
በሞቃዲሹ ወጣት ሴቶችን ለሱስ የዳረገው አደገኛ መድኃኒት በይበልጥ የታወቀው ባለፈው ዓመት የ22 ዓመት ሴት አስክሬን በከተማዋ መንገድ ላይ ከተገኘ በኋላ ነበር። የወጣቷ ሕይወት ያለፈው ኦፒኦይድ የተባለ መድኃኒት ከልክ በላይ በመውሰዷ መሆኑን የጤና ባለሙያዎች ተናግረዋል። ኦፒኦይድ በተለይም በቀዶ ሕክምና ጊዜ ለህመም ማስታገሻ በሕክምና ባለሙያዎች የሚሰጥ መድኃኒት ነው። ያለአግባብ ለዚያውም ከልክ በላይ ሲወሰድ ለሱስ ይዳርጋል።
Source: Link to the Post