኖርበትን ይወስናል እንጂ የኛ ህልም፣ ስሜትና ቅዠት ያን ያክል ሥር ነቀል ለውጥ አያመጣም፡፡ የምናገኘውም ኾነ ልናገኝ የምንችለው ኹለንተናዊ ፍሬም ከዚሁ የሚነሣ ይኾናል፡፡ ስንዴ ዘርቶ ማንጎ፤ ጤፍ ዘርቶ ቦቆሎ፤ ባህር ዛፍ ተክሎ ወይራ – – – እንደማይገኝ እናውቃለን – በተግባር ግን መሻታችንን፣ ገለጻችንን እና ጽሑፋችንን ብንመለከት ተቃርኖ እንመለከታለን፡፡ ምን አይነት ኢትዮጵያ እንሻለን? ከማለት በፊት ምን አይነት ኢትዮጵያ ናት የነበረችንና ያለችን? ብሎ መጠየቅ እጅጉን ያስፈልጋል፡፡

በዓለም የሰው ልጅ ታሪክ እንደታየው ኹሉ በሀገራችን የረዥም ጊዜ ታሪክ ውስጥ የነገሥታትና የፊውዳሊስት ታሪክ ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረ ከመኾኑም ባሻገር ከዛ ከተላቀቅን /ተላቀቅን ካልን/ ግማሽ ክፍለ ዘመን (ሃምሳ ዓመት) እን£ አልሞላንም፡፡

ነገሥታት በባሕሪያቸውና በጠባያቸው ነገሥታቱ ይለያያሉ እንጂ አስተሳሰባቸውና አመለካከታቸው ተመሳሳይ ነው፡፡ ለአብነት፡- በጣዖትም የሚያመልኩት ይኹኑ በሚታወቁ ሃይማኖቶች የሚያምኑት ‘በፈጣሪ ተሾምን – በኃይላችን ነገሥን’ ይላሉ፤ በፈጣሪ እንደተሾሙም በብዙዎች ዘንድ ይታመናል፤ አነጋገሣቸው በርስ በርስ ትግል አልያም በወራሽነት ይኾናል፤ መግዢያቸውም ግን ኃይል ነው፡፡

የነገሥታትና ፊውዳሊስት አገዛዝ በባሕሪው ሀገራዊ /ሀገራዊ ብሔርተኝነትን በማቀንቀን/½ ከባቢያዊ /ከባቢያዊነትን ከትውልድ ሥፍራ ጋር በማስተሳሰር/ና ሃይማኖታዊ ተuማዊነትን በመላበስ /የሃይማኖት ባሕሪያዊ ማንነትን ሳይኾን ጠባያዊ ማንነት የኾነውን ተuማዊነት በመያዝ/ እንዲሁም ሕልውናውን በጠላት መኖርና በኃይል ላይ ያደረገና የሚያደርግ የሥልጣን ፖለቲካ ነው፡፡ መነሻውም ኾነ መዳረሻው ሥልጣን ነው፡፡

ከየትም ይነሣ ከየትም ይምጣ፤ ክርስቲያንም ይኹን ሙስሊም፤ የሚታወቅ ጣዖት አምላኪ ይኹን በማይታወቅ አምላክ የሚያምን፤ የሀገር ውስጥ ይኹን የውጭ – – – ነገሥታትና ፊውዳሊስቶች በጠባያት ካልኾነ በቀር በባሕሪያቸው ተመሳሳይ ናቸው፡፡

ነገሥታትና ፊውዳሊስቶች ሀገራዊነትና ከባቢያዊነትን ብቻ ሳይኾን የሃይማኖት ተuማትን ጭምር ወደ ሥልጣን ለመምጫነት½ ሥልጣን ለመጠበቂያነትም ኾነ ሥልጣንን ለማስተላለፊያነት ተጠቅመውበታል፡፡ የነገሥታቱና የፊውዳሊስቱን ያክል ባይኾንም የሃይማኖት ተuማትም በተለይ በውስጥ የሚያገለግሉ ተጠቃሚ ኾነዋል፡፡

የሃይማኖት ትልቁ የዕይታ አድማስ ነገሮችን ከውጤትና ከመዳረሻ (end) አንጻር ሳይኾን ከመነሻና ከመሣሪያ (means) ጋር ከዋናው ማዕቀፍ አንጻር መመልከት ነው፡፡ ከገንዘብ ይልቅ በምን መንገድና ለምን የሚውል ገንዘብ;፤ ከጾታዊ ግንኙነት ባሻገር ከማንና መቼ;፤ ከሥልጣን ባሻገር በምን መንገድ የተገኘና ለምን የሚውል ሥልጣን; እንጂ ገንዘብ½ ወሲብ½ ሥልጣን – – – ኹሉ በራሳቸው ኃጥያትም ኾነ ጽድቅ አይደሉም፡፡ ኹለቱን በመሠረታዊነት የሚለያቸው አመጣጣቸውና ዓላማቸው ነው፡፡ መለያውም የሃይማኖቱ ማዕቀፍ ይኾናል፡፡

የሥልጣን ፖለቲካ ግን ነገሮችን የሚመለከተው ከሥልጣን መነሻና መዳረሻነት አንጻር በመኾኑ ስለመሣሪያና መንገዶቹ ከሃይማኖት ፈጽሞ የተለየ ነው፡፡ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ግን የሃይማኖት ተuማት በዚህ አስተሳሰብና አመላካከት የበላይነት በመዋጣቸው – ባሕሪያቸውን ሲተውና መጠቀሚያ ለመኾን በቅተዋል፡፡ ይህም ያለ ሃይማኖት ልዩነት በክርሲያኑም ኾነ በሙስሊሙ እንዲሁም በሌላው በመላው ዓለም የነበረ ነው፡፡

በዚህ የሥልጣን ፖለቲካ አስተሳሰብና አመለካከት በእምነት½ በእውቀትና በድርጊት ደረጃ ቅኝ በገዛበት ሕብረተሰብ ውስጥ ኃጥያት ጽድቅ፤ ጽድቅም ኃጥያት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ጀብደኛ ጀግና ይደረጋል፤ ጀግናም በአንጻሩ ጀብደኛ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ባንዳ ይሸለማል – አርበኛ ይወቀሳል፡፡ ስለእውነት ሰዎች በአደባባይ ዋጋ ሲከፍሉ ብዙዎች እውነት ማን ጋር እንዳለ ያውቃሉ፡፡ ግን እውነተኛን ለመከላከልና ለመጠበቅ ዋጋ አይከፍሉም፡፡ &ማወቁን እናውቃለን – እንዳንናገር እናልቃለን& በሚል የሥልጣን ፖለቲካ ብሂል አብዝሃ ከእውነት ይልቅ በሀሰት መኖርን ይመርጣል፤ በእውነት ዋጋ ከመክፈል ይልቅ በሀሰት ዋጋ መክፈልን፤ በማወቅና ባለማወቅ መሐከል ድንበር አልባ መኾንን፤ በነጻነት ተጋድሎ ከመሞት ይልቅ የባርነት ሞትን ይመርጣል፡፡

ሙሰኝነት ያስከብራል፡፡ ሙሰኛን ሕብረተሰቡ በደንብ ያውቃል – ከሱ ጋር መዛመድ½ መብላት½ መጠጣት½ መታየት½ መግባባት – – – ወዘተ የሚሻውም – ይኸው ሕብረተሰብ ነው፡፡ ሃብቱ የተዘረፈው ሕብረተሰብ ራሱ ከሙሰኛው ጋር አብሮ መብላትና መጠጣትን በእጅጉ የሚሻ ይኾናል፡፡ ገዳዩን የሚወድ ሕብረተሰብ የሥልጣን ፖለቲካ አስተሳሰብና አመለካከት ቅኝ ተገዥነት ማሳያ ነው፡፡

ከገንዘብ በላይ ስለገንዘብ ምንጭ /ከየት; እንዴት; መቼ;/፤ ከሥልጣን በላይ ስለሥልጣን ምንጭ /ለምን; በምን; ለማን;/ – – – ላይ የጠራ ግንዛቤና መረዳት የሌለው ሕብረተሰብ የሥልጣን ፖለቲካ የበላይነት መገለጫው ነው፡፡

የሥልጣን ፖለቲካን ከታሪክ አንጻር የሩቁን ትተን በዘመነ መሳፍንትም ኾነ ከዛ በኃላ በኢትዮጵያ ዘመናዊ መንግሥት ታሪክ ባሉት አራት ነገሥታቶቻችን መሐከል (አጼ ቴዌድሮስ½ አጼ ተክለ ጊዮርጊስ½ አጼ ዮሃንስም ኾነ አጼ ምኒልክ) መሐከል መሠረታዊ ልዩነቱ ምንድነው; እርስ በርስ ያባላቸው ነገር ምንድነው; ብሎ መጠየቅ የጉዳዩን ፍሬ ነገር ለመረዳት በእጅጉ አስፈላጊ ይኾናል፡፡

ኹሉም ነገሥታት – እጅግ በከፊል ፊውዳሊስት፡ ነገሥታት ለመኾን የሚሹ½ ‘ፈጣሪ ሾመን’ ያሉ½ ስማቸውን የቀየሩ½ በፍትሐ ነገሥት ለመተዳደርና ለማስተዳደር የተጉ እንደመኾናቸው መጠን ይሄ ነው የሚባል መሠረታዊ ልዩነት የሥልጣን ፖለቲካን የመያዝና የማስጠበቅ ብሎም ጊዜና ወቅቱ ያመጣቸውን ነገሮች ከመያዝ ላይ ያያዝ ግለሰባዊ ልዩነት ካልኾነ በቀር በኹሉም ዘንድ የነገሮች /ሁነቶች/ መነሻና መዳረሻ ሥልጣንን በኃይልና በገዥነት ሥነ ልቦና መያዝ መኾኑ የሚታወቅ፤ በአስተሳሰብና አመለካከትም ኾነ በአገዛዝ መርሃቸው በመሠረታዊ መርሆዎች ላይ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ነገሥታቱ ነገሥታት ከመኾናቸው በፊትም ኾነ በኃላ በጊዜው በነበረው የነገሥታትና ፊውዳሊስ አስተሳሰብና አመለካከት ቅኝ የተገዙ ከፍ ሲልም አስፈጻሚ ለመኾን የሻቱና የኾኑም ናቸው፡፡

ቁም ነገሩ ያለው የሰዎች መለዋወጥ ውስጥ ስለምን መሠረታዊ ልዩነት ማየት ተሳነን; ለምንስ አልቻልንም; ይህም ኾኖ እርስ በራስ በእጅጉ ለምን ተበላሉ;

በርግጥ የነገሥታትና የፊውዳሊስቶች ሂደት በእምነት½ በእውቀትም ኾነ በተግባር የዓለም ሕዝብ በሂደት ያያቸው የአስተሳሰቡና አመለካከቱ ደረጃ ውጤት መኾናቸውን ከማዕቀፍ አንጻር ለሀገራችንም ቢኾን መዘንጋት አያሻም፡፡

አውሮፓውያን በትምህርት½ በኢኮኖሚ ዕሳቤ መስፋፋትና መዳበር½ በሳይንስ ስፋት½ በኢንዱስትሪ መጀመርና መዳበር½ በዓለም አቀፍ ግንኙነት መጠናከርና በእጅጉ መተሳሰር½ በአስተዳደር ጽንሰ ሀሳብ መጎልበት½ በቴክኔሎጂና ግኝቶች ዕድገት½ በትግል½ በለውጥ ማዕበሎች – – – በመነሣት ከኛ ቀደም ብለው ከሥልጣን ፖለቲካ ወደ ፖለቲካ ኹለንተናዊ እንቅስቃሴ ተሸጋገሩ፡፡

የነገሥታትና ፊውዳሊስቶች ባሕሪያትና ጠባያት – በጀግንነት እየተወደሱ መኖር½ ዳር ድንበር ማስከበር½ ራስን ለመጠበቅ ዘወትር መትጋት½ በትላንት ማዕቀፍ ውስጥ መኖር የጀርባ አጥንቱ ነው፡፡

ይህ የዓለም ሕብረተሰብ በሙሉ ያለፈበት ነው፡፡ ልዩነቱ አንዳንድ ሕብረተሰቦች ቀድመው ከዚህ አገዛዝ ከክፍለ ዘመናት በፊት ሲወጡ ሌሎች በቅርብ ጊዜ ውስጥ ካልኾነ በቀር የጠባይ እንጂ የባሕሪ ልዩነት ፈጽሞ የላቸውም፡፡ በእሳት መቃጠል በየትም ቦታ በእሳት መቃጠል ነው፡፡ ልዩነቱ የእሳት መጠን½ አቃጣይ½ የተቃጣይ½ የመቃጠል ቆይታ½ የመቃጠል መጠን½ የማቃጠያ አስፈላጊ ነገሮች ልዩነት½ የመቃጠል ውጤት ካልኾነ በቀር መቃጠል መቃጠል ነው፡፡ ማቃጠልም ማቃጠል ነው፡፡

በነገሥታትና ፊውዳሊስት ውስጥ ሥልጣን ማለት ምን ማለት እንደሆነ በጥልቀት መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ሥልጣን ለነገሥታትና ፊውዳሊስቶች ኹሉ ነገራቸው (everything) ነው፡፡ የኢኮኖሚ½ የክብር½ የታሪክ½ የዝና½ የኩራት½ የምቾት½ የአ‘‘ር ዘይቤ½ የሕይወት ትርÕሜ½ የበላይነት ማሳያ  – – ምንጭ ነው:: እነዚህም፡- በእጅ በተያዙ ብቻ ሳይኾን በእጅ እንዲያዙ የሚፈለጉን፤ የዛሬን ብቻ ሳይኾን የነገ ጭምር፤ የራስ ብቻ ሳይኾን የትውልድ /ትውልድ ተሻጋሪ/ ፍላጎትን የሚይዝ ነው፡፡ ሥልጣን ማጣት ማለት ኹሉን ነገር (everything) ማጣት ነው፡፡ ዛሬን ብቻ ሳይኾን ነገን ጭምር ማጣት ነው፡፡ በሌላ uንu የሕልውና ጉዳይ ይኾናል፡፡ ለዚህም ነው አባት ልጁን½ ልጅ አባቱን½ ወንድም ወንድሙን½ ዘመድ ዘመዱን ከቅርብ ኾነ ከሩቅ – – – ሲገዳደሉ የነበሩት፡፡ ኹለንተናዊ ትግሉ ከሥልጣኑ በላይ ሥልጣኑ የተሸከመው ነው፡፡

ሥልጣኑ ሥልጣን ለያዘውና ለመሰሎቹ ብቻ ሳይኾን ለልጆቹና ለልጆቻቸው ብሎም ለአካባቢያቸው ሰዎች ታሪክ እንደኾነና እንደሚኾን ያምናሉ፤ ይረዳሉ፡፡ ለዚህም ኹለንተናዊ ዋጋ ለመክፈል ሙሉ በሙሉ ዝግጁዎች ናቸው፡፡ አሸናፊነቱና ተሸናፊነቱም እንዲሁ በንቃትም (consciously) ኾነ ያለንቃት (unconsciously) ትግሉ የትላንትና የዛሬ ብቻ ሳይኾን የነገም ጭምር ነው፡፡

ይህ አስተሳሰብና አመለካከት በእምነት½ በእውቀትም ኾነ በድርጊት ደረጃ ገዥውንም ኾነ ተገዥውን ቅኝ የገዛ ነበር፡፡ የሚያሳዝነው የሃይማኖት ተuማት (ሃይማኖት ሳይኾን የሃይማኖት ተuማት፤ ባሕሪያዊ የሃይማኖት ማንነት ሳይኾን ጠባያዊው የሃይማኖት ማንነት) ሳይቀር ጠባያዊ ማንነታቸው ባሕሪያዊ ማንነታቸውን ጋርዶ የሥልጣን ፖለቲካ ቅኝ ተገዢዎችና ዋና ተዋንያን በመኾን ወሳኝ አሻራን አሳርፈዋል፡፡

ይኸውም የሥልጣን ፖለቲካ በባሕሪው ጥብቅ (rigid)½ ወግ አጥባቂነት (conservatism) የሚጎላበት½ ለለውጥ እጅግ ዘገምተኛ (static behaviours) የሚኾን½ ከወደፊት ይልቅ ከኃላ ትላንት አንጻር ነገሮችን የሚመለከት /የትላንት ማዕቀፍ ቅኝ ተገዢ/½ በትንሹ የሚረካ½ የታሪክ ፍጻሜ ቅኝ ተገዥ /በታሪክ ለመኖር የሚተጋ/½ የገዥነት /managerial/ ባሕሪያትና ጠባያትን የሚላበስ½ ትርጉም ያለው ትውልድ ተሻጋሪ ራዕይ½ ግብና ዓላማ የሌለው½ በሀሳብ ድህነት እጅጉን የተዋጠ፣ ጠላትነትን ከህልውናው ጋር ያስተሳሰረ፣ በኹኔታዎች የሚመራ ሲኾን ፖለቲካ በአንጻሩ የመሪነት (leadership) ባሕሪያትና ጠባያትን የሚይዝ½ ከኹኔታዎች ጋር ራሱን መቀየርና ማሻሻል የሚችል (flexible)½ ለለውጥ ከፍተኛ ፍላጎት (eagerness) ያለው½ ነገሮችን ከወደፊት አንጻር የሚመለከት½ በትንሹ የማይረካ½ ታሪክ ለመስራት የሚተጋ½ ትርጉም ያለው ትውልድ ተሻጋሪ ራዕይ½ ግብና ዓላማ የሚኖረው½ በሀሳብ የበላይነት የሚያምን፣ ሀገራዊነትንና ሀገራዊ ማዕቀፍን የህልውናው መሠረት የሚያደርግ፣ ኹኔታዎችን የሚመራ ነው፡፡

በሌላ በኩል የ’ሥልጣን ፖለቲካ’ የራስ አሸናፊነትን ብቻ ሳይኾን የሌላውን ተሸናፊነት ጭምር በተግባር ማረጋገጥ ይሻል¿ ከመኖር ባሻገር የሌላው አለመኖርን፤ ከማግኘት ባሻገር የሌላው አለማግኘትን/ማጣትን፤ ከመበልጸግ ባሻገር የሌላው መደህየትን፤ ከግማሽ ማግኘት ሙሉ ማጣትን፤ ከመቆጣጠር ባሻገር የሌላው ሎሌነትን፤ ከመተባበር ባሻገር የሌላው አለመተባበርን የሚሻ – እንደጦርነት ስልት ራስን ከማጠንከር ባሻገር ሌላውን ማዳከምን የሚይዝ – ሁለት ስለት ያለው ጠላት ፈላጊ እንዲሁም ጠላት ‘ፈጣሪ’/አድራጊ ነው፡፡ በዚህም የተነሣ መተማመን አልባ ይኾን ዘንድ ግድ በሚልበት ኹኔታ የሚኖርና የሚልበትን ምቹ ኹኔታ የሚፈጥር ነው፡፡

‘የሥልጣን ፖለቲካ’ ትልቁ መለያ እንደኔ ካላሰባችሁ½ እንደኔ ካልሆናችሁ½ እንደኔ ፈቃድ½ የኔ መንገድ ብቻ½ እኔን ብቻ½ በጋራ እናስብ – – – የሚል ኾኖ እናገኘዋለን፡፡ ይህም ኢ-ተፈጥሯዊና ከሰው ልጅ ባህሪ አንጻር የሚቃረን ነው፡፡ ሰው በጋራ ማሰብ አይችልም፡፡ ሀሳብን የጋራ ማድረግ እንጂ በጋራ ማሰብ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ሰው የአንዱን ሀሳብ ጨምሮም ይኹን ቀንሶ አልያም እንዳለ የጋራ ሊያደርግ ይችላል እንጂ በፍጹም በጋራ ሊያስብ አይችልም፡፡

የሥልጣን ፖለቲካ ግብ ሥልጣንን ማስጠበቅ ሲኾን የፖለቲካ ግብ ሀገራዊ ግንባታ (nation building) እና ሕብረተሰብን ማነጽ (reshaping society) ፤ የሥልጣን ፖለቲካ መነሻና መዳረሻ ሥልጣን ሲኾን የፖለቲካ ሀገራዊነት፤ ለሥልጣን ፖለቲካ ሥልጣን መጨረሻው (end) ሲኾን ለፖለቲካ መሣሪያው እንጂ መጨረሻው አይደለም (means not an end)፤ የሥልጣን ፖለቲካ ጠላትነትና ኃይል የሕልውናው መሠረት ሲሆን ለፖለቲካ ሀሳብና ተuማዊነት የህልውናው መሠረት፤ በሥልጣን ፖለቲካ ሥልጣን ኹሉ ነገሩ (power is very thing) ሲኾን ለፖለቲካ ሀገራዊ ማዕቀፍ ኹሉ ነገሩ (national framework is everything) ነው፡፡

የሀገራችን ፖለቲካ ጠቅለል ባለ መልኩ ስንመለከተው በእምነት½ በእውቀትና በድርጊት ደረጃ ‘የሥልጣን ፖለቲካ’ ቅኝ ተገዢ ነው፡፡ ሥልጣን ላይ የነበሩ½ ያሉት½ የሚሹትም ኾኑ ከዛ ውጭ ያለነው በአስተሳሰብና በአመለካከት ደረጃ ‘የሥልጣን ፖለቲካ’ ቅኝ ተገዥዎች ነን፡፡ በምዕራባውያን ድሃውም ኾነ ባለሀብቱ በተመሳሳይ ደረጃ የካፒታሊስታዊ ሀሳብ ተጽዕኖ እንዳለበት – በዚህም ‘ካፒታሊስታዊ ነው’ ሲባል ካፒታል ያለው ብቻ ሳይኾን የሌለው የባለካፒታሉ ባሪያ የኾነው ጭምር ካፒታሊስታዊ እንደኾነው ኹሉ – እኛም ያለ ልዩነት ‘የሥልጣን ፖለቲካ’ ቅኝ ተገዢዎች ነን፡፡

ስለኾነም የሥልጣን ፖለቲካን ወደ ፖለቲካ ማሳደግና ማበልጸግ አልቻልንም፡፡ የእውነታ ፖለቲካን (real Politics) ከእውነት ፖለቲካ (truth Politics) ጋር አብሮ ማስኬድ አልተቻለም፡፡ በዚህም በሀገር ኹለንተናዊ ሂደት መኾን የነበረበት እየኾነ ካለው ጋር ማጣጣም፤ ጽንሰ ሀሳብን ከተግባር ጋር ማቀራረብ አልተቻለም፡፡

ታድያ ያለነው የሥልጣን ፖለቲካ ውስጥ ኾኖ እንዴት የፖለቲካ ውጤት/ፍሬ እንጠብቃለን? ዛሬ ያለንበት ነባራዊ ኹለንተናዊ ነባራዊ ኹኔታ የአስተሳሰብና አመለካከታችን ውጤት መኾኑን እንዴት እንዘነጋለን?

በመኾኑም በሀገራችን እውነተኛ ለውጥ የምንሻ ከኾነ መወያየት ያለብን ያለንበት ነባራዊ ኹለንተናዊ ኹኔታ ምን ይመስላል? ከሥልጣን ፖለቲካ እንዴት ወደ ፖለቲካ እንሻገር? ከኃይል ወደ ሀሳብ፤ ከገዥነት ወደ መሪነት የፖለቲካ ዕሳቤ እንዴት እንሻገር? ፈጣሪ ሀገራችን ነጻ ፍቃድን የኹሉ ነገር ማዕከል ወደሚያደርግ የዕሳቤ ሂደት ትገባ ዘንድ ይርዳን!

ቸር እንሰንብት!  

Leave a Reply