
“…ኦነግ አዲስ አበባ ተቀምጦ “እኛ በአማራነታችን አዲስ አበባ ፖሊስ ታስረናል በጣም ያሳፍራል‼” ጋዜጠኛ ገነት አስማማው አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 8/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ጋዜጠኛ ገነት አስማማው እና ደራሲ አሳዬ ደርቤ እና መልዕክታቸው:_ (1) ጋዜጠኛ ገነት አስማማው:_ “…ኦነግ አዲስ አበባ ተቀምጦ “እኛ በአማራነታችን አዲስ አበባ ፖሊስ ታስረናል በጣም ያሳፍራል‼” “…እኔ በስራዬ ጋዜጠኛ ነኝ ማንነቴ ከጠየከኝ አማራ ነኝ ይኽንን መለውጥ አልችልም።” በአማራነቴ ለማሸማቀቅ ሲፈልጉ እኔ እኮራበታለሁ የጠሉት ሙያዬን ሳይሆን ማንነቴን ነው ለዛ ደግሞ በርካታ በደሎች ደርሶብኛል። ስያዝ ተደብዴቤአለሁ የስነ ልቦና ጫና አድርሰውብኛል። “…ኦነግ አዲስ አበባ ተቀምጦ “እኛ በአማራነታችን አዲስ አበባ ፖሊስ ታስረናል በጣም ያሳፍራል። የብልፅግና መሪ ዐቢይ አህመድ የአማራ ህዝብ በተፈጸመበት ጄኖሳይድ መጠየቅ አለበት በርካታ በደሎች በዚህ አምስት አመት ተፈጽሟል ባለቤቱ ዐቢይ አህመድ ነው። ጋዜጠኛ ሆኜ ይህን መዘገብ ግዴታዬ ነው ክሳችን ለምን ወንጀላችን አጋለጣችሁ ነው። ለምን ዘገባችሁ ተብሎ ነው ስራዬ እንደ ጋዜጠኛ ለተጎዳው ህዝብ ሽፋን መስጠት ሙያዊ ግዴታዬ ነው የታሰርኩት ግን እንደ አማራ ነው። ትልቅ በደል ተፈጽሞብናል። “በእስሬ እናቴ በጣም ትጨነቃለች ይኽን ስራ ለምን አትተይም ትለኝ ነበር አሁንም ድረስ እንደጥፋተኛ በመቁጠር ቀድሜ ነግሬሽ ነበር በማለት ትናገረኛለች እኔ ብተዋቸው ማንነቴን አይተውትም ስላት መልሳ ታበረታኛለች። አሁን እየገባት መጥቷል አልሰበረም! (ጋዜጠኛ ገነት አስማማው!) (2) ዛሬ ቅዳሜ በፌደራል ፖሊስ እና አዲስ አበባ ፖሊስ አማሮችን ጠይቄ ነበር። ታሳሪዎቹ የሰጡኝ መልዕክት በአጭር አገላለጽ አቀርበዋለሁ። “አዎ አማራ ነኝ! ከአማራ ህዝብ አጀንዳ ውጭ ምንም ቅድሚያ ልሰጠው የሚገባ ነገር የለኝም። በዚህ ጉዳይ እንደወንጀል ተቆጥሮ በመታሰሬ አልጸጸትም። አማራ ተበድሏል በሚገባ ትክክል ነኝ። ይሁን እና የሚከፈለዉ ዋጋ በተገቢዉ ልክ ለህዝባችን በማድረስ ረገድ ክፍተት አለ። አማራዎች ድምፅ እንድትሆኑ እጠይቃለሁ። ለማነው የታገልነው ብዬ እንዳስብ ልገደድ አይገባም ለአማራ ብለን እንጅ ሌላ ምክንያት ኖሮን አይደለም። ብዙ አጀንዳ አለ አውቃለሁ ቢሆንም ስለኛም መናገር የትግሉ አካል ነው። “..በአግባቡ ድምፃችን እንዲሰማ ህዝባችን ከጎናችን ሊቆም ይገባል። “አዎ አማራ ነኝ! አሳዬ ደርቤ ከፌደራል ፖሊስ ሜክስኮ ምንጭ_ስንታዬሁ ቸኮል
Source: Link to the Post