ኦሚክሮን ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ዋነኛው ቫይረስ ሆኗል

በደቡብ ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ክፍለ ግዛት ህይወቱን ያጣ አንድ ሰው አሁን በሃገሪቱ እየተስፋፋ ባለው የኦሚክሮን የኮቪድ-19 ቫይረስ ሳቢያ የሞተ የመጀመሪያው ሰው ሳይሆን አይቀርም ተባለ፡፡

ቴክሳስ ውስጥ የሃሪስ ወረዳ የጤና ባለሥልጣናት እድሜው በ50ዎቹ ውስጥ የሚገኘው ይህ ሰው የኮቪድ-19 ክትባት ያልወሰደና ለአደጋ በሚያጋልጥ የጤንነት ችግር ውስጥ የነበረ መሆኑን ትናንት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ተቋም ባላፈው ሰኞ እንዳስታወቀው ካሉት ተላላፊና ተስፋፊ ቫይረስ ዝርያዎች ውስጥ በፈጣን ተስፋፊነቱ ባሁኑ ወቅት 73 ከመቶውን የያዘው የኦሚክሮን ቫይረስ መሆኑን ገልጿል፡፡

ይህ አሃዝ ከቀደመው ሳምንት በ6 ከመቶ ብልጫ ማሳየቱን የጠቀሰው ተቋም የታህሳስ ወር ሲገባ ገና 1 ከመቶ ብቻ እንደነበር አመልክቷል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ሆስፒታሎች በኮቪድ-19 ህሙማን እየተሞሉ መምጣታቸውም በዘገባው ተገልጿል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply