ከሁሉም የራያ አካባቢዎችና የህ/ሰብ ክፍሎች የተወጣጡ አካላት የሚሳተፉበት የራያ ህዝብ የምክክር መድረክ እየጀመረ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም…

ከሁሉም የራያ አካባቢዎችና የህ/ሰብ ክፍሎች የተወጣጡ አካላት የሚሳተፉበት የራያ ህዝብ የምክክር መድረክ እየጀመረ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ በቆቦ ከተማ ተገኝቷል። አሚማ ላለፉት በርካታ ዓመታት በአፋኙ ትሕነግ ህዝብ በጅምላ ሲገደልበት፣ ሲታሰርበት፣ሲፈናቀልበት የቆየው የራያ አማራን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች በሚናገሩበት መድረክ ላይ በመገኘቱ ደስተኛ ነው። የህዝቡ ጥያቄ እንዲመለስ፣መብት፣ ጥቅሙንና ፍላጎቱ ይከበር ዘንድ በየጊዜው ያለመታከት ደፋ ቀና ከሚሉ የራያ አማራ ጀግኖችና ያገባኛል ከሚሉ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ጋርም ተገናኝቷል። በኮሚቴ የተዋቀሩት የራያ አካባቢ ተወላጆችና ተቆርቋሪዎች ከራያ ቆቦ ወረዳ እና የቆቦ ከተማ አስተዳደሮችን ጋር በመተባበር በባለቤትነት ዝግጅቱን እየመሩ ነው። ከሁሉም የራያ አካባቢዎችና የህ/ሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ወጣቶች፣ሴቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ምሁራንና ሌሎችም በተገኙበት የሚደረገውን የራያ ህዝብ የምክክር መድረክን ተከታትሎ መረጃ ወደ እናንተ የሚያደርስ ይሆናል። ከራያ ቆቦ፣ከቆቦ ከተማ፣ከራያ አላማጣ፣ኦፍላ፣ጨርጨር፣መሆኒ፣ዋጃ፣ጥሙጋ እና ከሌሎችም የተወጣጡ ተጋባዦችና የውይይቱ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። ትናንት የተለያዩ ጹሁፎቹን ባቀረቡት በዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ እየተመራ የተለያዩ ጥናታዊ ጹሁፎች የሚቀርቡበት ይሆናል። መድረኩን ታሪካዊና ለየት የሚያደርገውም በገርጋሪው፣በአፋኙ እና ተስፋፊው ትሕነግ ከ30 ዓመታት በላይ በዚህ መልኩ በመድረክ እንዳይገናኙ ሲከለክላቸው የቆዬው ያ ክፉ ስርዓትና ጊዜ አክትሞ ተገናኝተው የልብ ልባቸውን የሚያወሩበት፣መልዕክት የሚያስተላልፉበት፣ ፍላጎታቸውን የሚገልፁበት ሁሉን አገናኝ መድረክ መሆኑ ነው። የራያ ቆቦ እና የቆቦ ከተማ የባህል ቡድኖችም ሁለ ገብ የባህል አዳራሽን ማድመቃቸውን ጀምረዋል። አሚማም እየተከታተለ መረጃዎችን ለእናንተ ያደርሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply