ኦነግ-ሸኔ በምስራቅ ሸዋ በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ ጥቃት አደረሰ ባህርዳር:- ሚያዚያ 11/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በመንግሥት ባለሥልጣናት እንደሚደገፍ የሚነገርለት…

ኦነግ-ሸኔ በምስራቅ ሸዋ በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ ጥቃት አደረሰ ባህርዳር:- ሚያዚያ 11/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በመንግሥት ባለሥልጣናት እንደሚደገፍ የሚነገርለት አሸባሪው ኦነግ-ሸኔ ከወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ ተፈናቅለው በኦሮሚያ መስተዳድር ምስራቅ ሸዋ ዞን ወለንጭቲ በሚገኙ ተፈናቃይ አማሮች ላይ ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ጥቃት አድሷል። አሸባሪ በድኑ “ከወለጋም ያፈናቀልናችሁ እኛ ነን፤ እዚህም አትኖሩም። ከአማራ ውጭ የሆናችሁ ካላችሁ አንነካችሁም። ተረጋጉ። አማራን ግን እንገድላለን” በማለት ተፈናቅዮች በተጠለሉበት ቻይና ካምፕ ላይ ተኩስ መክፈቱን የዓይን እማኞች ተናግረዋል። ገዳዮች ወደ መጠለያ ጣቢያው ሲገቡ ከጠመንጃ በተጨማሪ በነፍስ ወከፍ ቆንጨራዎችን መያዛቸውንም የዓይን ምስክሮች ገልፀዋል። ከተኩሱ በኋላ የቻይና ካምፕ የፋብሪካ ማሽኖችን ዘርፈው መሄዳቸውንም ጠቁመዋል። ቦሌ ኑራ በተባለ ሌላ የአካባቢው መንደር ላይም ተመሳሳይ ተኩስ ተከፍቷል። ጥቃቱ የተከፈተባቸው ተፈናቃዮች በአማራዊ ማንነታቸው ከወለጋና ምዕራብ ሸዋ ከወራት በፊት ተፈናቅለው አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፣ ተቀባይ በማጣት ከአዲስ አበባ ደብረ ብርሃን፣ ከደብረ ብርሃነ እንደገና አዲስ አበባ እና ከዚያም አርሲ (ፈጠጋር) ሲንከራተቱ ቆይተዋል። በተለይም ከአዲስ አበባ መንግሥት ኃይል መባረራቸው ይታወሳል። #ስንታየሁ ቸኮል ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply