ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ያለፈው ዓመት እንዴት እንዳለፈ ባዘጋጀው ህዝባዊ መድረክ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 28 ቀ…

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ያለፈው ዓመት እንዴት እንዳለፈ ባዘጋጀው ህዝባዊ መድረክ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት_ መኢአድ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በሚያካሂደው ህዝባዊ ምክክር ያለፈው ዓመት እንዴት እንዳለፈ ሊገመግም መሆኑን አስታውቋል። የተከበራችሁ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሙሉ ነሐሴ 28 ቀን ልክ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ያለፈውን አመት የዳሰሰ ጥናታዊ ጽሁፍ ለማቅረብ የተዘጋጁ አቅራቢዎችና የድርጅቱ አመራሮች፣አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም የክብር እንግዶች ፒያሳቴዎድሮስ አደባባይ በሚገኘው በመኢአድ ዋና ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ እየገቡ ነው። በውይይት መድረኩ በዕለቱ ጥናታዊ ጽሁፍ የሚያቀርቡትም፦ 1. መ/ር ታዬ ቦጋለ እና 2. ዶ/ር ቴዎድሮስ ዘውዱ ሲሆኑ በስፍራው ተገኝተዋል። በፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ ቸርቸር ጎዳና ከሊሴ ገብረማሪያም ት/ቤት አጠገብ ከቴሌው ጎን በሚገኘው የመኢአድ ጽ/ቤት አዳራሽ በሚደረገው ህዝባዊ የምክክር መድረክ የ2013 ቆይታችን ይገመገማል፤ ላልተሻገርናቸው አሁናዊ ፈተናዎች የመፍትሄ አቅጣጫም ይቀመጥለታል ተብሎ ይጠበቃል። “ድል እና ውጤት ያለ ትግል አይታሰብም!” የሚለው መኢአድ ይህ መድረክ ከህዝብ ጋር በመሆን እያደረገ ያለውን ትግል የበለጠ አጠናክሮ ለመቀጠል እንደሚረዳው ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በመኢአድ የስብሰባ አዳራሽ ተገኝቷል፤ ተጨማሪ መረጃዎችን የሚያጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply