“እውነተኛ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ ፣ሰላምን ያወኩ ተጠያቂ መሆን አለባቸው “አምባሳደር ታየ አጽቀ ስላሴ

https://gdb.voanews.com/0F609EBA-0E72-437E-884A-858CCFD1F3DF_w800_h450.jpg

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት ለህዝብ ደህንነትና ህልውና አስፈላጊ የሆኑ ተቋማት ጥበቃ ሊደረገግላቸው በሚችልበት ጉዳይ ላይ ባደረገው ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት በመንግስታቱ ድርጅቱ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሆኑት ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ታጣቂ ሀይሎች ሆን ብለው ለህዝብ መሰረታዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ በመግለፅ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

የታጠቁ ሀይሎች ሆን ብለው በእርሻዎች፣ የውሀ ማስተላለፊያ ቱቦዎችና የጤና ተቋማት ላይ ቦምብ በመጣል እንደሚያጠቁና ህዝብ መሰረታዊ መገልገያውን እንዲያጣ እንደሚያደርጉ የገለፁት አምባሳደር ግሪን ፊልድ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለውን ግጭት እንደማሳያ አቅርበዋል።

“በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያልው ውጊያ የህዝብ መገናኛ አውታሮች እንዲቋረጡ፣ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሽቦዎች እንዲወድቁ፣ ሆስፒታሎች እንዲዘረፉና ከጥቅም ውጪ እንዲሆኑ አድርጓል። የትግራይ ህዝቦች መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ለደህንነታችው አስጊ የሆኑ በተለይ ፆታዊ ጥቃት የሚፈፀምባቸው ረጅም ጉዞዎች እንዲጓዙ ተገደዋል” ያሉት አምባሳደር ግሪንፊልድ በትግራይ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆምም ጠይቀዋል።

ከአምባሳደሯ ንግግር ጋር በተያያዘ የመንግስታቸውን አቋም የጠየቅናቸው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ በበኩላቸው ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የህዝቦች ሰላማዊ ኑሮ እንዳይታወክ በተቻለው አቅም እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ፣ “እውነተኛ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ  ሰላምን ያወኩ ተጠያቂ መሆን አለባቸው” ብለዋል።

ከአምባሳደር ታየ ጋር የተደረገውን አጭር ቆይታ ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply