ኦነግ ሸኔ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሐሮ አዲስ ዓለም ቀበሌን በግራ እና በቀኝ ከቧል ተባለ! የአማራ ሚዲያ ማእከል መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሁንም ኦነግ ሸ…

ኦነግ ሸኔ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሐሮ አዲስ ዓለም ቀበሌን በግራ እና በቀኝ ከቧል ተባለ! የአማራ ሚዲያ ማእከል መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሁንም ኦነግ ሸኔ በምስራቅ ወለጋ ዞን በኪረሙ ወረዳ የሐሮ አዲስ አለም ቀበሌን ለመውረር በግራና በቀኝ ከቧል ሲሉ ኗሪዎች ለአጉልዞ ጥያቄ ገለጸዋል። በዚህም የተነሳ በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን በአሙሩ ወረዳ በአጋምሳ ቀበሌ ስር በሚገኙት የኦነግ ሸኔ ካምፕ ውስጥ አሰሳ በማድረግ ከበባ ከፈጸሙባቸው አከባቢዎች መካከል፦ በአጋምሳ ቀበሌ፥ ዋዩ ሉቅማ ጆጅ እና ምግር የሚባሉ ቦታዎች በስፋት የሚገኙባቸው ሲሆኑ፥ በጊዳ አያና ወረዳ፥ ጃንግር ቀበሌ ጎበቶ ቀበሌ ኮኔጅ በተባለው ቦታዎችም በስፋት እየተንቀሳቀሰ ነው። ስለሆነም እነዚህ በሁለቱ ዞኖችና ወረዳዎች መካከል የሚገኙ የሐሮ አዲስ አለም ከተማ የአማራ ኗሪዎች በሸኔ እንቅስቃሴ እና ግስጋሴ ፍጹም የማንደናገጥ ህዝቦች ቢሆንም መንግስት ግን የህክምና ቁሳቁስ እንድያቀርብልን ሲሉ ተማፅነዋል። ከኦነግ ሸኔ ጋር በነበረው ፍልሚያ በርካታ ቁስለኞች በህክምና እጦት ህይወታቸውን አጥተዋል። በዚህም መሠረት ወደቡሬ ለማለፍ እንኳን የአጋምሳን ቀበሌ በከፍተኛ ቁጥር ባለው ሐይልና ሎጀስቲክ በሸኔ ቢዘጋም ከላይ በተጠቀሱት የሸኔ ካምፕ ላይ እርምጃ እንዲወስድላቸው በአፅንኦት ገልፀዋል። ምንጭ አሻራ ሚዲያ

Source: Link to the Post

Leave a Reply