ከሀዋሳ አዲስ አበባ በሚበር አውሮፕላን ጭስ ቢታይም መንገደኞች ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መውረዳቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀየበረራ ቁጥር ኢቲ 154 ዛሬ ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/pj5VmZpehq-Um5UKHsoS_NCdj4XChFk2AbumFR9OyrxLVuJ4MSaDdDP4wbByctlEENwaMrqX3I9KG9LeqMq5WThct84vyUVT9WBIz4t4EKO2hKWurFoh-C2pzoy3p21B-PUkNEWA9strhmVWHd9Lfp4fCryK33NhjmgUSe2_IZ3mMmKpopgtfbIzuvj-hH_MPCRHoe8pEIJKFSPX9XGXJbLyyAq9n6J0EhruFPuw1woGSnadWTbaQnLEcWjBWFfZjXf3P6esubnHb91LEw1QAuxOI4C_TFh_dCu0YmXdMO78ovOlZA6Qr7JQGeHnOHHBF8vlw2QExCLS9GA1okzK-g.jpg

ከሀዋሳ አዲስ አበባ በሚበር አውሮፕላን ጭስ ቢታይም መንገደኞች ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መውረዳቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ

የበረራ ቁጥር ኢቲ 154 ዛሬ ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ አውሮፕላኑ ውስጥ ጭስ ታይቷል ።

ይሁን እንጂ አውሮፕላኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል በመቆም መንገደኞች ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መውረዳቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ደንበኞቹን ይቅርታ መጠየቁን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

ሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply