“ኦሮሙማን አዲስ አበባ ውስጥ እየተከልን ነው ያለነው….” ሽመልስ አብዲሳ! “ቄሮ ተዋግቶ ጣርማ በር ደርሶ የነበረውን ህወሓት አሸንፏል…” የኦሮሚያ ክልል መስተዳድር ሽመልስ አ…

“ኦሮሙማን አዲስ አበባ ውስጥ እየተከልን ነው ያለነው….” ሽመልስ አብዲሳ! “ቄሮ ተዋግቶ ጣርማ በር ደርሶ የነበረውን ህወሓት አሸንፏል…” የኦሮሚያ ክልል መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ከክልሉ ምክር ቤት አባላት ከትላንት በስቲያ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ፣ “ጣርማ በር ደርሶ የነበረውን ህወሓት፣ ቄሮ ተዋግቶ አሸንፏል…..እንኳን የዚህ ድል ባለቤት ሆናችሁ ማለት እፈልጋለሁ ” በማለት አድማጮቻቸውን አስደምመዋል፡፡ “ኦሮሙማ አይጠፋም፣ ገና ያድጋል፤ ያብባል…..ገና ብዙ ፍሬዎችን ያፈራል…..የማይበቅል ነገር አይደለም የተዘራው…..እልፍ የሚያፈራ ነገር ነው የተዘራው…..የኦሮሞ ህዝብ በአለም የሰላም ሎሬት ዶ/ር ዐብይ አህመድ ተመርቶ ከፍ ብሏል….. ይህ ታላቅ መሪ እንኳን ከኦሮሞ ህዝብ አብራክ ተገኘ ማለት እወዳለሁ፤ እንኳን የኦሮሞ ልጅ ሆነ…..የሚጮሁት ይጮሀሉ እንጂ፣ የሚንጫንጩት ይንጫጫሉ እንጂ የህዝባችን ፍላጎት ምንም ማድረግ አይችሉም…..የኦሮሞን ህዝብ ድል በጭራሽ ወደ ኋላ መመለስ አይቻልም…..ኦሮሙማ ኢትዮጵያዊነት ነው…..ኦሮሙማ ክብር ነው…..ኦሮሞነት ከሌላው ጋር መኖር ነው…..እሮሙማ እንደ እሳት የሚያቃጥላቸው ትክክል ነው….. ምክንያቱም ኦሮሙማን ዝቅ አድርገው ማየት አይችሉም…..ኦሮሞን እየዘረፉ መኖር አይችሉም…..ይሄ ትውልድ ይህን ሰርቷል….. ኦሮሙማ ገና ያብባል፣ ገና ያድጋል የሚለውን ለወዳጅም ሆነ ለጠላት ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ…..በዚህ ጉዳይ ላይ የሚያለቅሱትን እንባቸውን የሚጠርጉበትን እንሰጣቸዋለን…..ኦሮሙማን አዲስ አበባ ውስጥ እየተከልን ነው ያለነው….ለዚህ ነው ኦሮሙማና ኦሮሚያ እያበበ ይገኛል የምንለው….. ይህንን ተደራጅተው የሚቃወሙንን ልንታገላቸው ይገባል፣ ይህ የእያንዳንችን ኃላፊነት ነው፡ ” ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply