ከሁሉም የሰሜን ሸዋ ዞን ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የአማራ ክልል የፖሊስ አባላት ዘመቻ ሚኒልክ በሚል ህግ ለማስከበር ወደ ራያ ግንባር አቀኑ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳ…

ከሁሉም የሰሜን ሸዋ ዞን ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የአማራ ክልል የፖሊስ አባላት ዘመቻ ሚኒልክ በሚል ህግ ለማስከበር ወደ ራያ ግንባር አቀኑ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሁሉም የሰሜን ሸዋ ዞን ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የአማራ ክልል ፖሊስ አባላት ዘመቻ ሚኒልክ በሚል ህግ ለማስከበር ወደ ራያ ግንባር በዛሬው እለት ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም ያቀኑ መሆናቸው ተገልጧል። የሸዋሮቢት ከተማ ፖሊስ አባለት፣ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር አመራሮች ፣ባለሙያ ፣ባለሀብቶች እንዲሁም ወጣቶችም ዛሬ ጠዋት ላይ ደማቅ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል ሲል የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር አስታውቋል። ከአማራ የተለያዩ አካባቢዎች በርካታ የሚሆኑ የፀጥታ አካላት እንዲሁም መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ህግ በማስከበር በሚል የተጀመረው እንቅስቃሴ በድል እንዲጠናቀቅ በልዩ ልዩ ድጋፎች የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑ ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply