ኦቪድ ሪል እስቴት 55ሺህ ቤቶች ልገነባ ነው አለ።

በቤት ልማት ላይ የተሰማራው ኦቪድ ሪል እስቴት በመዲናው የሚገነባቸው ቤቶች ይፋ አድርጓል።

የቤቶቹን ግንባታ ይፋ ባደረገበት ሰአት1ሺህ 500 ሰዎች ተመዝገበዋል ሲልም ነው ያስታወቀው።

በመጀመርያ ቀን ለተመዘገቡ ቤት ፈላጊዎች 40 በመቶ ቅናሽ ማድረጉንም ገልጿል።

እንደዚሁም በቅድምያ ለተመዘገቡ 100 ሰዎች የቤት ፈርኒቸር እንደሚያቀርብ ቃል ገብቷል።

በመጀመርያ ዙር ቤቶቹን የሚገነቡት በፓስተር እና እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ እንደሆነ ነው የተገለጸው።

ዜጎች ብዙ መልፋት ሳይጠበቅባቸው የቤት ባለቤት ማድረግ የድርጅቱ ዋና አላማ መሆኑን ነው የተገለጸው።

እንደዚሁም በኢትዮጵያ ያለው የቤት ችግር በማቃለል የዜጎችን ችግር መፍታት ነው ብሏል።

324 ቤቶች የሚገነቡት በፓስተር ሳይት ሲሆን በርካታ አገልግሎቶች ዘመናዊ ቤቶች ናቸው ተብሏል።

1740 ቤቶች ያሉት ደግሞ በተለምዶ ጥይት ቤት ተብሎ በሚጠራው ቦታ ወይም ከቤተ መንግስት ወረድ ብሎ ያለው ቦታ ነው።

ኦቪድ ሪል እስቴት ከሰሞኑ ከአየር መንገድ ጋር 5ሺህ ቤቶች ለመገንባት ስምምነት ማድረጉ ይታወሳል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply