የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ/ም አገራዊ አጠቃላይ ምርጫ
ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ጋር ተዳብሎ፣ የደቡብ ምዕራብ ክልልን መመስረት ለመወሰን የሚደረገው ሕዝበ ውሳኔ 8ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ/ም እንደሚከናወን አስታውቆል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ/ም የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክርቤቶች ምርጫዎች እንደሚፈፀሙ አስታወቆል፡፡ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ቀናት ምርጫውን ለምን ማድረግ እንደፈለገ የሚሠጠው ምላሽ ውኃ አያነሳም፡፡ ግንቦት 28 ቀን የመረጡት የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ሰዎች በሌላ መታወቂያ አዲስ አበባና ድሬዳዎ ከተማ ውስጥ ገብተው እንዲመርጡ የተደረገ የፖለቲካ ምርጫ ሴራ ነው፡፡ የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በተለይ የአዲስ አበባ ምርጫ በባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አሸናፊነት እንደሚጠናቀቅ በውስጣዊ ጥናት በማረጋገጣቸው የሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ/ም ምርጫ በአዲስ አበባ ምርጫ እንዳይካሄድ ሁከትና ሽብር በመቀስቀስ ምርጫው እንዳይካሄድ ያደርጋሉ፡፡ የስድስተኛው ዙር ምርጫ በኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ አሸናፊ እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለህዝብ ያሳውቃል፡፡ በኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ ከወራት በኃላ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በባለአደራ መንግሥት እንድትተዳደር በፓርላማ ያስወስናሉ፡፡ ኢዜማና ብልጽግና ፓርቲዎች በጋራ አዲስ አበባን ያስተዳድራሉ፡፡ ፕሮፊስር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሹመት ይታጫሉ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተቌማቱ ዝግጁነትና ገለልተኛነት፣ የታዛቢዎችና የምርጫው ሂደት ታዓማኒነት፣ የብሔረሰቦች የማንነት ጥያቄዎችና ከምርጫ ክልል ጋር የሚያያዙ ጥያቄዎች፣እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄዎችና የሚዲያ ሚዛናዊነትና ተዓማኒነት፣ ምርጫው ውጤት ጋር ተያይዘው ሊነሱ የሚችሉ ጉዳዩች አፈታት የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ባለው መሠረት ያስፈፅማል፡፡ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ለማድረግ የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ አለመረጋጋት እያለ በምርጫው ተጨማሪ ግጭቶች ተቀስቅሰው የሰዎች እልቂትና የህዝብ መፈናቀል እንደሚከሰት ያውቃሉ ከወዲሁ በኦሮሚያ ወለጋ፣ ቢኒሳንጉል መተከል፣ በደቡብ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ አጣዬ በኦነግ የሚደረገው ዘር ማጥፋትና የህዝብ መፈናቀል እያለ ምርጫ ዘበት እንደሆነ ከተላላኪ አስፈፃሚ ሹማባሾች በስተቀር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተገንዝቦል፡፡
የኦሮሞ ጦር (ልዩ ሀይል) ከእንጦጦ ተራራ ጀርባ የሰፈረው ለምን አላማ ይሆን? ከ2011ዓ.ም መገባደጃ ጀምሮ አዲስአበባ ከተማ ዙሪያዋን ከብቦ የሰፈረው የኦሮሞ ጦር ይበልጥ ወደ መዲናዋ መቅረቡ ነዋሪዎችን እያሳሰበ ነው። በተለይ በእንጦጦ ጀርባ በሽዎች የሚቆጠር የኦነግ ጦር ከሰፈረ አንድ አመት አልፎታል ያሉት በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች ናቸው። የወንጭፍ ምንጮች እንዳረጋገጡት በእንጦጦ ተራራ ጀርባ ለሰፈረው ጦር በየቀኑ ከአስር በላይ ሰንጋ በሬዎች እርድ እንደሚፈፀም እና የቄራ መኪኖችም በየቀኑ እንደሚመላለሱ ተመልክተናል ብለዋል፡፡ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ ይህ በየተራሮችና ጫካዎች እየተቀለበ የሚገኝ ጦር ሰሞኑን በየካና እንጦጦ ተራሮች ላይ መታየት መጀመራቸው በቅርቡ አዲስ አበባ ነዋሪዋች ስጋታቸውን ገልጸዋል ። የኦሮሚያ ክልል ከ30-35ሽህ ልዩ ሀይል በ34 በሆነ ዙር እንዲሁም የኦሮሞ ነፃነት ግንባርም በሽዎች የሚቆጠር አዲስ ወታደሮች ማስመረቃቸውን ከሰሞኑ አስተውቀዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ የሚገኙ የውጭ ሃገራት ኤምባሲዎች ለዘጎቻቸው ጥብቅ የሆነ የደህንነት መልዕክት ማስተላለፍ መጀመራቸው ተሰምቷል። በተለይ የአሜሪካ የእንግሊዝ የእስራኤል ኢምባሲዎች “አዲስ አበባ ዙሪያ የሰፈረ ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ጦር አለ። ጦሩ በማን እንደሚመራም አይታወቅም። እናም እንጦጦን ጨምሮ ማንኛውም የውጭ ሃገር ዜጋ ለጊዜው ከአዲስ አበባ ውጪ እንዳይንቀሳቀስ። በእንጦጦ ጫካም ለጊዜው የእግር ጉዞ እንዳያደርግ” የሚል መልእክት ለዜጎቻቸው በኢሜይል ማስተላለፋቸው ነው የተሰማው። የኢትዮጵያ ህዝብ ህዝቡ ግን ምርጫው ይቆየን፣ የመታረጃ ሜንጫው፣ ገጀራው፣ ካራው፣ ጦሩ፣ በፊት እንዲሰበሰብለት ይማፀናል!!! በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሁንም ብዙ ህዝብ እየታረደ ሲሆን መቶ ሰባ አምስት ሽህ ህዝብ ከቀየው ተፈናቅለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ስድስተኛው ዙር ምርጫ ይቆየን፣ በሃገሪቱ የተሠራጨው ህገወጥ የጦር መሳሪያ የመታረጃ ገጀራው፣ ሜንጫው፣ ካራው፣ ጦሩ፣ በፊት ይሰብሰብልን ብሎ ይማፀናል፡፡ በኢትዮጵያ ህገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ዶክተር አብይ ስልጣን ከጨበጡበት መጋቢት 2010 ዓ/ም ጀምሮ በከፍተኛ ዓይነትና ብዛት መጨመሩ መረጃዎች ይጠቆማሉ፡፡ በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰ የስብዓዊ መብቶች ጥሰት ፡-
- ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ የህወሓት ኃይሎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ በተቀሰቀሰው ጦርነት ሳቢያ 52 ሽህ ወጣቶችን ህይወት እንደቀጠፈ መረጃ ወጥቶል፡፡
- ከዚህ በተጨማሪም ግጭቱን በመሸሽ ከ60 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን የገቡ ሲሆን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩት ደግሞ እዚያው በክልሉ ውስጥ ተፈናቅለው ይገኛሉ፡፡
- በትግራይ ከነበሩት 226 (ሁለት መቶ ሃያ ስድስት) የጤና ተቌማት ውስጥ በሥራ ላይ ያሉ 20 ብቻ ናቸው፡፡
- በትግራይ ከነበሩት 40 (አርባ ) ሆስቲታሎች ውስጥ በሥራ ላይ የሚገኙ አሥር ብቻ ናቸው፡፡
- በትግራይ ከነበሩት 250 የጤና ተቋማት አምቡላንሶች ተዘርፈው የቀሩት 54 አምቡላንሶች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ጠቅሶ በቀጣይ ጊዜያትም ተጨማሪ 52 አምቡላንሶች ተጠግነው አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ብሏል።
- በትግራይ ከነበሩት 271 (ሁለት መቶ ሰባ አንድ) ትምህርት ቤቶች ተዘርፈዋል ወድመዋል፡፡ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተለይተዋል፡፡
- በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ኃይሎች መካከል በተነሳው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል እንዲሁም በመቶ ሺዎች ደግሞ ከመኖያቸው መፈናቀላቸውን የረድኤት ድርጅቶች ገልጸዋል። 700 000 (ሰባት መቶ ሽህ) የተፈናቀሉ ዜጎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ፡፡
- ህወሓት ከሥልጣን ሲወገድ በፌደራል መንግሥቱ የተሾመው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደሚለው ከትግራይ ክልል ነዋሪ ውስጥ ከግማሽ በላይ ወይም አራት ሚሊዮን ያህል ሰዎች የእርዳታ ድጋፍ ይፈልጋሉ።
- ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል።
- በትግራይ 524 (አምስት መቶ ሃያ አራት) ሴቶች ተደፍረዋል፡፡
- የኢትዮጵያ መንግስት በጦርነት ኢኮኖሚ ውስጥ ተዘፍቆል፣ ሃገሪቱ በትግራይ ክልል 52 ሽህ ወጣቶችን ህይወት የቀጠፈ በልማት ሊሰማራ የሚችል ትኩስ ኃይሎን አጥታለች፣ በሌላ በኩልም ሱዳን ኢትጵያን ወራለች፡፡ በዚህ የጦርነት ኢኮኖሚ በአንድ በኩል በመላ ሃገሪቱ በትግራይ ጦርነት ምክንያት 3.5 ሚሊዩን ህዝብ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል፣ በትግራይ ከ50 ሽህ ሰዎች በላይ ወደ ሱዳን ተሰደዋል፣ በትግራይ መቐለ የውኃ ችግር ተባብሶል፣ በአማራ ክልል የአንድ ቢሊዮን ብር የሚገመት የእርሻ የሰብል ምርት በሱዳን ወታደሮች ተዘርፈዋል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በወለጋ በአማራ ዜጎች ላይ የዘር ማፅዳት የተነሳ ብዙ ሰዎች ታርደዋል ከመቶ ሽህ ህዝብ በላይ ተፈናቅለዋል፣ በደቡብ ክልል በአማሮና ቡርጅ ግጭት ሃያ ሰባት 27 ሽህ ሰው ተፈናቅሎል፣ ኮንሶ ሃምሳ ስድስት ሰዎች ተገደሉ፣ ከሃምሳ ስድስት ሽህ ሰዎች ይፈናቀላል ይሰደዳል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የሆኑት ሚሼል ባሽሌት በትግራይ ግጭት የተሳተፉ አካላት “የጦር እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ፈጽመው ሊሆን እንደሚችል” ገልጸው ነበር። ሚሸል ባሽሌት “የሚረብሹ” ያሏቸው የመደፈር፣ የዘፈቀደ ግድያ፣ መጠነ ሰፊ የንብረት ውድመትና ዘረፋ መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች እየወጡ መሆኑን ጠቅሰው፤ ግልጽና ነፃ ምርመራ ካልተካሄደና ጥሰቱን የፈፀሙትን አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ካልተቻለ እነዚህ ጥቃቶች ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ስጋታቸውን ገልጸው ነበር።
በትግራይ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ የተለያዩ ወገኖች የተፈፀሙ ከባድ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊ እርዳታ ሕጎች ጥሰት መፈጸማቸውን እንደሚያመለክቱ ተናግረዋል። በዚህም የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ተፈጸሙ የተባሉትንና እንደ ጦር ወንጀል ሊቆጠሩ የሚችሉ ሪፖርት የተደረጉ የጅምላ ግድያዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ወሲባዊ ጥቃቶችን ለመመርመር እንዲችል ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር። የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ በእነዚህ ድርጊቶች ውስጥ ሳይሳተፉ አይቀሩም በሚል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን፣ ህወሓትን፣ የኤርትራ ወታደሮችን፣ የአማራ ክልል ኃይሎችን ጠቅሶ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥትም ተፈጽመዋል ስለተባሉት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ግድያዎችን በሚመለከት ከተለያዩ ወገኖች በኩል የሚወጡትን መረጃዎች መሠረት በማድረግ የአገሪቱን የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን፣ ዐቃቤ ሕግን፣ የትግራይ ገዜያዊ አስተዳደርንና የፌደራል ፖሊስን ያካተተ ቡድን አቋቁሞ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል። በተጨማሪም የአፍሪካ ሕብረትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት እየተደረገ ባለው ምርመራ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ በማድረግ ቀረቡትን ክሶች ለማጣራት ፈቃደኝነቱን አሳይቷል።
ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ በምርጫ ወይ በሜንጫ ስድስተኛውን ዙር ምርጫ ለማሸነፍ ቆርጦ ተነስቶል፡፡ ኦነግ ሸኔ በሰሜን ሸዋ አጣዬ ወረራ የፈፀመው የአዲስ አበባን ህዝብ ከወዲሁ ከበነሃል መጣንልህ ለማለት የተዶለተ የፖለቲካ ሴራ ሲሆን ከእንግዲህ የአማራ ህዝብ ‹‹ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉት፤ አንዱን ግባ በለው!!!›› ኦዴፓ ብልፅግናን እና ኦነግ ሸኔን፣ ኦህዴድ በማለት ‹‹በመሣሪያ የመጣ፣ በመሣያ ይወጣ!!!›› ‹‹ በኃይል የመጣ፣ በኃይል ይወጣ!!!›› ይልኃል፡፡
‹‹ከምርጫ በፊት ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለውና!!!›› ‹ብልፅግና ሸኔ› ኦነግ ሸኔና ኦነግ በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት (International Criminal Court) መቅረባቸው አይቀርም!!! እንደ ህወሓት የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ደኢህዴን ወንጀለኞች ለፍርድ ይቀርባሉ፡፡ የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የአሜሪካ፣ የእንግዚዝ፣ የካናዳ፣ በአጠቃላይ የአለም ህብረተሰብ በተደጋጋሚ በኦሮሚያ ክልል፣ በወለጋ ዞን እና በቤኒሻንጉል ክልል፣ መተከል ዞን በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ተከታታይ የዘር ማፅዳት ወንጀል የኦነግ፣ ኦነግ ሽኔ እና ሌሎች ታጣቂ ጏይሎች ወንጀል በማስረጃ አቅርቦ ማስቀጣት የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው፡፡ የዘርና የኃይማኖት ፍጅቱንና ጥቃቱን ባለማስቆም የክልሎቹ መንግስታት እና የፌደራል መንግስቱም እኩል ተጠያቂዎች ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም፡፡ የኣለም ህብረተሰብ ዓይን ኢትዮጵያ ዜጎች ላይ ነው ለአንዴና ለሁሌ በነፃነት በህይወት የመኖር መብታችንን ለማስከበር ጊዜው አሁን ነው!!!! አራጆቻችንን ለዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት መስጠት ታሪካዊ ሃላፊነት አለብን፡፡ ለስድስተኛው ዙር ምርጫ ለመታዘብ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ስለተጋበዙ ፌዴራል መንግሥት ብልፅግና ፓርቲና የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መር ሽብርተኛነትን አጋልጦ መስጠት ጊዜው አሁን ነው!!! የኦነግ ሠራዊት በህዝብ ላይ ጥቃት ቢፈፅም የዓለም ሠላም አሰከባሪ ኃይል በኢትዮጵያ ምድር እንዲገባ ህዝብ በታረዱት ወገኖቹ ስም ይጠይቃል!!! የኦነግ ተረኞቹ አራጆች የሚወገዱት ጊዜው አሁን ነው!!! በተመሳሳይ ሁኔታም ትግራይ ውስጥ በንጹሐን ዜጎች ላይ ለደረሰው እና እየደረሰ ላለው አሰቃቂ ጉዳት፤ በሰሜን ዕዝ እና በማይካድራ የደረሱትን እጅግ አሰቃቂ ጥቃቶች ጨምሮ ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው፤በአንደኛ ደረጃ ህውሃት እና አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሉ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱን ከመለኮስ ጀምሮ ለደረሰው ጠቅላላ ጉዳት፣በሁለተኛ ደረጃ፣ ገዥው ፖርቲ ብልጽግና እና አመራሮቹ፤ በዋነኝነት ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱ ተጠናቋል ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በንጹሀን ዜጎች ላይ ለደረሰው ሰቆቃ፣በሦስተኛ ደረጃ የኤርትራ መንግስት፤ በተለይም ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፎወርቂ፤ በወታደሮቻቸው ለተፈጸመው ዝርፊያ፣ ግድያ እና አስገድዶ መድፈር፤ በእነዚህ አካላት በአንድ ወይ በሌላ መልኩ ለተፈጸሙት የዘር ማፅዳት ወንጀል፣ የመብት ጥሰቶች፣ ጭፍጨፋዎች እና ግጭቶች፤ ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ይሁን፤ ማድረግ የሚገባቸውን ባለማድረግ ተጠያቂ የሆኑትን ሁሉ በገለልተኛ አካል በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንዲጣራ ማድረግ ለኢትዮጵያ ህዘብ ጊዜው አሁን ነው!!!
በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አራጆቹ ይቅረቡ!!!