ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ ከጫካ ቡና ጋር በመተባበር የሬስቶራንት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ

ሐሙስ መስከረም 12 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ ከጫካ ቡና ኃ.የተ.የግ.ማ. ጋር አዲስ አጋርነት በመፍጠር ለደንበኞቹ ጥራት ያለው የጫካ ቡና ካፌ እና ሬስቶራንት አገልግሎት መጀመሩን በዛሬው ዕለት አስታውቋል።የቻካ ቡና ካፌ እና ሬስቶራንት አገልግሎቱ በአዲስ አበባ ብሄራዊ ቲያትር አካባቢ በሚገኘው ራስ ኦላ ኢነርጂ አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ግቢ ውስጥ ነው በይፉ የተጀመረው።ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያን ወደ አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎቹ ለሚመጡ ደንበኞቹ ኹሉ “የአንድ ቦታ ግብይት አገልግሎትን” ከማቅረብ አኳያ መፍትሔ ለመስጠት የገባውን ቃል ለማጠናከር፤ ይህ ከጫካ ቡና ጋር አብሮ ለመስራት የተደረገው ሥምምነት ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው የኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሽኩሪ ዱሪዲ ተናግረዋል፡፡

ኩባንያው በአሁኑ ወቅት በመላ አገሪቱ የሚገኙ ከ180 በላይ በሥራ ላይ ያሉ የችርቻሮ አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች እንዳሉት የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ በቀጣይም መሠል አገልግሎቶችን በየጣቢያዎቹ ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የጫካ ቡና ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤት ብስራት በላይ በበኩላቸው፤ ሥምምነቱ ጫካ ቡና አገልግሎት መስጫ ሱቆቹን እንዲያሳድግ እንዲሁም፤ በራስ ኦላ ኢነርጂ አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ውስጥም ለደንበኞች ልዩ የቡና ተሞክሮዎችን ጤናማ እና ባህላዊ በሆነ መንገድ ከተዘጋጁ የቁርስ ዝርዝሮች ጋር አጣምሮ በማቅረብ ተደራሽነቱን ለማሳደግ እድል እንደሚሰጠው ገልጸዋል።

ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ፤ በነዳጅ፣ በቅባት እና በሌሎች የፔትሮሊየም ምርቶች አቅርቦት፣ ሥርጭት እና ግብይት ላይ ተሰማርተው ቁልፍ ሚና ከሚጫወቱት ተዋናዮች መካከል አንዱ የሆነው የኦላ ኢነርጂ አካል ሲሆን፤ ኦላ ኢነርጂ በአሁኑ ወቅት በ17 የአፍሪካ አገራት ላይ በመስራት ላይ ይገኛል።

ጫካ ቡና ኃ.የተ.የግ.ማ. በ2016 ጫካ ቡና በሚል ብራንድ የከተማ ካፌ አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ የግል ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ ሲሆን፤ በአጭር ጊዜ ውስጥም ተወዳጅነትን በማግኘቱ በ2009 ኹለተኛውን የቡና መሸጫ ሱቅ በከተማው ማዕከላዊ የንግድ አካባቢ እንዲሁም ኹለት ተጨማሪ ቅርንጫፎችን በ2013 በመጨመር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

The post ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ ከጫካ ቡና ጋር በመተባበር የሬስቶራንት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply