“ከሕወሓት ጋር ድርድር መታሰብ የለበትም!”    አባ ገብረ እየሱስ ኪዳነ ማርያም  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…    ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ ከዋልድባው…

“ከሕወሓት ጋር ድርድር መታሰብ የለበትም!” አባ ገብረ እየሱስ ኪዳነ ማርያም አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከዋልድባው…

“ከሕወሓት ጋር ድርድር መታሰብ የለበትም!” አባ ገብረ እየሱስ ኪዳነ ማርያም አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከዋልድባው አባት ከአባ ገ/እየሱስ ኪዳነ ማርያም ጋር በወቅታዊ ጉዳይ የተደረገ ቆይታ! ስለቤተ ክርስቲያን በተለይ ደግሞ ሕወሓት በዋልድባ ገዳምና በመነኮሳት ላይ ሲፈፅመው የነበረውን የለየለት ግፍ በማውገዛቸው፣አምርረው በመታገላቸው፣ ከእምነታችን እጃችሁን አንሱ በማለታቸው ለዓመታት ከእነ አባ ገ/ስላሴና ከሌሎች ጀግኖች ጋር በእስር የተሰቃዩ አባት ናቸው። በክህደትና በዘር ማጥፋት ወንጀል የተሰማራውን ሕወሓትን እየደመሰሰ በግዳጅ ላይ ላለው የአማራ ፋኖን፣የአማራ ልዩ ሀይልን፣የአማራ ሚሊሻንና የመከላከያ ሰራዊትን አመስግነው በርቱ ብለዋል! ለሀገሩ፣ለክብሩ፣ለነፃነቱ፣ለማንነቱና ለእርስቱ ሲል ለከሀዲዎች ለማይመቸው ነፍጠኛ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል! ነፍጠኝነት ይለምልም ብለዋል! ሕወሓትን የምንታገለው ስለሀገር፣ ስለህልውና ሲባል ነው፤ ያገባኛል፤ እናገራለሁ፤ እታገላለሁም ብለዋል። በዋልድባ ገዳም፣ በራያ፣ወልቃይት ጠገዴ እንዲሁም በጠለምት ጉዳይ ሀሳባቸውን አጋርተውናል! ሕወሓት በዋልድባ ገዳምና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የፈፀመው በደል ተነገሮ አያልቅም! ከሕወሓት ጋር ድርድር አይታሰብም፤ ደም እየፈሰሰበት፣ዘር እየጠፋበት ያለውን የወልቃይት፣ጠገዴ፣ራያ የአማራ እርስት ለህወሀት መዋቅር አሳልፎ መስጠት ዳግም ባርነትን መቀበል ስለሆነ አይታሰብም! በመተከል፣በኦሮሚያና በሌሎችም በደመ ነፍሶች አማራ ላይ ስለሚፈፀመው እልቂት መንግስት ተባባሪዎችን ያፅዳ፣መዋቅሩን ይፈትሽ? ተጠያቂ ነው፤ ገብቶ እርምጃም ይውሰድ ብለዋል! በአማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ/AMC ይጠብቁ!

Source: Link to the Post

Leave a Reply