ከሁለት ሳምንት በኃላ ኖ ማስክ ኖ ሰርቪስ (NO MASEK NO SERVICE) ሀገራዊ ንቅናቄ ይጀምራል

ከሁለት ሳምንት በኃላ ኖ ማስክ ሰርቪስ (NO MASEK NO SERVICE) በሚል ሀገራዊ ንቅናቄ እንደሚጀመር የጤና ሚኒስቴር እና የህብተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

የኮቪድ-19 ስርጭት ለመከላከል የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃዎች ሲደረጉ ቢቆም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መዘናጋቶች በርክተዋል፡፡ባለፉት አስር ወራት እንድ ሀገር ሲደረጉ የነበሩ የንቅናቄ ስራዎች ተቀዛቅዘዋል፡፡

የጥንቃቄ መንገዶች በግልም ሆነ በተቋማት ደረጃ ሲጓደሉ ምላሽ አሰጣጡ ተቀዛቅዟል ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል፡፡እንደ ሀገር ባለው የመከላከል አቅም የእጅ መታጠብ የፊት ማስክ ማድረግ እና ተራርቆ አገልግሎት ማግኘት የተቀመጡ መመሪያዎች ናቸው፡በዚህም በቀጣይ ሁለት ሳምንት ማስክ ካላደረግጉ አገልግሎት አያገኙም /ኖ ማስክ ኖ ሲርቭስ/ በሚል ሀገራዊ ንቅናቄ እንደሚጀምር የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትር ዋና ዳይሬክተር አስቻለው አያሌው ተናግረዋል፡፡

*******************************************************************************

ቀን 14/ 03/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply