#ከልክ ያለፈ ውፍረት እና መዘዙ፤የውፍረት በሽታ ከደም ግፊትና ልብ ሕመም ቀጥሎ ሶስተኛው የዓለማችን ገዳይ በሽታ እንደሆነ ይገለጻል፡፡ታዲያ ይሄን አስመልክቶ ዶክተር ነጋሽ አሰፋ በአዳማ ውስ…

#ከልክ ያለፈ ውፍረት እና መዘዙ፤

የውፍረት በሽታ ከደም ግፊትና ልብ ሕመም ቀጥሎ ሶስተኛው የዓለማችን ገዳይ በሽታ እንደሆነ ይገለጻል፡፡

ታዲያ ይሄን አስመልክቶ ዶክተር ነጋሽ አሰፋ በአዳማ ውስጥ በሚገኝ እዮር የውስጥ ደዌና የህፃናት ስፔሻሊቲ ሴንተር የህክምና ባለሙያ ስለ ውፍረት በሽታ ምንነት መንስኤ እንዲሁም ስሚያስከትለው ተጓዳኝ በሽታ ዘርዘር ያሉ ነጥቦችን አንስተዋል፡፡

#ከልክ ያለፈ ውፍረት ወይንም ከመጠን በላይ ክብደት ምንድነው ?

ከመጠን በላይ ክብደት በሰውነታችን ውስጥ ከተገቢው በላይ የሆነ የስብ ክምችት ሲኖር የሚፈጠር ነው ።

#መቼ ነው ሰውነታችን ከተገቢው በላይ ውፍረት አለው የምንለው ?

የሰውነታችን ክብደት ከቁመታችን ጋር በማካፈል የሚገኝ ሲሆን ብዙ የህክምና ተቋማት ውፍረትን ለመለካት ልዩ ልዩ መንገዶችን ይጠቀማሉ ። እሱም BMI ወይንም ቦዲ ማስ ኢንዴክስን በመባል ይታወቃል ።

ትክክለኛ የሰውነት ክብደት መጠን የምንለው የሰውነታችን BMI ከ18 እስከ 25 ባለው መጠን ሲሆን ነው ፣ ከ18 በታች ከሆነ ከመጠን ያነሰ ክብደትን ያመለክታል።

ይህ ቁጥር ከ25 እስከ 30 ባለው መሀል ከሆነ Overweight/ የመጀመሪያ ደረጃ ውፍረት እንለዋለን።
ይህ ቁጥር ከ30 በላይ ከሆነ ደግሞ Obese/ እጅግ ከልክ ያለፈ ውፍረት የምንለው ደረጃ ይደርሳል።

ሌለኛዉ የውፍረት መለኪያ መንገድ የወገብ ስፋት (waist circumference) የምንለው ነው።

ይህም የሆድን ዙሪያ በሜትር በመለካት የሚገኝ ቁጥር ሲሆን በዚህ ልኬት መሰረት ወንዶች የሆድ ዙሪያ ስፋታቸው ከ40 ኢንች በላይ ከሆነ እና ለሴቶች ደግሞ ከ35 ኢንች በላይ ከሆነ ከልክ በላይ ውፍረት አለ ማለት እንችላለን።
በዚህ ዘዴ የሚለካ ውፍረት በተለይ ለጤና የበለጠ ጠንቅ የሆነውን በሆድ ዙሪያ አካባቢ የሚከማቸው ስብ ለመለካት ያገለግላል። በተለምዶ ቦርጭ የምንለው ማላት ነው።

ሁለቱንም መለኪያዎች ማለትም BMI እና የሆድ ዙሪያ ስፋት (Waist Circumference) አብሮ መጠቀም የሰውነት ውፍረትን በትክክል ለማወቅ ይረዳናል ይላሉ ባለሙያዉ፡፡

#ከመጠን በላይ ክብደት መንስኤዎች ምንድን ናቸው?

ለልዩልዩ ነገር የምንጠቀመው አንዳንድ መድሃኒቶች፤የአመጋገብ እና የአኗኗር ዘይቤዎች ፤የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያለማድረግ ስብ የበዛበት እንደጮማ ያሉ ምግቦችን አብዝቶ መጠቀም፣ አልኮል መጥኖ ያለመጠቀም ከመጠን በላይ ለሆነ የስብ ክምቺት ወይንም ዉፍርት መያዝ ምክንያት ናቸዉ ተብሎአል።

#ከመጠን በላይ ቦርጭ ምን ያስከትላል?

#ዶከተር ነገሽ አሰፋ:-
1.የዜጎችን ከቦታ ቦታ እንደልብ ተዘዋውሮ የመስራት አቅም ይቀንሳል ፡፡

2. በሰውነታችን ውስጥ ያለው የስብ መጠን ከፍተኛ ሲሆን ፣ ኢንሱሊን ሚባለው ንጥረነገር በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የግልኮስ መጠን እንዳይጠቀም ያደርገዋል። የግልኮስ መጠን በውስጣችን በዛ ማለት ለስኩር በሽታ እንያዛለን ።በስኳር በሽታ ተያዝን ማለት ደግሞ ለልብ ህመም፣ለስትሮክ፣ለጊፊት መጠን መጨመር ፣ ለኩላሊት ህመም ፣ እንዲሁም የደምስሮች ስብ መጠን በመጨመር ለልዩልዩ ህመሞች ይዳርገናል ።

3.ሌለኛው ለካንሰር በሽታ ያጋልጣል ሴቶችን ለጡት ካንሰር የሚያጋልጥ ሲሆን ወንዶችን ደግሞ የአንጀት ካንሰር እንዲይዛቸውና ለሌላም አይነት የካንሰር አይነቶች መንስኤ ይሆናል።

በተጨማሪም መተንፈሻ ትቦዎች እንደፈለጉ መተንፈስ መቸገር እና ሳንባችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ።

ህክምናዉ በቂ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ፤አልኮልን መጥኖ መጠቀም፤ስብ ያላቸዉን ምግቦች መቀነስ ናቸዉ ተብሎአል ፡፡

#በልዑል ወልዴ

መጋት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply