
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቀውስ በኦሮሚያ ክልል በተባባሰው ፖለቲካዊ እና ብሔር ተኮር ውጥረት ሳቢያ እጅጉን ተባብሷል። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከዚህ ቀደም ሊደርስባቸው ወዳልቻላቸው ከተሞች እየቀረበ ጥቃት እየፈጸመ ነው። ቀውሱን ለመግታት ከቡድኑ ጋር ንግግር የማድረግ ሐሳብን ገሸሽ ያደረገው መንግሥት፣ ምላሽ እየሰጠ ያለው ወታደሮች በማሠማራት እና የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት በማካሄድ ነው።
Source: Link to the Post