እግረኞችን መቅጣት መጀመሩን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ እስካሁን 89 እግረኞች የትራፊክ ደንብን በመተላለፍ እንዲቀጡ ማድረጉን ባለስልጣኑ አስታወቋል፡፡

በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እግረኞችን የሚቀጣ የህግ ማዕቀፍ አዘጋጅቶ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ነው ለ ኢትዮ ኤፍ ኤም ያስታወቀው፡፡

በአዲስ አበባ ካሉት 11 ቅርጫፎችም በለሚኩራ ክ/ከተማ ቅርጫፍ ስራው መጀመሩን ቅርጫፍ ፅህፈት ቤቱ ለጣብያችን አስታውቋል፡፡

የለሚ ኩራትራፊክ ማኔጅመንት ቅርጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ምስጋና ፋንታሁ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ቅጣቱ የተጀመረው በጎሮ አደባባይ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ቦታው በከፍተኛ ሁኔታ የትራፊክ መጨናነቅ የሚስተዋልበት በመሆኑና እግረኞች በመኪና መንገድ ላይ በመግባት አደጋ እየደረሱ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ተቀጪዎች የትራፊክ ፍሰቱን እንዲያስተባብሩ እና በመንገድ ትራፊክ መረጃ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲያኙ በማድረግ የተጀመረው የቅጣት ሂደቱ በቀጣይ የገንዘብ ቅጣትን ጨምሮ የተለያዩ እርምጃዎች እንደሚኖሩትም ተጠቁሟል፡፡

በጎሮ አደባባይ በተጀመረው ቅጣት እስካሁን 89 እግረኞች ደንብ ሲተላለፉ በመገኘታቸው ቅጣት ተላልፎባቸዋል ብለዋል፡፡

አሁን ላይ የገንዘብ ቅጣት መጣል ምቹ ሁኔታ ባይፈጠርም ከ40 ብር እስከ 80 ብር የሚደርስ ቅጣት በህግ ማዕቀፉ እንደተቀመጠ ኢትዮ ኤፍ ኤም ከባለስልጣኑ ሰምቷል፡፡

በለሚ ኩራ የተጀመረው እግረኞችን የመቅጣት ስራ በሁሉም አካባቢዎች ቀጣይነት እንደሚኖረውም ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአቤል ደጀኔ

የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply