ከመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን የኤሌክትሪክ አደጋ ለመከላከል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ፡፡ከመስቀል ደመራ በዓል አከባበ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Pub7wnMlVYhdyjpljQp_msDzgOl4A0EF3CuPzuFd4LAN9FJuQo8ItHbQNSeM3wDTaYDfp9zZAtvpqbr8iNAGtOuxilSJZm-SYxJI-f5p3E3iiHjpSl0vqpB0GSFeIV-LxRkTkDlhP3OzkZ9P1Odj615kpxHDrlEqeA7ru3w-elD5Ie7o3OmpYMFCbtw9-dyVyX_h81UHJ8LTZ1u8ZSGTgF5iHpwWj_VRxWmFiLjiqpdxjV08_VNAE7uQW2nLsg4ivdcXzJ8RiDPUmr2BWCTPyLpAvSFHHd1FIoFNgtk890YPBw8JZ4_JaFn6deJPLPYvdcqVX_LsqlQgKmOKEJK3wg.jpg

ከመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን የኤሌክትሪክ አደጋ ለመከላከል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ፡፡

ከመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ የእምነቱ ተከታዮች በተለያዩ ቦታዎች ችቦ የማብራት ስነ-ስርዓት ያካሂዳሉ፡፡
በዚህ ወቅትም ደመራ ሲለኮስ ከኤሌክትሪክ መስመሮች፣ ምሰሶዎች፣ ትራንስፎርመሮች በጣም በራቀ መልኩ ማከናወን እንዲሁም የእሳት አደጋ እንዳይከሰት ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡

በጥንቃቄ ጉድለት የኤሌክትሪክ ንክኪ ጋር በሚፈጠሩ አደጋዎች በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡
በመሆኑም ለአከባበሩ ድምቀት የሌሌክትሪክ ምሰሶዎችን በመጠቀም የሚደረጉ የማስዋብ ሥራዎች ለኤሌክትሪክ አደጋ ሊያጋልጥ ስለሚስችል ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚገባው ተቋሙ አሳስቧል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ በኤሌክትሪክ ማሰራጫ ምሰሶዎች ላይ በተሽከርካሪዎች አደጋ የማደርስ ተግባር በበዓላት የሚሰተዋል በመሆኑ፣ አሽከርካሪዎች ጥብቅ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተቋሙ ጨምሮ ገልጧል፡፡

ስለሆነም ህብረተሰቡ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ የበኩልን ትብብር እንዲያደርግ የጠየቀው አገልግሎቱ፤ ሆኖም ድንገት ከኤሌክትሪክ ጋር በተገናኘ አደጋ ካጋጠመ ወይም ሌላ መረጃ ሲፈለግ ወዲውኑ በአቅራቢያ በሚገኝ አገልግሎት መስጫ ማዕከል 905 ቀጥታ ስልክ በመደወል ወይም በአካል በመሄድ ማሳወቅ እንደሚገባም ጠቁሟል፡፡
አገልግሎቱ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ ሲልም መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply