ኦሮሙማ ከወገብ በላይ አቃፊ፣ ከወገብ በታች አግላይ!!! ነጭ ጅብ ወጣ፣ ጥቁር ጅብ ገባ!!! ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

አብይ አህመድ፣ሽመልስ አብዲሳ፣ መዓዛ አሸናፊ፣ ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንድአርጋቸው፣ ላቀ አያሌው፣ አገኘሁ ተሻገር፣ አሻደሊ ሃሰን፣ተስፋዬ ቤልጂጌ

‹‹ቁርጥምጥም አድርጎ ሰውን ከበላው
ነጭ ጅብ ጥቁር ጅብ ምንድን አሰኘው?››

‹‹ወያኔ ሆነ ኦህዴድ/ ብልጽግና ሰው በላ ከሆነ ሰው በላ ነው። ታላቋ ትግራይ፣ ታላቋ ኦሮሚያ የሚሉ ቅዠቶች፣ እንደ ታላቋ ሶማልያ ቅዠት ካልጋ ሲሉት አመድ የሚያደርጉ እብደቶች ናቸው።›› 1 ነጭ ጅብ ወጥቶ፣ ጥቁር ጅብ ገባ!!! የኦዴፓ ብልፅግና የምርጫ የውክልና ጦርነት በቤኒሻንጉል፣ ወለጋ፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ ወዘተ የኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ  በምርጫም፣በሜንጫም ለማስቀጠል ይንደፋደፋሉ፡፡

  • መዓዛ አሸናፊ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት፣ የኢትዮጵያን የፍትህ ሥርዓት ከወያኔ ወደ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በኦሮሙማ በመተካት የተተኪና ዘረኛ ሥርዓት ዘርግተዋል፡፡ በዚህም መሠረት በኦሮሞ የተያዘ የሥልጣን ስብጥር በሚመለከት፣ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ስልሳ ስድስት በመቶ፣ የፍርድ ቤት ማኔጅመንት ካውንስል ስልሳ በመቶ፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ጉዳዬች  ስልሳ ሰባት በመቶ እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ችሎት ስልሳ ሰባት በመቶ  በኦህዴድ/ ኦዴፓ ብልጽግና ተረኛ ዘረኛ ሹመኞች የፍትህ ሥርዓቱ ተዘርግቷል፡፡ መዓዛ አሸናፊ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔና የፍርድ ቤት ማኔጅመንት ካውንስል የስልጣን ስብጥር ከአስሩ ውስጥ ሰድስቱን ኦሮሞ፣ (መዓዛ አሸናፊ፣ ሰለሞን አረዳ፣ ቦጃ ታደሰ፣ ዘሪሁን ጌታሁን፣ ብርህነመስቀል ወጋሪ፣ ተስፋዬ ንዋይ) ሁለቱ ትግራይ(ተክሊት ይመስል፣ ፉአድ ኪያር) አንድ አማራ (ተናኘ ጥላሁን)፣ አንድ ደቡብ (አሸነፈች አበበ) የሌሎች ክልሎች የፍትህ ሥርዓት የሰው ኃይል ስብጥር የሱማሌ፣ አፍር፣ ቤኒሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪ ወዘተ የህግ አዋቂዎችን አግላይ በመሆኑ ይሄን ተረኛና ዘረኛ የኦሮሙማ አንባገነናዊ ሥርአት በእንጭጩ ለመቅጨት ከወዲሁ መታገል የእኩልነትና የዜግነት ግዴታችሁ ነው እንላለን፡፡ ነጩን ጅብ ወያኔን በትግላችን አስወግደን፣ ለሌላ ጥቁር ጅብ አህዴድ/ ኦዴፓ ብልጽግና መበላት የለብንም፡፡
  • ብርቱካን ሚደቅሳ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ሠብሳቢ የፓርቲዎች የጠቅላላ ጉባዔ የማስረዘም ለኦዴፓ ብልጽግና የምርጫ መስፈርቶች ያላሞላውን ለማስተካከል የተደረገ ሸፍጥ ታሪክና ህዝብ አይረሳውም
  • ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ የኦህዴድ የኦሮሚያ የፖለቲካ ሥልጣን ውክልና አርባ በመቶ እንዲሆን አድርገው እየሰሩ መሆኑንና የቤኒሻንጉል የመተከልን ዲሞግራፊ በኦሮሞ ስለመቆጣጠራቸውና ስለቀጣይም እቅዶች አሲረዋል፡፡

*በመተከሉ የግፍ ሥራ ብልጽግና እና ዶ/ር ዐቢይ በሚሳሱለት እና ጁንታዬ እያሉ በሚያቆላምጡት ሕወሃት ሊያሳብቧቸው የማይችሏቸው የገዛ የግል ንብረታቸው የሆኑ ክፋቶች ማሳያዎች እነሆ (የሕወሃት ድርሻ እንደተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው) • ዶ/ር ዐቢይ በመተከል ጉብኝንት ማንንም ሕጻን የማይሸውድ ቀሺም ግን እጅግ አደገኛ የጂኖሳይድ ቅስቀሳ ድራማ መመድረካቸው። ከጨፍጫፊው ጎን ተቀምጠው፣ ጨፍጫፊው አስቀድሞ የተዘጋጀበትን የዘር ፍጅት ቀስቃሽ መልእክትና አሳፋሪ ቅንብር በቴሌቪዥን እንዲተላለፍ ማድረጋቸው፣ በስብሰባው እውነተኛ የተጠቂ ወገን ያልተሳተፈ መሆኑ አስተዛዛቢና አሳፋሪ ከሀገር መሪ የማይጠበቅ ተግባር ነው። በስብሰባውም ስለተጠቂዎች የተጠቀሙት ቋንቋ እጅግ አሳሳች ነው። ተጠቂዎች ሁሉ ከሌላ ክልል የመጡ በማስመሰል ተናግረዋል። አማራ፣ አገውና ሺናሻ የመተከል ጎጃም ባለርስቶች ናቸው።

  • የዶ/ ዐቢይ አህመድን ጉብኝት ተከትሎ አጅግ አስከፊ ጭፍጨፋ ሲካሄድ እሳቸው ያስተላለፉት አቃላይና ፌዘኛ መልእክት። እንደ መሪ ሀገራዊ ሃዘን እንዲታወጅ ማድረግ፣ ተጓዳኝም የእርዳታ ጥሪ ማስተላለፍ ሲገባቸው። የችግሩ ሰለባዎች በግሬደር ባንድ ጉድጓድ እንዲቀበሩ መደረጉ። ይህንን በሕወሃት ማሳበብ ይቻላል? ችግሩን ለመፍታት ብለው የመደቧቸው በደቡብ ዘረፋና ጭፍጨፋ ሲመሩ የነበሩትን ተስፋዬ ቤልጂጌ እና የቤንሻንጉሉን አንጋፋ አስጨፍጫፊ አሻድሊ ሃሰን ዓይነቶቹን መሆኑ በመተከልም ሆነ በወለጋ የሚደረገው ጭፍጨፋ ሲካሄድ ብልጽግና በሚቆጣጠራቸው ሚድያዎች እነዚህን ዜናዎች የሚደፍቅ የተቀነባበረ የማስቀየሻ የሚድያ ዘመቻ ማካሄዱ። ይሄም በሐሰት ተያዙ፣ ተደመሰሱ የሚላቸውን የሸኔ ታጋዮች ዜና ይጨምራል። ተላከ ወይም ተመደበ የሚባለው መከላከያ፣ ኮማንድ ፖስት ወዘተ ተሻለ ሲባል ችግር ከደረሰ በኋላ የሚደርስና የቀብር አስፈጻሚ ሥራ እንዲሠራ የተደረገ መሆኑ ችግሩ እንዳይፈታ፣ ሕዝቡ ራሱን የሚከላከልበትን መሣሪያ እንዳይታጠቅም ሆነ የታጠቀ ልዩ ኃይል ከአማራ ክልል ገብቶ እንዳያረጋጋ እንቅፋት ሆነው መቆየታቸው።
  • ‹‹ተስፋዬ ቤልጂጌ የተባለ የሕወሃት ዘመን ወንጀለኛ፣ በደቡብ ቤተክርስትያንን ሲያዋርድ፣ የቤተክርስትያን ንብረት ሲዘርፍ፣ የተዋሕዶ ፣ምእመናንን ሲያሳድድ የነበረ የኢህአዴግ/የብልጽግና ባለሥልጣን፣ የመተከልን ጭፍጨፋ ከአሻድሊ ጋር ሆኖ መፍትሔ እንዲሰጥ በዶ/ር ዐቢይ ተሹሟል። ዶ/ር ዐቢይ በጎጃም ተወላጆች ቁስል ላይ የጋለ ብረት መሰካትን ለምን እንደመረጡ እሳቸው ብቻ ናቸው የሚያውቁት። ዛሬም እለት እለት በመተከል መንደሮችና ጫካዎች ኢትዮጵያውያን ይጨፈጨፋሉ። የንጹሐኑ፣ በግሬደር የተቀብሩት፣ ከእልቂት ተርፈው በዱር በገደሉ የተሰደዱት፣ በየከተማው ታዛ የወደቁት የደሃ ገበሬ ቤተሰቦች ደም በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እጅ ነው።* ትህነግን የተፋረደ የንጹሐን ደም እሳቸውንም እንደሚፋረዳቸው መጽሐፍ ቅዱስና የኢትዮጵያ ታሪክ ያስተምሩናል። መንገዳቸውን በጊዜ ቢያርሙ ለሳቸውም ለኢትዮጵያም ይበጃል።›› (ተስፋዬ ቤልጂጌ – አሁንገና ዓለማየሁ JANUARY 12, 2021)
  • / ግርማ አመንቴ (የጎጃም ኦሮሞ) በኦሮሚያ ከፍተኛ ባልሥልጣንነት በመተከል የሚያሳልጠው የኦነጉማ ሥራ
  • አሻድሊ ሃሳንን ጨምሮ የመተከል የሕወሃት ዘመን ጭፍጨፋ አሳላጮች በብልጽግና ዘመን ከበፊቱ እጅግ የከፋ ጭፍጨፋና ማፈናቀልን መርተው እየተሾሙና እየተሽሞነሙኑ መሆናቸው

 

የአማራ ክልላዊ መንግሥት ባንዲራውን ዝቅ ሲያደርግ፣ ይከተላል ጎረቤት

ላቀ አያሌው፣ የብአዴን/አዴፓ ብልፅግና ፓርቲ አመራር በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ አማራዎች በህይወት የመኖር መብት ባለመጠበቁ በአማራው ላይ  በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጉሙዝ ንቅናቄ አሸባሪ ታጣቂዎችና በወለጋ የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር   የዘር ማፅዳት ጭፍጨፋ ተከናውኖል፡፡ የማንኛው ሰው በህይወት የመኖር መብቶች ሳይከበሩ ስድስተኛውን ዙር ምርጫ ማድረግ ለሌላ ዙር የዘር ጭፍጨፋ ይዳርጋል፡፡  ምርጫው ሌላ ግጭቶች ያስነሳል ትንሽ ይዘግይ፡፡ በአማራ ህዝብ ላይ የተደረገውን የዘር ጭፍጨፋ የአማራ ክልል ባንዲራውን ዝቅ ሲያደርግ ይከተላል ጎረቤት  እንላለን፡፡

ላቀ አያሌው፣ ‹‹ተላላኪ ነበርን አሁንም ቀጥሎል!!!››…‹‹የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም!!!›› ብለው በድፍረት እቅጮን ከገለፁልን በኃላ በኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ አሰራር ተከትሎ፣ የተረኛና የዘረኛ ስሜት ተላቆ  ትግሉን እስካልመራ ድረስ በአንድ ሰው አንባገነንነት ማስቀጠል ስለሚሆን ከአዴፓና ከብልፅግና ፓርቲ መውጣትና ራስን ማግለል ለውጥ ያመጣል፣ ቆራጥ አመራር የሚሰጡ ወጣት የአዴፓ አመራሮች መተካት አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ ካለዛ አበው ሲተርቱ ‹‹በሬ ከአራጁ ጋር ይውላል!!!››እንዳሉት ኦህዴድ ብልፅግና ለወያኔ ሹማምንት የዘነበው ቦንብ፣ ለብአዴን ሹማምን አያካፋም ብለው መጠበቅ ቂልነት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እስካልተገነባና የአንድ ሰው አንባገነናዊ አገዛዝ እስከቀጠለ ድረስ የፖለቲካ ሥልጣን ቀጣይ ሽኩቻ በኦህዴድና ብአዴን መሆኑ አይቀሬ ነው እንላለን፡፡ ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንድአርጋቸውና ፣ አገኘሁ ተሸገር በሃሳብና ዴሞክራሲያዊ ልዕልና ምጥቀት ‹አስሬ ታግሳችሁ አንዴ ቁረጡ!!!›

ኦዴፓ ብልጽግና የሃገሪቱን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ዘርፎች አንድ በአንድ በወያኔ እግር እየተተካ በትረ ሥልጣኑን በክልሎችና በፌዴራል መንግስት እየተቆጣጠረና እየዘረጋ መሆኑን አይቷ እንዳላየ፣ ፈርቷ እንደደፈረ በማስመሰል መኖር የኃላ ኃላ አሟሟቴን አሳምርልኝ ያስብላልና  ከአሁኑ የኦሮሙማን ተራኛነትንና ዘረኛነትን በህብረት ከሁሉም ክልሎች (የሱማሌ፣ አፋር፣ ሀረሪ፣ ደቡብ፣ ሲዳማ፣ ጋምቤላ፣ ቢኒሻንጉል) ጋር ሆኖ መታገል አንገብራቢ ጥያቄ ነው፡፡  የፌዴራል መንግሥታዊ መዋቅሮች ሥልጣን፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ ኃይል ጀነራል መኮንኖች፣ የውጭ ሃገራት አንባሳደሮች፣ ወዘተ ስልጣን የብሄር ተዋፆኦ በግልፅ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መፍታት ተረኛነትንና ዘረኛነትን የመከላከያ አንዱ ዘዴ ነው እንላለን፡፡

ገድለ ላቀ አያሌው፣ ሠላማዊ ሠልፍ የመሰብሰብ መብት የለንም፣ ሃሳባችንን በማህበራዊ ሚዲያ መግለፅ ታግደናል፣  ጀኖሳይድ (የዘር ማፅዳት) አትበሉ ግጭት ነው በሉ፣ ወዘተ እየተባሉ መኖር ከአሁን በኃላ በውሽት ስንት አመት ለመኖር ነው!!! እንደ አቦይ ስብሃት ነጋ ዕድሜ ቢረዝም የማታ እንጀራ ከልጅ ልጆች ጋር በእስር ቤት ከተበላና የታሪክ አተላ ሆኖ ከመኖርና የዛ የክፍ ልጅ እየተባሉ ከመታወስ፣ ከወዲሁ ከፖለቲካ ጭንብል አውልቆ መሰናበት ቢያንስ ለልጅ ልጆቻችሁ ሠላማዊ ህይወት ታተርፋላችሁ እንላለን፡፡

ለማጠቃለል ላቀ አያሌው እንደደመደሙት በሃገሪቱ ዴሞክራሲያዊ መብቶች፣ የአመለካከት እና ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብት በነጠፈበት፣ የፕሬስ ነፃነት በሌለበት የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት በተነፈገበት፣ የመደራጀት መብት በታቀበበት፣ የመዘዋወር ነፃነት በሌለበት፣ የዜግነት መብቶች መጠበቅ በተሳነበት ወዘተ በተግባር እስኪተገበሩ  ድረስ ስድስተኛ ዙር ምርጫ ይቆየንና በፊት መገደያችን ህገወጥ የጦር መሣሪያዎች ጠመንጃ፣ ሽጉጥና ቦንብ፣ እና መታረጃችን ገጀራ፣ ሜንጫ፣ ጦሩ ተሰብስቦ ምርጫ ቦርድ ሙዚየም ውስጥ ይቀመጥ እንላለን፡፡

 

ኦዴፓ ብልጽግና ከህወሓት ኢህአዴግ አወዳደቅ ይማር!!!

ስብዓዊ እርዳታ ለትግራይ ህዝብ ይቅረብ!!!

ጦርነት መቼም የትም አይደገም!!! በጦርነት አሸናፊም ተሸናፊም የለ!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

 

ጀነዋሪ 22 ቀን 2021እኤአ ተጻፈ ……መሸ ደህና ደሩ!!!

Leave a Reply