
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ውስጥ ከ400 በላይ የአማራ ተወላጆች ላይ በተፈጸመው ጭፍጨፋ ላይ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ገለልተኛ የሆነ ምርመራ እንዲያከናውኑ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ። የመብት ተቆርቋሪው ድርጅት በዛሬው ዕለት ሐምሌ 14/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በምዕራብ ወለጋ፣ ጊምቢ ወረዳ፣ ቶሌ ቀበሌ ሰኔ 11/2014 ዓ.ም. በተፈጸመው ጭፍጨፋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን እንዲሁም በርካቶች መቁሰላቸውን ገልጿል።
Source: Link to the Post