እያደር ጥሬ በሚሆነው የሃገራችን ፖለቲካ ውስጥ መቀጠል የምችለው እስከመቼ ነው? – ልደቱ አያሌው

ስቃያችሁ መቋጫ የሌለው እንዲሆን በማድረግም አብዝቼ በድያችኋለሁና ይቅር በሉኝ። ልደቱ አያሌው

" 27 ሲደመር 2 " -- አዲስ መጽሐፍ  ****************************** "ኢትዮጵያ -አዲስ አምባገነናዊ ሥርዓት በማዋለድ ሂደት" የሚል ርዕስ የተሰጠው የልደቱ አያሌው  መጽሐፍ ለህትመት ወደ ማተሚያ ቤት ከመሔዱ ጥቂት ቀደም ብሎ የተቀየረው የመጽሐፉ የመጀመሪያ ርዕስ " ከድጡ ወደ ማጡ" የሚል ነበር።  ” 27 ሲደመር 2 ” — አዲስ መጽሐፍ  “ኢትዮጵያ -አዲስ አምባገነናዊ ሥርዓት በማዋለድ ሂደት” የሚል ርዕስ የተሰጠው የልደቱ አያሌው መጽሐፍ ለህትመት ወደ ማተሚያ ቤት ከመሔዱ ጥቂት ቀደም ብሎ የተቀየረው የመጽሐፉ የመጀመሪያ ርዕስ ” ከድጡ ወደ ማጡ” የሚል ነበር።
የዚህን መፅሃፍ ረቂቅ ፅፌ ጨርሼ ወደ ማተሚያ ቤት ለማስገባት በዝግጅት ላይ እያለሁ ከአንድ አጎቴ፣ አንድ ምሽት ላይ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ፡፡ ይህንን የስልክ ጥሪ ላለፉት ሁለት ወራት ከነበርኩበት የስሜት ውጣ-ውረድ ጋር ተዛማጅ ሆኖ ስላገኘሁት በቀላሉ ልረሳው አልቻልኩም፡፡ ስለ አጎቴ የስልክ ጥሪ ይዘት ከማውራቴ በፊት በቅድሚያ ባለፉት ወራቶች ስለአጋጠሙኝ ስሜት አዋኪ ሁኔታዎች ትንሽ ለማለት ልሞክር፡፡ ²

ከአቶ ጀዋር መሐመድ ጋር በኦ.ኤም.ኤን ቴሌቪዥን ለቃለ መጠይቅ ተጋብዤ ከቀረብኩ በኋላ ከዓመት በፊት መቀሌ ሄጄ በአንድ ስብሰባ ላይ በተገኘሁበት ወቅት ሲሆን እንደታየው ከፍተኛ የአሉባልታ ዘመቻ ተከፈተብኝ፡፡ በዚያ የአሉባልታ ዘመቻ ላይ ከመንግስት ባለስልጣናት ጀምሮ በርካታ ታዋቂ የሚባሉ ሰዎች ሲረባረቡብኝ አየሁ፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያምን የመሰሉ ትልቅ የሃገር ምሁርና አዛውንት ሳይቀሩ በእኔና ጀዋር ላይ መንግስት ሰይፉን እንዲመዝብን በአደባባይ ሲመክሩ ሰማሁ፡፡ አንዳንድ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎችም በስልኬ ላይ እየደወሉ እንደሚገሉኝ ሲዝቱብኝ ሰነበቱ፡፡ አንዳንድ ከእኔ ጋር ከረዥም ጊዜ ጀምሮ የቢዝነስ ግንኙነት የነበራቸው ሰዎችም ማንነቱን የማያውቁት ሰው ስልክ እየደወለ ከእኔ ጋር ስላላቸው ግንኙነት እንደጠየቃቸው ነገሩኝ፡፡

የኖቤል ሽልማት ተሸላሚው ዶ/ር ዐቢይም ከመስከረም 30፣

Source: Link to the Post

Leave a Reply