You are currently viewing “ከልብ በሆነ አንድነትና አብሮነት ተደማምጠን ይህን አማራ ጠል ወንበዴ ስርዓት ለመጨረሻ ጊዜ ልንታገለው ይገባል።”     የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋሮቢት       አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

“ከልብ በሆነ አንድነትና አብሮነት ተደማምጠን ይህን አማራ ጠል ወንበዴ ስርዓት ለመጨረሻ ጊዜ ልንታገለው ይገባል።” የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋሮቢት አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

“ከልብ በሆነ አንድነትና አብሮነት ተደማምጠን ይህን አማራ ጠል ወንበዴ ስርዓት ለመጨረሻ ጊዜ ልንታገለው ይገባል።” የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋሮቢት አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 12/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ከአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋሮቢት ለመላው የከተማዋ እና ለሸዋ ህዝብ የተላለፈ አስቸኳይ የትግል ጥሪ! እንደሚታወቀው የአብይ አህመድ አስተዳደር በአማራ ህዝብ ላይ እጅግ አስከፊ በአለም ላይ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍ እና ወረራ እየፈፀመ ይገኛል። በሸዋሮቢት ከተማ ሰሞኑን በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት ሲፈጥር ሰንብቷል። ብዙ ግዜ ሸዋሮቢትን ከኦሮሙማው ስርዓት ወረራ እና ቃጠሎ የታደጉ ጀግና ልጆቻችንን ፋኖዎች ላይ በከባድ መሣሪያ የታገዘ ወረራ ከፍቶ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። እነሱም በሚገባው ቋንቋ እያናገሩት ይገኛሉ። ስለሆነም በዚህ ወሳኝ ሰዓት መተባበርና አንድነት ከማን ምን ይጠበቃል የሚለውን መልዕክት እንደሚከተለው እናስተላልፋለን። 1) በከተማችንን የምትገኙ ማህበረሰብ ሆይ ሸዋሮቢት ካለ ፋኖ አንድቀን እንደማታድር አውቃችሁ ደግሞም ከሰንበቴ ሸኔ ብዙ ግዜ ከመቃጠል የታደጋት ባለውለታዋ መሆኑን ታውቃላችሁ። ስለዚህ ጾታ ሳትለዩ በአንድነት ከፋኖ ጎን በመቆም ለነፃነታችንን አብራችሁ እንድትታገሉና የተለምዶውን ድጋፍና ደጀንነት ሳታቆሙ ከባለፈው በበለጠ ለሬሽን፣ለምግብ እና ለተለያዩ ነገሮች ድጋፍ ለማድረግ እንድትዘጋጁ ስንል እናሳስባለን። 2)የሸዋሮቢትየማፉድ፣የይፋት፣በራሳ፣በቀወት፣ጣርማበር፣እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች የምትገኙ ወጣቶች ነፍጣችሁን እየያዛችሁ ፋኖን በመቀላቀል ለመጨረሻ ግዜ በአንድነት ተናበህ በመነሳት ማርከህ ለመታጠቅ እድል ስለተፈጠረ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ወደ ግንባር እንድትመጣ ስንል በአክብሮት እና በጥብቅ ጥሪ እናደርጋለን። 3) በከተማዋ የምትገኙ ባንዳዎች ህዝባችሁን በሆዳችሁ የሸጣችሁ የመንግስት አመራሮች፣ተራ ተላላኪ ሌቦች ለመጨረሻ ግዜ ከሎሌነት ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ስንል እናስጠነቅቃለን። 4) በሰሜን ሸዋ በሁሉም ወረዳ የምትገኙ ሚሊሻዎች እና ፖሊስ ከፋኖ ጎን በመሠለፍ በአንድነት እንድንታገሉ ጥሪ እናቀርብላችኋለን። 5) የከተማው ወጣትና ህዝብ አንድ ሆነህ በመነሳት ከዬትኛውም አቅጣጫዎች ተጨማሪ የኦነግ ሀይል እንዳይገባና መንገድ በመዝጋት ድጋፍና ከጎናችን መቆማችሁን ልታሳዩ ይገባል። 6) በከተማዋ ሰብአዊነት ያላችሁ መከላከያ ከጀግኖች ወንድሞቻችሁ ከፋኖ ጎን እንድትቆሙ እና እንድትቀላቀሉ ጥሪ ቀርቦላችኋል። 7) በአስቸኳይ የሸዋ ህዝብ እንደ አማራ የመጣበትን የህልውና አደጋ ለመቋቋም ፋኖን እንዲቀላቀል እንዲሁም በውስጡ ያሉትን ሆዳም ባንዳዎችን እንዲመከሩ መልክታችንን እናስተላልፋለን። 8) በአጠቃላይ የአማራን ህዝብና ፋኖን ሱሪውን አስወልቃለሁ ብሎ የተነሳው የኦሮሙማው ጦር በአንድነት ተነስተህ ታገል። ይህ አሸባሪ የወንበዴ ቡድን ሰሞኑን በወጣቱ ላይ ጅምላ እስርና ጅምላ ድብደባን ቀጥሏል። ስለሆነም ከልብ በሆነ አንድነትና አብሮነት ተደማምጠን ይህን አማራ ጠል ወንበዴ ስርዓት ለመጨረሻ ጊዜ ልንታገለው ይገባል። የእሸቴ ሞገስ እና የአስማረ ዳኜ ልጆች ማርከህ በመታጠቅ ታሪክህን አስከብር ህልውናህን አረጋግጥ….. አማራ በነፍጡ ታሪኩን ያድሳል! ድል ለአማራ ጥምር ጦር!

Source: Link to the Post

Leave a Reply