You are currently viewing ከሀሮ አዲስ ዓለም እና አካባቢው ወደ ኪረሞ ተወስደው የሰለጠኑ የአማራ ሚሊሾች ለህዝባችን እንድረስ በሚል ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ መደረጉና እስር በሚመስል መልኩ በመስተዳድሩ ክትትል ላይ መሆና…

ከሀሮ አዲስ ዓለም እና አካባቢው ወደ ኪረሞ ተወስደው የሰለጠኑ የአማራ ሚሊሾች ለህዝባችን እንድረስ በሚል ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ መደረጉና እስር በሚመስል መልኩ በመስተዳድሩ ክትትል ላይ መሆና…

ከሀሮ አዲስ ዓለም እና አካባቢው ወደ ኪረሞ ተወስደው የሰለጠኑ የአማራ ሚሊሾች ለህዝባችን እንድረስ በሚል ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ መደረጉና እስር በሚመስል መልኩ በመስተዳድሩ ክትትል ላይ መሆናቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሀሮ አዲስ ዓለም እና አካባቢው ወደ ኪረሞ ተወስደው የሰለጠኑ የአማራ ሚሊሾች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔና በግብረ አበሮቹ ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ ግልጽ ጦርነት የተከፈተበትን በብዙ ሽህዎች የሚቆጠር ተፈናቃይ ህዝባችንን ለመታደግ እንሄዳለን ቢሉም በመስተዳድሩ ክልከላ ተደርጎባቸዋል። ሚሊሾቹ አቶ ደስታ የተባሉ ከሽብር ቡድኑ ጋር እንደሚሰሩ የተነገረላቸው በሚመሩት መስተዳድር ክልከላና እስር በሚመስል መልኩ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑ ለአሚማ የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል። ከመካከላቸው ስልካቸውን የተቀሙ፣ በልዩ ኃይል ካምፕ እንዲገቡ መደረጉንና ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸውም እንዳሉ ምንጮች ተናግረዋል። መስተዳድሩ ገጠር ላይ ያሉ ጠንካራ የአማራ ሚሊሾችን ወደ ከተማ በመጥራት እኛ ነን ስምሪት የምንሰጣችሁ በማለት ተቋም እንዲጠብቁ በሚያደርግበት ወቅት ገጠር ያሉ ንጹሃን ለአሸባሪው ቡድን ጥቃት ተገላጭ እየሆኑ መቸገራቸው በተለያዩ ጊዜያት ተነግሯል። ይህ የኪረሞ መስተዳድር ከምስራቅ ወለጋ ዞን ጋር በመሆን መስከረም 26 ቀን 2014 በሀሮ አዲስ ዓለም የነበሩ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላትን እንዲወጡ ማድረጉ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም ባለፈው ነሃሴ 11 ቀን 2013 የልዩ ኃይል አባላትን ከመርጋ ጅሬኛ ቀበሌ ስኒ ዶሮ ከተማ በማስወጣት በማግስቱ ነሃሴ 12 ቀን 2013 በትንሹ ከ300 በላይ አማራዎች እንዲጨፈጨፉ ማድረጉን በመጥቀስ አሁንም ከቡድኑ ጋር በመገናኘት በንጹሃን ሕይወት ላይ የሚሰሩትን ድራማ ሊያስቀጥሉ ነው በሚል በከፍተኛ ስጋት ላይ መሆናቸውን ገልጸው ነበር፤ ድረሱልን ሲሉ መማጸናቸውም አይዘነጋም። አማራ ሚዲያ ማዕከል(አሚማ) በወቅቱ የኪረሞ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደስታንና የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁን የነዋሪዎችን ቅሬታ መሰረት በቀጥታ በእጅ ስልካቸው በመደወል አነጋግሮ ነበር። አቶ ደስታ ወደ ላይ ደውል እኔን አይመለከተኝም ሲሉ አቶ አለማየሁ ችግር የለውም የተደራጀ የሚሊሻ ኃይል ስላለ አትስጉ በማለት መልሰዋል፤ በዚህም ጉዳዩን ቀለል አድርገው እንደተመለከቱት ተረድተናል። እንደተፈራው አልቀረም መስከረም 30 ቀን 2014 እና በማግስቱ ጥቅምት 1 ቀን በአካባቢው ተደራጅቶ የንጹሃንን ደም ለማፍሰስ ሲያሰፈስፍ የከረመው የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በቡድን መሳሪያ ጭምር በመታገዝ ተኩስ በመክፈት በርካቶችን መግደሉና ማቁሰሉ ታውቋል። በቡድኑ በኩልም ቀላል የማይባል ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል፤ አማራዎቹ አስከሬንና ቁስለኛን በሰው እና በአልጋ እየተሸከሙ ሲወስዱ የሽብር ቡድኑ ግን ከኪረሞ እና ከጊዳ ወረዳ በመኪና ጭምር እየመጣ ሲራገፍ ተስተውሏል፤ በተለይ በጊዳ መስመር የአምቡላንስ እገዛ ጭምር እየተደረገለት መሆኑ የዐይን እማኞች ገልጸዋል። አሚማ ዛሬ ጥቅምት 2 ቀን 2014 ከሀሮ አዲስ ዓለም እና ከኪረሞ ያነጋገራቸው ምንጮች እንዳረጋገጡት ብዙዎች ካለቁ በኋላ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላትን ልኳል። የአማራ ሚሊሾችን የከለከለው መስተዳድሩ ሰልጣኝ የኦሮሞ ሚሊሾችን፣ ቤታችን ተቃጥሎብናል የሚሉ ለአማራ ጥላቻ ያላቸውና ተነጋግረው ለመግባባት አማርኛ ቋንቋ የማይችሉ የልዩ ኃይል አባላትን መላኩ ተገልጧል። አሚማ ወደ ባጊን ቀበሌ እና ቡሬ ቀበሌ ብዙ ሽህዎች ተፈናቅለው እየሸሹ መሆናቸውን አውቋል። ከሀሮ እና ኪረሞ ምንጮችን ለማነጋገር እንደሞከረው ተፈናቃዮች እንዳይጨፈጨፉ ሲታገሉ የነበሩ ሚሊሾችና ወጣቶች ከኦነግ ሸኔ ለምን ተገደለ በሚል ቁጣ በልዩ ኃይል አባላትና አብረው በመጡ የኦነግ ሸኔ ተባባሪዎች እንጠቃለን፣ እንዘረፋለንም የሚል ስጋት እንዳለባቸው ለማወቅ ችሏል። አሁንም ከፍተኛ የሆነ ውጥረት በመኖሩ የሚመለከተው የመንግስት አካል የፌደራል የጸጥታ አካል አስገብቶ እንዲታደጋቸው ነው ተጎጅዎች ጥሪ ያቀረቡት። አሚማ በሁለት ቀኑ ተኩስ በርካታ ንጹሃን እንደተገደሉና እንደቆሰሉ ከነዋሪዎች አረጋግጧል። ከተገደሉት መካከል የ7፣ ከቆሰሉት እና ህክምና ለማግኘት ካልቻሉት ደግሞ የ8 ሰዎች ስም ዝርዝር ደርሶታል። (1) ከተገደሉት መካከል:_ 1) አብዬ ወንድዬ፣ 2) ጌታቸው ካሴ፣ 3) አበበ አደም፣ 4) ሞገስ ለማ_ በመስከረም 30 ቀን 2014 ቆስሎ ጥቅምት 1 ቀን 2014 ያረፈና ቡሬ ሚካኤል ስርዓተ ቀብሩ የተፈጸመ። 5) አንዳርጌ ይርዳው_ መስከረም 30 ቀን 2014 ቆስሎ አድሮ በጥቅምት 1 ቀን 2014 ህይወቱ ያለፈና በሀሮ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ስርዓተ ቀብሩ የተፈጸመ። 6) የሱፍ ከማል እና 7) እስሌማን ወርቁ (2) ከቁስለኞች መካከል:_ 1) ጀማል ክንዱ፣ 2) መሀመድ ይበልጤ፣ 3) ሙላት አስናቀው፣ 4) ጋሻው ይመር፣ 5) ሰለሞን ጋሻው፣ (የአቶ ጋሻው ይመር ልጅ) 6) እባቡ ደሳለኝ፣ 7) ስማቸው ረዳ እና 😎 አድማሱ አብዲሳ_መስከረም 30 ቀን 2014 ተገድሏል በሚል የገለጹ ምንጮች በስህተት ነው ቆስሏል እንጅ በህይወት አለ በሚል አስተካክለውታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply