እድለኛው ባለመገኘቱ ስምንት ሚሊዮን ብሩ ተመላሽ ሊሆን ነው፡፡

የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕድለኛው ባለመገኝቱ ስምንት ሚሊዮን ብሩ ተመላሽ ሊደረግ መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

የ2016 ዓ ም አዲስ ዓመት ከወጣው ከ20 ሚሊዮን ብር የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አሸናፊ መካከል፣ የስምንት ሚሊዮን ብር እድለኛ ባለመገኝቱ ገንዘቡ ለመንግስት ተመላሽ ሊደረግ መሆኑን አስተዳደሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

ላለፉት ስድስት ወራት ያህል ባለእድለኛው የተጠበቀ ቢሆንም፣ አሸናፊ ነኝ የሚል አለመገኘቱን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድር አስታውቋል።

አሸናፊ የሚያደርገውን ትኬት የያዘው ሰው በኦሮሚያ ክልል፣ መተሃራ ከተማ ወይም በዛ ዙሪያ ሊሆን እንደሚችል የአስተዳደሩ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጸዋል።

ከትልልቆቹ ሎተሪዎች አንዱ የሆነው የእንቁጣጣሽ ሎቶሪ አዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ ወጥቶ እንደነበርና 12 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው ትኬት ገተዝው የነበሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሽልማታቸውን እንደወሰዱም አቶ ቴዎድሮስ ገልጸዋል።

20 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ቁጥር 1820259 መሆኑ ተገልጿል፡፡

የብሔራዊ ሎተሪ ዕጣ ከወጣ በኋላ በየትኛው ቅርንጫፍ ከስንት ቁጥር እስከ ስንት ያሉት ትኬቶች እንደተሰራጩ ስለሚታወቅ ትኬቱ የተሸጠበትን አካባቢ ማወቅ እንደሚቻል አስረድተዋል።

የመተሃራ ነዋሪዎች ወይም ለገበያ ከገጠር ከተማ የመጡ ሰዎች ትኬቱን ገዝተው ሊሆን እንደሚችል የገለጹት አቶ ቴዎድሮስ፣ አሸናፊ የሚያደርገውን ትኬት የገዛ ሰው ገንዘቡን እስከሚወስድ የሚጠበቀው ለስድስት ወራት እንደሆነ ተናግረዋል።

እናም እስከ ነገ ቅዳሜ ስድስት ሰአት ድረስ ካልመጣ ገንዘቡ ተመላሽ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply