ከሕወሓት ጋር በማበር በሀገር ላይ ሁከትና ብጥብጥ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል በሚል የተጠረጠሩት ኮሎኔሎች ፍርድ ቤት ቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም…

ከሕወሓት ጋር በማበር በሀገር ላይ ሁከትና ብጥብጥ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል በሚል የተጠረጠሩት ኮሎኔሎች ፍርድ ቤት ቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም…

ከሕወሓት ጋር በማበር በሀገር ላይ ሁከትና ብጥብጥ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል በሚል የተጠረጠሩት ኮሎኔሎች ፍርድ ቤት ቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከካሃዲው ሕወሓት ጋር በማበር በሀገር ላይ ሁከትና ብጥብጥ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል በሚል የተጠረጠሩት ኮሎኔሎች ዛሬ ፌዴራሉ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ኮሎኔሎቹ ተጨማሪ ወንጀል ስለመፈጸማቸው በማስረጃ ማረጋገጡን ለፍርድ ቤት ገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ ኮሎኔል ምሩጽ በርሄ፣ ኮሎኔል ገብረመድህን ገብረመስቀል፣ ኮሎኔል ተስፋዬ ሀጎስ እና ኮሎኔል መብርሀቱ ተድላ ናቸው። ከተጠርጣሪዎቹ ኮሎኔል ገብረመድህን ገብረመስቀል በሶማሊያ ሰላም ማስከበር ላይ የነበሩ ሲሆን በሞቃዲሾ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሠራዊት አስኮብለለው የትግራይ ሀይል እንዲሆን ሲቀሰቅሱ ተደርሶባቸው በአስቸኳይ አዲስ አበባ እንዲመጡ ተደርጎ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል። የኮሚሽኑ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ ቡድን ለፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የገለጸው። ከመከላከያ ሠራዊት በጡረታ የተሰናበቱ ሦስቱ ተጠርጣሪዎች በተለያዩ ድርጅቶች የተቀጠሩ የጥበቃ ሰራተኞች በፌደራል ተቋማት ላይ ጥቃት እንዲፈጽሙ ተልዕኮ ሰጥተዋል። እንዲሁም ሀሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል እና ከመከላከያ የተሰናበቱትን እየመለመሉ ወደ ትግራይ በመላክ ለጦርነት እንዲዘጋጁ አድርገዋል በሚል ወንጀል ነው የተጠረጠሩት። ከዚህ ባለፈም ከሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች እና ከኦነግ ሸኔ ቡድኖች ተልዕኮ ስለመቀበላቸው የሚያረጋግጥ የሰው ምስክር ስለመቀበሉ የምርመራ ቡድኑ ለችሎቱ አስረድቷል። ፖሊስ በተሰጠው የግዜ ቀጠሮ ያከናወናቸውን የምርመራ ስራዎች ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል ከወንጀሉ ስፋት አንጻር ለቀሪ የምርመራ ስራ 14 ቀን ጠይቋል። ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን አልፈጸምንም በማለት በነጻ ወይም በዋስ እንለቀቅ በማለት አቤቱታ አቅርበዋል። የግራ ቀኙን ክርክር የተከታተለው ችሎቱ ፖሊስ ከጠየቀው ተጨማሪ ጊዜ 10 ቀን ፈቅዷል።ተጠርጣሪዎች የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታቸው ይከበርም ብሏል ችሎቱ በሰጠው ትዕዛዝ። ዋልታ ሚዲያ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply