እየተሰጠ ያለው የሰብዓዊ ድጋፍ ተመጣጣኝ አለመሆኑን የመቀሌ ከተማ ከንቲባ አስታወቁ፡፡

 በጦርነቱ ብዙ የመሰረተ ልማት አገልግሎት መስጫ ተቋማት  ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች የኢኮኖሚ ጥገኛ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ተብሏል፡፡የመቀሌ ከተማ ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለስላሴ ለአሐዱ እንደተናገሩት በመቀሌ ከተማ የኤሌትሪክ ኃይል፣ የውሀ፣ የባንክ እንዲሁም የመንግስት የጤና ተቋማት ለማህበረሰቡ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡የማህበረሰብ አገልግሎት መስጫ ከሆኑት አንዱ ትምህርት አለመጀመሩን የተናገሩት ከንቲባው ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ግን በየወረዳና ዞኖች እንዲሁም ክፍለ ከተሞች ለማዳረስ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በመቀሌም አገልግሎት ለሚሰጡ የጤና ተቋማት 16 ሚሊየን ብር የሚገመት መድኃኒቶችና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፋ መደረጉን አስታውሰዋል፡፡መሰረተ ልማቶች የማሟላት ስራው እየተሰራ ነው ያሉት አቶ አታክልቲ ጦርነቱ  ባስከተለው የኢኮኖሚ ጫና በርካቶች የሰብዓዊ እርዳታን እንዲጠብቁ አድርጓቸዋል ብለዋል፡፡የሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ እና እየተደረገ ያለው እርዳታ ተመጣጣኝ አለመሆኑ የሚፈለገውን ያህል ተደራሽ ማድረግ እንዳይቻል ሆኗል ብለዋል፡፡

የፌደራል መንግሥትና ጊዚያዊ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ሲሆን የሰብዓዊ በእርዳታ ለማድረግ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ድጋፋ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

**********************************************************************

ዘጋቢ፡ፍቅርተ ቢተው

ቀን 21/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply