ኦነግ ‹‹ነፍጠኛ ከኦሮሚያ ይውጣ!!!››‹‹ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር!!!›› በኢትዮጵያ የከተማ ንዋሪዎች ከሻሸመኔ ህዝብ ጭፍጨፋና ቃጠሎ ተማሩ ሰዓቱ ደረሰ!!! ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

በ1983ዓ/ም አራጆቹ ወያኔው መለስ ዜናዊ፣ የሻብያ ኢሳያስ አፈወርቂና የኦነግ ሌንጮ ለታ በአሜሪካው ህእር ማን ኮን
አንጋሽነት ሥልጣን ተቆጣጠሩ፣ በመለስና ኢሳያስ የበድሜ ጦርነት መቶ ሽህ ወታደሮች ህይወታቸው ተቀጠፈ፡፡
በ2010ዓ/ም በኢሳያስ አፈወርቂና በዶክተር ዐባይ አህመድ እርቅ ወረደ፣ በዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤልና አብይ አህመድ
ጦርነት ተከፈተ እስከ ሰባ ሽህ ወታደሮች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በሦስተኛው ፎቶ ኦነግን ከአስመራ ከነትጥቁ ያስገቡት ለማ
መገርሳ፣ ወርቅነህ ገበየሁ፣ የኦነግ ዳውድ ኢብሳን በማስገባት በአማራ ዎች ላይ የዘር ፍጅት ለሦስት አመታት ተካሄደ፡፡ ለዚህ የዘር
ፍጅት ተጠያቂዎች ኢሳያስ አፈወርቂ፣ አብይ አህመድ፣ ለማ መገርሳ፣ ወርቅነህ ገበየሁ፣ ዳውድ ኢብሳ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣
ዋነኛዎቹ አራጅ ጋኔሎች በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት መጠየቃቸው ሰዓቱ ደርሶል፡፡
የዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ለፍርድ መቅረባቸው የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ የዐብይ አህመድና ኢሣያስ አፈወርቂ
ጭፍራና ቡችላ ዶክተር ደብረፂዮንና የወያኔ ካቢኔ፣ የሱማሌው አብዲ ኢሌና የሱማሌ ካቢኔ፣ እስከ ቤኒሻንጉሉ አሻድሊ ሃሰን
በዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ በመሆን ለፍርድ ይቀርባሉ፡፡
የወያኔ ኢህአዴግ ጣምራ ድርጅቶች የነበሩ የህወሓት፣ የብአዴን፣ ኦህዴድና፣ የደኢህዴህ፣ ወንጀለኛና መሪዎችና ካድሬዎች
እንዲሁም የኦዴፓ ብልፅግና፣ አዴፓ ብልጽግና፣ የደኢህዴህ ብልጽግና ወንጀለኛ መሪዎችና ካድሬዎች በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለፍርድ
መቅረባቸው አይቀርም፡፡
የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት አቃቢ ህግ ክስ የሚመሠርትባቸው ግለሰቦች በፈፀሙት ወንጀሎች ዝርዝር ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ
ወንጀል በአንቀጽ አምስት ደንብ መሰረት የዘር ማፅዳት(አንቀፅ ስድስት)፣ የስብዓዊ መብቶች ጥሰት ወንጀል (አንቀፅ ሰባት)፣
የጦር ወንጀል (አንቀፅ ስምንት)፣ እንዲሁም የወረራ ወንጀል (አንቀጽ ስምንትንኡስ አንፅ) ክሶች ናቸው፡፡
The Court's subject-matter jurisdiction means the crimes for which individuals can be
prosecuted. Individuals can only be prosecuted for crimes that are listed in the Statute. The
primary crimes are listed in article 5 of the Statute and defined in later
articles: genocide (defined in article 6), crimes against humanity (defined in article 7), war
crimes (defined in article 8), and crimes of aggression (defined in article 8 bis) (which is not yet
within the jurisdiction of the Court; see below). [80]  In addition, article 70 defines offences against
the administration of justice, which is a fifth category of crime for which individuals can be
prosecuted.
የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት አቃቢ ህግ የአስራ ሶስት አገሮች መሪዎች ህግ ፊት ለማቅረብ የክስ ቻርጁ በአፍጋኒስታ፣ ብሩንዲ፣
በመካከለኛው አፍሪካ ሪፓብሊክ፣ ኮትዲቮር፣ሱዳን ዳርፉር፣ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ፣ ጆርጅያ፣ ኬንያ፣ ሊቢያ፣ ማሊ፣
ኡጋንዳ፣ ባንግላዲሽ ሚያንመር መርመራ አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም የአቃቢ ህግ የመጀመሪ ደረጃ የምርመራ ሁኔታ በኮሎንቢያ፣
ጊኒ፣ ናይጀሪያ፣ ፓሊስቲን፣ ፌሊፒንስ፣ ዩክሬን፣ ቦሊቪያና ቬኑዙላ አድርገዋል፡፡
To date, the Prosecutor has opened investigations in thirteen situations: Afghanistan; Burundi;
two in the Central African Republic; Côte d'Ivoire; Darfur, Sudan; the Democratic Republic of the
Congo; Georgia; Kenya; Libya; Mali; Uganda; and Bangladesh/Myanmar. [173]  Additionally, the

Office of the Prosecutor is conducting preliminary examinations in nine situations: Colombia;
Guinea; Nigeria; Palestine; the Philippines; Ukraine; Bolivia; and two in Venezuela. [174]
በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች ውስጥ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው
የአካባቢው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ገለፁ።
በዞኑ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ41 ሺህ በላይ እንደሆኑ ለቢቢሲ ገልጸዋል።በግጭቱ ምን ያህል ሰዎች ሕይወታቸውን
እንዳጡ የተጠየቁት ኃላፊው "የሞቱ ሰዎች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ የሚያጣራ ቡድን አዋቅረን መረጃ እየተሰበሰበ ነው" ብለዋል።
እስካሁን ድረስ እጃቸው ላይ የደረሰው መረጃ 41 ሺህ 625 ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የሚያሳይ መሆኑን የገልጹት አቶ ታደሰ፤ ነገር ግን ወደ
ዘመድ አዝማድ እና ሌላ አካባቢ የሸሹ ስለሚኖሩ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊሆን ይችላል ሲሉ ይናገራሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ ግጭቱ የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ውስጥ የምትገኘዋ ጅሌ ድሙጋ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ጀማል ሐሰን በተፈጠረው ችግር
ሳቢያ በወረዳቸው 40ሺህ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "እስካሁን እጃችን በደረሰው መረጃ መሰረት 67
ሰዎች መሞታቸውን፣ 114 መቁሰላቸውን እና በወረዳው ስምንት ቀበሌዎች 815 ቤቶች መቃጠላቸውን ለማወቅ ችለናል" በግጭቱ
የተፈናቀሉት ሰዎች ትምህርት ቤቶች መስጂዶች እና በተለያዩ ቦታዎች ተበተትነው እንደሚገኙ አቶ ጀማል ይናገራሉ። የሰሜን ሸዋ ዞን
አስተዳዳሪውአቶ ታደሰ በበኩላቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ደብረብርሃን፣ አጣዬ፣ ኤፍራታ፣ ሸዋ ሮቢት ገንደ ውሃ፣ መሀል ሜዳ እና የተለያዩ
ቦታዎች እንደሚገኙ ተናግረዋል። (1)
በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ ማክሰኞ መጋቢት 21/2013 ዓ.ም በዞኑ ውስጥ በሚገኘው በቦኔ ቀበሌ ውስጥ በሚገኙ
ሰዎች ላይ "አሰቃቂና ዘግናኝ" መፈፀሙን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስታውቋል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ረቡዕ ምሽት ላይ ይፋ እንዳደረገው በምዕራብ ወለጋ ውስጥ በሚገኘው በዚህ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት
የተገደሉት ሰዎች 28 መሆናቸውንና ጉዳት የደረሰባቸው 12 መሆኑን ገልጿል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው እነዚህ የቦኔ ቀበሌ ነዋሪዎች
ከእነዚህም በተጨማሪ በአካባቢው ከብቶቻቸውን በመያዝ ለግጦሽ በአቅራብያ ወደ ሚገኝ ቀበሌ ይዘው ሄደው የነበሩ 15 ታዳጊዎችም
በታጣቂዎች መገደላቸውን ገልፀዋል። ሁለቱም ግለሰቦች ማክሰኞ ምሽት የተከሰተውን ለቢቢሲ ሲያስረዱ፣ ታጣቂዎቹ ግለሰቦቹን ከየቤቱ
በማውጣት አንድ ቦታ በመሰብሰብ በጥይት መግደላቸውን ገልጸዋል። ከጥቂት ወራት በፊት በተመሳሳይ በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ
በሚገኝ ሌላ ስፍራ ላይ ታጣቂዎች ነዋሪውን በአንድ ቦታ ላይ በመሰብሰብ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰዎችን መገደላቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የተፈጸመውን ግድያ በተመለከተ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው "በምዕራብ ወለጋ
በነዋሪዎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት በአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ አለመሻሻሉንና ይልቁንም ወደ አዋሳኝ አካባቢዎች እየተስፋፋና ተያያዥ
የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እያስከተለ መሄዱን ያሳያል" ብሏል።ወደ ሰላሳ ለሚደርሱ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን ጥቃት የተፈጸመው
ኦነግ-ሸኔ በተባለው ቡድን እንደሆነ የክልሉ መንግሥትና ከጥቃቱ የተረፉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ኦነግ-ሸኔ የተባለው ቡድን ከኦሮሞ ነጻነት
ግንባር አፈንግጦ የወጣ መሆኑ የሚነገር ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ አካባቢዎች በተደጋጋሚ በሰላማዊ
ሰዎች ላይ በመፈጸም ስሙ ይተቀሳል። በተጨማሪም ቡድኑ የጸጥታ አካላትን፣ የአካባቢ አስተዳዳሪዎችንና የመንግሥት ሠራተኞችን ኢላማ
በማድረግ ግድያዎችን መፈጸሙ በተደጋጋሚ ተዘግቧል። ቡድኑ በሚፈጽመው ጥቃት የቀበሌና የክልል አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ንጹሃን
ዜጎች መገደላቸውን ያመለከተው የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ረቡዕ እለት ባወጣው መግለጫ፤ በጥቃቶቹ የግልና የመንግሥት ንብረቶች
መውደማቸውንም ገልጿል። የታጣቂ ቡድኑ እንቅስቃሴ በተለይ በምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች እጠነከረ በመጣበት ጊዜ የፌደራልና
የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ተከታታይ እርምጃዎችና ዘመቻ ማካሄዳቸው ይታወሳል። በዚህም መንግሥት ታጣቂ ቡድኑን ከአካባቢው
ለማስወገድ በተለያዩ ጊዜያት በወሰዳቸው እርምጃዎች በርካታ አባላቱን መግደሉንና መማረኩን ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል። የኦሮሚያ
ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሉት ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የጸጥታ አካላት በኦነግ-ሸኔ ላይ በተወሰዱት እርምጃ 1947 አባላቱ ሲገደሉ
489ቱ ደግሞ መማረካቸውን ተናግረዋል። ቡድኑ በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የሚፈጽመው ጥቃት በተለይ በዚህ ዓመት እተደጋገመና
የሚገደሉ ሰዎች ቁጥርም እየበረከተ መጥቷል። (2)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ክልል በምእራብ ወለጋ ዞን በንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት
አውግዘዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በኦሮሚያ ክልል በምእራብ ወለጋ ዞን በንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት እናወግዛለን፤
የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን ለሟች ቤተሰቦችና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እንገልጻለን” ብለዋል፡፡” ጠላቶቻችን በውስጥና በውጭ
ተደራጅተው ንጹሀን ዜጎቻችንን በመግደል የጀመርነውን ጉዞ ለማሸማቀቅ እና ከመንገዳችን ለማስወጣት ጥረት እያደረጉ ነው ያሉት
ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሥዋዕትነት እየከፈልንም ቢሆን የኢትዮጵያን አንድነት አጠናክረን ጉዟችንን እንቀጥላለን ብለዋል።በሁሉም
ቦታ በደርሰው ጥቃት አጸፋ እርምጃ በክልልና በፈዴራል መንግሥት ቅንጅት እየተወሰደ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መላው
የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ጥፋት ኃይሎች ወጥመድ ላለመውደቅ በማስተዋል እየተጓዘ፤ በእንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ከመንግሥት ጋር
ተባብሮ ጥፋተኞችን ወደ ሕግ ለማቅረብ እና እንደዚህ ዓይነት ግድያዎች ፈጽመው እንዲቆሙ በትብብር ልንሠራ ይገባልም ብለዋል።
“ኢትዮጵያ በመሥዋዕትነት የቆመች፤ በመሥዋዕትነት የምትቀጥል ሀገር ናት። በትብብርና በአንድነት መንፈስ የኢትዮጵያን ጠላቶች
ደግመው እንዳይነሡ አድርገን ማጥፋት አለብን” ሲሉም ነው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የገለፁት። (3)
የኦሮሞ ህዝብ በኦነግ ስብዓዊ ጋሻነት (Human shield) ተይዞል፣ የኦሮሞ ክልል የጦር አበጋዞች የተማሩ የኦሮሞ ልጆች ኦህዴድ
በመሆናቸው ምክንያት ከሰባት መቶ በላይ የመንግሥት ሠራተኞች ተገለዋል ከሽህ በላይ ሰዎች በፖለቲካ አመለካከታቸው በኦነግ
ሸማቂዎች ቆስለዋል፡፡ በኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ አማራዎች ታርደዋል ብዙዎቹን ያዳናቸው የኦሮሞ ህዝብ ነው፡፡ ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ
እስከዛሬ የኦሮሞ ክልል የጦር አበጋዞች የትግራይ ክልል የጦር አበጋዞች ተክተው መንበረ ሥልጣኑን በመቆጣጠር ፖለቲካውን፣
ኢኮኖሚውን፣ ወታደራዊውንና የደህንነቱን ዘርፎች ተቆጣጥረዋል፡፡ ባንኩም፣ ታንኩም፣ መሬቱም፣ ጦሩም ኬኛ ሆኖል፡፡

‹‹በአንጻሩ አገሪቷ ወሳኝ የተባለውን ምርጫ ለማካሄድ ሽር ጉድ እያለች ነው። ምርጫው በራሱ ይዟቸው የመጣው መዘዝ እንዲሁ
የአገሪቷን መከራ የማያልፍ ቀን አስመስሎታል። አገሪቱ ይህን ወሳኝ ምርጫ ማካሄድ አለባት ብለው ከሚያምኑት አንዱ ብሆንም
ተያይዘው የመጡት አደጋዎች እንቅልፍ ከነሷቸው ኢትዮጵያዊያንም ራሴን እመደባለሁ። የምርጫው መዘዞች በጥቂቱ፤
 ወሳኝ የሆኑ የኦሮሞ ፖርቲዎች ከወዲሁ በሰበብ አስባብ እና በተፈጠሩ መሰናክሎች ከምርጫው ሂደት እራሳቸውን
ማግለላቸው ሰፊ ቁጥር ያለው የኦሮሞ ሕዝብ አማራጭ እንዳያገኝ ከማድረጉም ባሻገር የክልሉን ሰላም ወደ ከፋ አግጣጫ
ሊያመራው ይችላል፣
 የተወሰኑ ክልሎች ውስጥ የሚታየው የሰላም መታጣት፣ የርስ በርስ ግጭት፣ የውስጥ ድንበር ውዝግብ፣ የታጣቂ ሃይሎች
መጠናከር እና እየጨመረ የመጣው የውስጥ መፈናቀል በአገሪቱ በርካታ ቦታዎች ምርጫ ለማካሄድ የማያስችሉ
ሁኔታዎችን ከወዲሁ እየፈጠረ ይመጣል፣
 ተቃዋሚዎች ተንቀሳቅሰው የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ የሚችሉባቸው የአገሪቷ ክፍሎች እየጠበቡና የዜጎችም
የመንቀሳቀስ ነጻነት በመሀል የአገሪቱ ክፍል እየተወሰነ መጥቷል፣
 በክልሎች መካከል ያለው ውጥረት እየከረረ እና አልፎ አልፎም ወደ ግጭት ማምራቱ እራሱ ገዢው ፖርቲ የፖለቲካ ነውጥና
የሥልጣን ትንቅንቅ ወስጥም የገባ አስመስሎታል፣
የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አስተዳደር ከላይ የተዘረዘሩትን አደጋዎች አንድም በተናጠል እያየ አለያም አደጋዎቹን አኮስሶ እየገመተ
ወይም በማን አለብኝነት ስሜት ተሰቅፍ ወይም በተስፋ መቁረጥ ሊሆን ይችላል አደጋዎችን የሚመጥን ምላሽ ሲሰጥ አይታይም።
በአንዳንዱ ሁኔታዎች እንደውም በተቃራኒው አደጋዎቹን የሚያባብሱ ሥራዎች በመንግሥት አካላት ሲፈጸም ይስተዋላል። አደጋዎቹን
አቅላችሁ ለማየታችሁ አንዱ ማሳያ የኦነግ ሽኔ ታጣቂ ቡድን ከወለጋ ተነስቶ የአገሪቷ እምብርት ላይ በደረሰበት እና ኢትዮጵያ በዚህ
ሁሉ ቀውስ እና ውጥንቅጥ ውስጥ በወደቀችበት በዚህ ወቅት ካድሬዎችዎ የዕርሶን የሦስት አመት ሲመተ በዓል ለማክበር ሽር ጉዲ
ሲሉ መታየታቸው ነው። አዎ አገሪቷ የገባችበት አጣብቂኝ እና ያንጃበቡባት አደጋዎች ለእርሶ ለጠቅላዩም ሆነ ለተከታይ ካደሬዎችዎ
እየታያችሁ አይመስልም። የእናንተን በሥልጣን መቆየት አገሪቱ ለተጋፈጠቻቸው ችግሮች ሁሉ እንደ ቁልፍ መፍትሔ አድርጎ ማየት
የአደጋውን መጠን እና ጥልቀት ያለመረዳት ችግር ብቻ ሳይሆን የመጣንበትን የፖለቲካ አዙሪት ድግምግሞሽ ማሳያም ይመስለኛል።
የኢትዮጵያ ችግር ከቁመታችሁ በላይ ከሆነ ውሎ አድሯል። አደጋዎቹም እናንተ ብቻችሁን የማትመልሱትበት ደረጃ ላይ ከደረሱ
ከራርሟል። ሞልቶ እየፈሰሰ ያለውም ግፍ እናንተን ጠራርጎ የሚሄድ ብቻ ሳይሆን አገሪቷንም ወደ ለየለት የፖለቲካ ቀውስ የመክተት
አቅሙ እና ፍጥነቱም እየጨመረ መሜጣቱን ከወዲሁ መገመት ይቻላል።›› ያሬድ ኃይለማርያም የስብዓዊ መብቶች ተሞጋች፡፡
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ቢሮ መረጃ መሠረት በኦሮሚያ ክልል ህዝብ በ1994 እኤአ አስራ ሰባት ሚሊዮን ነበረ፡፡ በዊኪፒዲያ
(Wikipedia) ድር-ገፅ ገንዘብ ከፍለው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ አዲስ አበባ ወይም ፍንፍኔ በመባል
እንደምትታወቅ ታሪክን በርዘው አፅፈዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልለ ውስጥ የሚገኙ ሃያ አንድ የዞን አስተዳደር ከተሞች ውስጥ አዳማ፣ አንቦ፣ አሰላ፣ ባደሳ፣ ባሌ ሮባ፣ በደሌ፣
ቢሸፍቱ፣ ቤጊ፣ ቡሌ ሆራ፣ ጭሮ፣ ደንቢ ዶሎ፣ ፍቼ፣ ጊንቢ፣ ጎባ፣ ሃረማያ፣ ሆለታ፣ ጅማ፣ መቱ፣ ነገሌ አርሲ፣ ነቀምት፣ ሰበታ፣
ሻሸመኔ፣ እና ወሊሶ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በነዚህ ከተሞች ውስጥ ኦሮሞ ያልሆነ ህብረ ብሄር ህዝብ በቁጥር ስለሚበልጥ
የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ሌላውን ህብረ ብሄር ህዝብ ከኦሮሞ ምድር ውጡ በማለት ልክ እንደ ሻሸመኔ ከተማን
አቃጥለው፣ ሰዎች ገድለው፣ ንብረት ዘርፈው በአደባባይ የፈጸሙትን ወንጀል በሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ የተፎካካሪ
ፓርቲዎችን እጩዎች በመግደል፣ በመደብደብና በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ፡፡ “The Oromia
Region (Oromo: Oromiyaa) is a regional state in Ethiopia, the homeland of the Oromo people.
The capital city of the State of Oromia is Addis Ababa also known as Finfinne. [4][5]  Currently the
state consists of 21 administrative zones. [6][7] Towns in the region
include Adama, Ambo, Asella, Badessa, Bale Robe, Bedele, Bishoftu, Begi, Bule
Hora, Chiro, Dembidolo, Fiche, Gimbi, Goba, Haramaya, Holeta, Jimma, Metu, Negele
Arsi, Nekemte, Sebeta, Shashamane and Waliso, among many others.”
የኦሮሚያ ክልል ከሱማሌ ክልል በስተ ምስራቅ ፣ አማራ ክልል፣አፋር ክልል፣ እነ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ በስተ ሰሜን፣ ድሬዳዋ
ከተማ አስተዳደር በሰሜን ምስራቅ፣ ደቡብ ሱዳን መንግሥት፣ ጋምቤላ ክልል፣ ደቡብ ክልል እና ሲዳማ ክልል በስተ ምዕራብ ፣
ኬንያ መንግሥት በስተ ደቡብ ያዋስናሉ፡፡ በ2011 የህዝብ ቆጠራ የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር ሠላሳ አምስት ሚሊዮን እንደሆነና
የኦሮሚያ መሬት ሥፋት ሁለት መቶ ሰማንያ ስድስት ስድስት መቶ አስራ ሁለት ስኮየር ኪሎሜትር (286,612 square
kilometers) እንደሆነ በአፈ ታሪክ ያለአንዳች ማስረጃ የሌሎች ክልሎችን መሬት ጠቅሎ በመውሰድ ለድንበርና ወሰን ግጭት
ከየድንበርተኞቹ ክልላዊ መንግስታትና አጎራባች አገራቶች ጋር ጭምር ለማያባራ ጦርነትና የህዝብ እልቂት፣የመሠረተ ልማቶች
ውድመት፣ የፋብሪካዎች መቃጠል፣ የስልክ የመብራት፣ ውኃ፣ የኢንተርኔት አገልግሎቶች መቃጠል፣ የመንግስታዊ ተቆማቶች
ቢሮዎች መጋየት (ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች ወዘተ)፣ የግል ትምህርት ቤቶች ክሊኒኮች፣ሆቴሎች፣ የእርሻ ቦታዎች ወዘተ
መውደም ኦነግና ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የፌዴራል መንግስት ዐብይ አህመድ፣ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ሽመልስ አብዲሳ
ለአለፈውም ለመጭውም ጥፋት ተጠየቂ ናቸው፡፡
“It is bordered by the Somali Region to the east; the Amhara Region, the Afar Region and
the Benishangul-Gumuz Region to the north; Dire Dawa to the northeast; the South
Sudanese state of Upper Nile, Gambela Region, Southern Nations, Nationalities, and Peoples'
Region and Sidama Region to the west; the Eastern Province of Kenya to the south; as well

as Addis Ababa as an enclave surrounded by Oromia Special Zone Surrounding Finfinne in its
center and the Harari Region as an enclave surrounded by East Hararghe in its east.
The 2011 census reported the population of Oromia as 35,000,000; this makes it the largest
regional state in population. It is also the largest regional state covering 286,612 square
kilometers. [8]  Oromia is the world's forty-second most populous subnational entity, and the most
populous subnational entity in all of Africa.” (4)
በኢትዮጵያ ከተማ ንዋሪዎች ከሻሸመኔ ህዝብ ጭፍጨፋና ከተማ ቃጠሎ ምን እንማራለን!!! በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች
ፍርድ ቤት ወንጀለኞቹ ለማቅረብ ከወዲሁ ተደራጅተን ስለ ወንጀለኞቹ መረጃ እየሰጠን ለፍርድ ማቅረብ ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሲን
ሊዳኙ ሰዓቱ ስለደረሰ ሳንፈራ የኦነግን የፖለቲካ ሴራ ማጋለጥ ተገቢ ነው እንላለን፡፡ ጥንትም ሆነ ዛሬ ሻብያ ወያኔና ኦነግ አንድም
ሁለትም ሦስትም ናቸው፡፡ ኦነግ ከወያኔ ያማይማር አራጅ ድርጅት ነው!!! ለዚህ ነው በግፍ ሰዎች የገደለ፣ ሴቶች የደፈረ፣ ህዝብ
ያሰቃየ፣ ኢሰብዓዊ ግርፋት፣ ድብደባ ያደረገ፣ እስረኞች ያሰቃየ፣ ለፍርድ እንዲቀርብ ማድረግ ይኖብናል፡፡ የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት
አቃቢ ህግ ክስ የሚመሠርትባቸው ግለሰቦች በፈፀሙት ወንጀሎች ዝርዝር ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ ወንጀል በአንቀጽ አምስት
ደንብ መሰረት የዘር ማፅዳት፣ የስብዓዊ መብቶች ጥሰት ወንጀል፣ የጦር ወንጀል እንዲሁም የወረራ ወንጀል ክሶች ማስረጃ ማቅረብ
የሁሉም ዜጋ ግዴታ ነው እንላለን፡፡
ሻሸመኔ ምን እንማራለን መደራጀት… መደራጀት… መደራጀት!!!
ከሃጫሉ ግድያ በኋላ በተከሰተ ሁከት ከፍተኛ የንብረት ውድመት ከተከሰተባቸው ስፍራዎች መካከል ሻሸመኔ ከተማ አንዷ ነች
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች የተፈጸሙ ጥቃቶች በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ
ወንጀሎች ናቸው ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርት መሠረት።
የሦስት ልጆች አባት ሆነው ታዋቂው ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሰኞ ሠኔ 22/2012 ዓ.ም ምሽት አዲስ አበባ ውስጥ ገላን
ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በተተኮሰበት ጥይት ለህልፈት መዳረጉ ይታወሳል።
ኢሰመኮ በሪፖርቱ በወንጀል ድርጊቱ ሲሳተፉ የነበሩት ሰዎች፤ ተግባራቸው ስልታዊና የተቀናጀ ወይም የሰፊ ጥቃት አካል መሆኑን
በማወቅ የተሳተፉበት እንደነበር ጠቅሶ፤ እነዚህ በቡድን የተፈፀሙት ጥቃቶች ጠቅላላ ድርጊቶቹና ውጤታቸው በሰብአዊነት ላይ
የተፈጸመ የግፍና ጭካኔ ወንጀል መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል። መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጨምሮም
ምርመራ ባደረገባቸው 40 የኦሮሚያ አካባቢዎች፣ የአርቲስቱን ሞት ተከትሎ በነበሩት 3 ተከታታይ ቀናት በተከሰተው የፀጥታ
መደፍረስ፣ የ123 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ቢያንስ በ500 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል ብሏል። ሕይወታቸው ካለፈ ሰዎች
ውስጥ 35ቱ በሁከቱ በተሳተፉ ግለሰቦችና ቡድኖች የተገደሉ መሆኑን ኢሰመኮ ጠቅሶ፤ በተጨማሪም ጥቃት ፈጻሚዎቹ በ306
ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሰዋል ብሏል። በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ ቢያንስ 76 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን
ከ190 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው አመልክቶ፤ በፀጥታ መደፍረስ ወቅት በተከሰተ ፍንዳታ፣ ቃጠሎና መሰል
አደጋዎች 12 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ሪፖርቱ ገልጿል። በሁከቱ በህይወትና በሰዎች አካል ላይ ከደረሰው ጉዳት
በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸው፣ በግለሰቦች፣ በንግድ ድርጅቶች እንዲሁም በመንግሥት
ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመትና ዘረፋ መፈጸሙን የኮሚሽኑ ሪፖርት አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው በዚህ ዝርዝር ሪፖርት ላይ በጥቃቶቹ ብዙ ቁጥር ያላቸው ከቦታ ቦታ በቡድን
ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎች እንደተሳተፉበት ገልጾ ለድርጊቱም የተለያዩ ነገሮችን መጠቀማቸውን ገልጿል። ጥቃት አድራሾቹ በሰዎች
ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን፣ የአካል ጉዳት ማድረሳቸውንና "ፍጹም ግፍና ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በማሰቃየት ወይም በማረድ
ጭምር ሰዎችን ገድለዋል" ሲል ድርጊቱ በሰለባዎቹ ቤት ውስጥና በመንገድ ላይ ጭምር የተፈጸመ እና አሰቃቂ እንደነበር ገልጿል።
አክሎም አጥቂዎቹ ከፈጸሙት ድብደባ፣ ግድያና ንብረት ማውደም በተጨማሪ ተጎጂዎችንና የተጎጂ ቤተሰቦችን "ብሔርን መሰረት
ያደረጉ ስድቦች ሲሳደቡ፣ ሲያንቋሽሹ፣ ሲያስፈራሩና ሲዝቱባቸው" እንደነበር ሪፖርቱ ጠቅሶ ይህም ሰላማዊ ነዋሪዎች በብሔር
ወይም በሐይማኖታቸው ምክንያት ለጥቃት የመጋለጥ ከፍተኛ ስጋትና የሥነ-ልቦና ጭንቀት እንደፈጠረባቸው ኢሰመኮ መገንዘቡን
ጠቅሷል። ይህ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ይፋ የተደረገው ሪፖርት እንደሚለው የጥቃቱ ባሕሪና መጠን እንደ የአካባቢው
ሁኔታ የሚለያይ ቢሆንም "በአመዛኙ የክርስቲያን እምነት ተከታዮች በብዛት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ጥቃቱ በአማራ ብሔር
ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች በብዛት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ደግሞ በኦርቶዶክስ ክርስቲያን
እምነት ተከታዮች ላይ ያነጣጠረ ነበር" (5)
በኦሮሚያ ክልል ከ1 (አንድ) ሺህ በላይ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱ ተነገረ።
በመኖሪያ እና በንግድ ቤቶች ላይ የደረሰ ጉዳት፤በአሮሚያ ክልል፤ 523 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። 499 (አራት መቶ ዘጠና
ዘጠኝ) መኖሪያ ቤቶች ደግሞ እንደተሰባበሩ የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል።መንግሥት
በመኖሪያ ቤቶች፣ በንግድ ቤቶች እና በመንግሥት ተቋማት ላይ የደረሱትን ጉዳቶች፤ "የተቃጠሉ፣ የተሰባበሩ እና የተዘረፉ" በሚሉ
ጎራዎች ከፋፍለው የደረሰውን የጉዳት እያጠኑ መሆኑን አስረድተዋል።
በንግድ ቤቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት በአሃዝ ሲያስቀምጡ፤ 195 (መቶዘጠና አምስት) ሆቴሎች መቃጠላቸውን እና ሌሎች 32
(ሠላሳ ሁለት) ሆቴሎች ደግሞ በንብረት ላይ የመሰባበር ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም 104 (መቶ አራት)
የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቃጠሎ ውድመት እንደደረሰባቸው አመልክተዋል። ስድስት አነስተኛ እና ግዙፍ ፋብሪካዎች በሁከቱ
መቃጠላቸውን የተናገሩት አቶ ጌታቸው፤ የተቃጠሉ አነስተኛ ንግድ ቤቶች ቁጥር ድግሞ 232 (ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለት)
እንዲሁም የተሰባበሩት አስተኛ ንግድ ቤቶች አሃዝ 219 (ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ) መሆኑን አስረድተዋል።
በተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት፤የክልሉ ቃል አቀባይ እንደሚሉት ከሆነ 232 የግል እንዲሁም 12 የመንግሥት ተሸከርካሪዎች
በእሳት እንዲጋዩ ተደርገዋል። በአጠቃላይ በግል እና በመንግሥት ቤቶች እንዲሁም ተሽከርካሪዎች ላይ የደረሰው ጉዳት መጠን
እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል። ዘረፋን በተመለከተ ግን የተሰባሰቡ ማስረጃዎች ተጠናቅረው ስላላለቁ ዝርፊያ የተፈጸመበትን
የንብረት መጠን ማወቅ ለጊዜው አዳጋች እንደሆነ ተናግረዋል። በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰው በምዕራብ አርሲ
ሦስት ወራዳዎች ውስጥ መሆኑን የተናገሩት አቶ ጌታቸው፤ በተለይ በሻሸመኔ እና ባቱ ከተሞች እንዲሁም በባሌ ዞን ሮቤ እና አጋርፋ
ከተሞች የደረሰው ገዳት ከሌሎች አካባቢዎች አንጻር ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በኦሮሚያ በብዙ ሽህ ህዝብ የተፈጸመ ወንጀል ግድያ፣ ዘረፋ፣ ንብረት ማውደም፣ ወዘተ ምን እንማራለን፡

ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በተፈጠረው አለመረጋጋት በኦሮሚያ ክልል በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰዎች ቁጥር 7123
(ሰባት ሽህ መቶ ሃያ ሦስት) መድረሱን አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የክልሉ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ጨምረውም
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሰዎች ጋር በተያያዘ ፖሊስ አና አቃቢ ሕግ ከ5 ሺህ በላይ በሚሆኑ መዝገቦች ተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ
መመስረታቸውንም አመልክተዋል። (6)
‹‹የሕግ የበላይነትን ለማስፈን፣ የአገሪቱን ጸጥታና ደህንነት ለማስከበር፣ የዜጎችን መብት ለማክበርና ለማስከበር፣ የአገሪቱን
ዳርድንበር ለማስከበር እና ግጭቶችን ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል ቁመና ያጣው አስተዳደርዎ ኢትዮጵያን እጅግ አስፈሪ ወደሆነ
ወጥመድ ውስጥ ከቷታል። ዛሬ ኢትዮጵያ፤ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ወድቃ ሌሎች አዳዲስ ግጭቶችን ልታስተናግድ አፋፍ ላይ
ነች፣ ከሻሸመኔ፣ ከመተከል፣ ከማይካድራና ከአክሱም የከፉ በዘር ላይ ያነጣጠሩ ግጭቶችን ልታስተናግድ እንደምትችል በአለም
አቀፊ ሚዲያዎች ሳይቀር መወያያ ሆናለች፣
የአባይ መዘዝ የቀሰቀሰው አካባቢያዊ ውጥረት ወደ ድንበር አቋራጭ ጦርነት ሊያመራ አንድ ሐሙስ የቀረው መሆኑን በርካታ
ማመላከቻዎች እየታዩ ነው፣ በአገሪቱ ውስጥ እየታየ ያለው አስከፊ የኑሮ ግሽፈት እና በላዩ ላይ የታከለው የኮቪድ ወረርሽኝ እጅግ
አስከፊ የሆነ የኑሮ እና የኢኮኖሚ መቃወስን እያስከተለ ነው፣ ከመቼው ጊዜ በከፋ ሁኔታ የእርስ በርስ ግጭቶች፣ መፈናቀል፣
ዝርፊያና የወንጀሎች መበራከት ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም ውሎ በሰላም ማደርን እንደ ብርቅ ነገር እንዲታይ እያደረገ ነው፣››
‹‹አገሪቱ በዚህ ሁሉ ውጥረት ውስጥ ሆና ጠቅላይ ሚንስትር አብይም ሆኑ አስተዳደራቸው በያዛችሁት የማስመሰል ፖለቲካ
የምትቀጥሉ ከሆነ ታሪክ የምትሆኑበት ጊዜ እሩቅ አይመስለኝም። ችግሩ እየመጣ ያለው አደጋ እናንተን ጠራርጎ የማያቆም መሆኑ
ነው። አሁንም ለእናንተም ሆነ ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ከመናገር ወደ ኋላ አልልም። መፍቴሔ + መንግስት አገሪቷ የገባችበትን
ቀውስ እና ያንጃበበውን አደጋ ከግምት በማስገባት የብሔራዊ የቀውስ መፍትሔ አፈላላጊ አካል በአፋጣኝ ሊያዋቅርና አፋጣኝ
የምክክር መድረኮችን ሊያካሂድ ይገባል። በዚህ ውስጥ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት መሳተፋቸውን ማረጋገጥ ግድ ይላል።
+ ገዢው ፖርቲም ሆነ ተፎካካሪ ፖርቲዎች ግጭት አባባሽ ከሆኑ ድርጊቶቻቸው ታቅበው ወደ ምክክር እና የጠረጴዛ ውይይቶች
ለመምጣት የሚከፈለውን መስዋትነት ሁሉ መክፈል አለባቸው።
+ በገዢው ፖርቲ አባላት እና በክልሎች መካከል የሚታየው መፉጠጥ እና ጤናማ ያልሆነ ፉክክር ከወዲሁ እልባት ይሻል።
በፖርቲው ውስጥ ያለን ሰላም ማምጣት የተሳነው በወ/ሮ ሞፈሪያት የሚመራው ‘የሰላም ሚንስትር’ የአገር ሰላም ለማምጣት
አቅም ያለው ስለማይመስል ሊፈተሽና በአዲስ መልክ ሊዋቀር ይገባል።
+ ውዝግብ የተነሳባቸው የውስጥ የድንበር ጥያቄዎች ዘላቂ የሆነ የሕግና የፖለቲካ መፍትሔ እስኪያገኙ ድረስ ለሌሎች ግጭቶች
መንስዔ ሳይሆኑ በፊት በአፋጣኝ ከተወዛጋቢዎቹ ክልሎች እጅ ወጥተው በፌደራሉ መንግስት እንዲተዳደሩ ሊደረግ ይደረግ።
+ የሽምቅ ተዋጊዎች፤ በዋነኝነት ኦነግ ሽኔ እያደረገ ያለውን መስፋፋት እና በንጹሀን ዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ሰቆቃ ባፋጣኝ
መቆጣጠር ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆን አለበት።
ያንዥበቡት አደጋዎች ሊቀለበሱ የሚችሉ ናቸው። ሆኖም የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ርብርብ ይጠይቃሉ። ገዢው ፖርቲ አደጋዎቹን
ብቻውን የመቋቋም አቅም እንደሌለው በብዙ መልኩ እየታየ ነው። የፖለቲካ ቁርጠኝነት ብቻ ሳይሆን ብሔራዊ፣ ሁሉን አቀፍ፣
የአጣዳፊና የቀውስ መፍትሄ ስልት መቀየስ የግድ ይላል። በዚህ ዙሪያም የምክክር መድረኮች ሊከፈቱ ይገባል።›› (7)
ኦነግ ‹‹ነፍጠኛ ከኦሮሞ ይውጣ!!!››‹‹ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር!!!›› በኢትዮጵያ የከተማ ንዋሪዎች ከሻሸመኔ
ህዝብ ጭፍጨፋና ቃጠሎ ተማሩ!!! በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ወንጀለኞቹ ሊዳኙ ሰዓቱ ደረሰ!!!
ምንጭ፡-
1-በሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች በተከሰተው ግጭት ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ/31 መጋቢት 2021/
https://www.bbc.com/amharic/news-56582178
2-በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ ስለተፈፀመው ጥቃት ነዋሪዎች ምን ይላሉ?/1 ሚያዚያ 2021
https://www.bbc.com/amharic/news-56596280
3- “በሁሉም ቦታ በደረሰው ጥቃት አጸፋ እርምጃ በክልልና በፌዴራል መንግስት ቅንጅት እየተወሰደ ይገኛል”- ጠቅላይ ሚኒስትር
ዐቢይ አሕመድ/ https://zehabesha.info/amharic/archives/116207
4-Oromia Region – Wikipedia
5-"መንግሥት ያለ አይመስልም ነበር"፡ በሰብአዊነት ላይ ወንጀሎች ተፈጽመዋል-ኢሰመኮ
1 ጥር 2021 https://www.bbc.com/amharic/news-55485498
6-በሁከቱ ከ1ሺህ በላይ መኖሪያና ንግድ ቤቶች፣ ከ240 በላይ ተሽከርካሪዎች ወድመዋል
21 ሀምሌ 2020 https://www.bbc.com/amharic/news-53488247
7-ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ/በያሬድ ሃ/ማርያም/

Leave a Reply