እጅግ ስኬታማ ውሎ ነበረን “የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሪነህ። አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 26/2013 ዓ.ም ባህርዳር የክልላችን ልዩ ኃይል፣…

እጅግ ስኬታማ ውሎ ነበረን “የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሪነህ። አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 26/2013 ዓ.ም ባህርዳር የክልላችን ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የመከላከያ ሰራዊት በየደረጃው ያሉ ዓመራሮች እና አባላት በተቀናጀ መልኩ ያደረጉት ተጋድሎ ስኬታማ ነበር:: በትናንትናው ዕለት በሶሮቃ እና ቅራቅር ከዕኩለ ሌሊት እስከ ረፋድ ተደጋጋሚ ማጥቃት ተሰንዝሮብን ነበር:: ከረፋድ በኋላ በሰነዘርነው ማጥቃት በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጥረናል:: በተቆጣጠርናቸው ቦታዎች ያለው የህዝብ ድጋፍ ድንቅ ነበር:: በርካታ ያለፍላጎቱ እንዲዋጋ የተገደደ የፀጥታ ኃይል በሰላም እጁን ሰጥቷል:: እዋጋለሁ ብሎ የመረጠም ፊቱን አዙሮ እኛን ሲያግዝ ውሏል:: ጦርነት አንፈልግም ስንል ጠላታችን ድህነት ነው ከሚል እንጅ ጦርነት ካለማወቅ አይደለም:: ዛሬም በሌላ ድል ታጅቦ ያልፋል!

Source: Link to the Post

Leave a Reply