ኦላፍ ሾልስ የጀርመን መራኄ መንግሥት ሆነው ዛሬ ተመረጡ። የቀድሞው የሀምቡርግ ከተማ ከንቲባ የ63 ዓመቱ ኦላፍ ሾልስ በፖለቲካ አቋማቸው ሶሻል ዴሞክራት ሲሆኑ፤ በምርጫው ከፍተኛ ድምፅ ካገኙ…

https://cdn4.telesco.pe/file/V9ngWHaVK0Kp9ukT9fJ_iN4w4wsaFhmkJuIxCgVXU6tyHmcwuyFiOk8wuN7fg3yWYoIRBcLL_CEl_m8Yq1giCuKtrQfQHSdS7varsKTHPrLA2b8AfvrNh67XsN8hjqRz8Q8PcnI3bX-hhf97AzIHNpAzG1vUiTmRVMzvKI8KEDlfKUUVRbtqBwyERWt_PJFmMzShuKycsIDjlyr8CAbIttruMPzAK15kVfmP_wVLG4j1xr6LQb1PKf2IT5iOKq8Kqmut_BWt8JR5Qg1Rq9GyydsDB-MwI2JfaNCBYWItAAhluddwNUUT4N7smgBt5OEge0QUaj4iJT97RBLm0Hy5iw.jpg

ኦላፍ ሾልስ የጀርመን መራኄ መንግሥት ሆነው ዛሬ ተመረጡ።

የቀድሞው የሀምቡርግ ከተማ ከንቲባ የ63 ዓመቱ ኦላፍ ሾልስ በፖለቲካ አቋማቸው ሶሻል ዴሞክራት ሲሆኑ፤ በምርጫው ከፍተኛ ድምፅ ካገኙት ከአረንጓዴ ፓርቲ እና ከነጻ ዴሞክራቶች ፓርቲዎች ጋር በመቀናጀት ሀገራቸውን ለመምራት ተስማምተዋል።

ሾልስ ዛሬ በጀርመን ምክር ቤት በተካሄደው ምሥጢራዊ የድምፅ አሰጣጥ ሂደትም ከ707 አባላት የ395ቱን በማግኘት ኦላፍ ሾልስ አዲሱ የጀርመን መሪ ሆነው ተመርጠዋል።

እንዲያም ሆኖ የተጣማሪ ፓርቲዎቹን አባላት ሙሉ ድምፅ አላገኙም።

በምርጫው ሂደትም 303 አባላት ተቃውመዋል፤ ስድስት የምክር ቤት አባላት ደግሞ ድምፅ አልሰጡም። ከድምፅ አሰጣጡ ሥርዓት በኋላ ወደ ፕሬዝደንቱ መኖሪያ በመሄድ የሹመት ደብዳቤያቸውን ተቀብለዋል።

በዛሬው ዕለት ከጀርመን ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በይፋ የመራኄ መንግሥትነት ሥልጣናቸውን የተቀበሉት ሾልስ ወደ ምክር ቤት በመሄድ ቃለመሃላ ፈጽመዋል።

በመቀጠልም የካቢኔ አባሎቻቸውን በማቅረብ አዲስ ሚኒስትሮቻቸውን በይፋ ሰይመዋል።

ላለፉት 16 ዓመታት የጀርመን መራኂተ መንግሥት የነበሩት አንጌላ ሜርክል የምክር ቤቱ አባል ባለመሆናቸው የአዲሱን መራኄ መንግሥት ምርጫ እና የቃለ መሃላ ሂደት ተመልካቾች በሚቀመጡበት ስፍራ በመሆን ተከታትለዋል።

ላለፉት በርካታ ዓመታት ለሀገራቸው ላበረከቱት አስተዋጽኦም የአዲሱ ምክር ቤት አባላት ከመቀመጫቸው በመነሳት አክብሮታቸውን ለሜርክል ገልጸዋል።

ኦላፍ ሾልስ በይፋ የጀርመን መራኄ መንግሥት መሆናቸውን ተከትሎም ከተለያዩ ሃገራት የደስታ እና አብሮ ለመሥራት ፈቃደኝነት ያካተተ መልእክት እየተላከ ነው።

ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply