You are currently viewing “እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ የአገሪቱን እና የዜጎችን ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ዉስጥ ያላስገባ ነው።” ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አወገዘ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

“እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ የአገሪቱን እና የዜጎችን ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ዉስጥ ያላስገባ ነው።” ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አወገዘ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

“እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ የአገሪቱን እና የዜጎችን ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ዉስጥ ያላስገባ ነው።” ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አወገዘ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ዙሪያ ህገ-ወጥ ናቸዉ የተባሉ ቤቶች በዘመቻ መልክ እየፈረሱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሀይሌ በአዲስ አበባ ዙሪያ እና ቡራዩ አካባቢ ቤት እየፈረሰባቸዉ ያሉ በርካታ ዜጎች ወደ ተቋሙ እየመጡ እንደሆነ ለአሐዱ ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ “ተቋማችን ሕገ-ወጥነትን አያበረታታም!“ ያሉት ዶክተር እንዳለ፤ አሁን እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ ወቅታዊ ሁኔታን ታሳቢ ያደረገ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ “ጉዳዩን በሕገ-ወጥነት መነጽር ብቻ መመልከት አግባብ አይደለም” ያሉት ዋና እንባ ጠባቂዉ፤ “የበአል ወቅት እንደመሆኑ በርካታ ተፈናቃዮች በተለያዩ ክልሎች እንደመኖራቸዉ እና ወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ በዘመቻ መልክ ይህን ለመፈጸም አስቻይ አይደለም” ሲሉ አስረድተዋል፡፡ “ሰዎች ሕገ-ወጥ አሊያም ሕግን ባልተከተለ መንገድ ቤት ከገበሬ ላይ የሚገዙበትን ምክንያት የመንግስት አካላት ሊያጤኑት ይገባል” ያሉት ዋና ዳሬክተሩ፤ “የመሬት ፖሊሲን፣ በቂ የቤት አቅርቦት እና ተደራሽነት መኖር እና የቤት ሽያጭ ስርዓቶች በሕግ ማእቀፍ ዉስጥ ያሉ ናቸዉ ወይ የሚለዉን ከግምት በማስገባት ማስተካከያዎችን መዉሰድ አለባቸዉ” ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ስለመናገራቸው አዲስ ማለዳ አጋርቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply