“ኧረ ተረሳን እኮ ምን ይሻለናል፤ ኧረ እባካችሁ ድምጽ ሁኑን!” ከዝዋይ አዳሚቱሉ የተፈናቀሉ_አቶ አወቀ ይዘንጋው! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም…

“ኧረ ተረሳን እኮ ምን ይሻለናል፤ ኧረ እባካችሁ ድምጽ ሁኑን!” ከዝዋይ አዳሚቱሉ የተፈናቀሉ_አቶ አወቀ ይዘንጋው! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አቶ አወቀ ይዘንጋው ይባላሉ። በዝዋይ አዳሚ ቱሉ ነዋሪ ነበሩ። የተሻለ የሚባል ቤትና ሱቅ ነበራቸው። ታዲያ ምን ይደረጋል! ሰኔ 22 ቀን 2012 በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ላይ ግድያ መፈጸሙን ተከትሎ በማያውቁት ጉዳይ ሌሊቱንና በማግስቱ ቤታቸውና ሌላው ንብረታቸው ምክንያታዊ ትግል በማያውቁ በኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን ባለተልዕኮዎች ወድሞባቸዋል። ከጅምላ አማራ ተኮር ፍጅቱ በተጨማሪ የለየለት ግፍ እና በደል ከደረሰባቸው ከሽህዎች መካከል አንዱ አቶ አወቀ “ኧረ ተረሳን እኮ ምን ይሻለናል፤ ኧረ እባካችሁ ድምጽ ሁኑን!” ሲሉ ግፉን አስታወሱን። በማንነታቸው የለየለት ግፍ የተፈጸመባቸውን ወገኖቻችን ለመደገፍ ብሎም በዘላቂነት ለማቋቋም ይቻል ዘንድ ከፍ ያለ ትኩረት እንስጣቸው፤ እንታገልላቸውም! አሚማ መንግስትን ጨምሮ ያገባናል የምትሉ ወገኖች ሁሉ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ለማስታወስ ይፈልጋል!

Source: Link to the Post

Leave a Reply