‹‹ ከመስከረም እስከ ታህሳስ ባሉት ወራት በኦሮሚያ ክልል 53 ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጬያለሁ ›› አለ ኢሰመጉየኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ‹ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ…

‹‹ ከመስከረም እስከ ታህሳስ ባሉት ወራት በኦሮሚያ ክልል 53 ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጬያለሁ ›› አለ ኢሰመጉ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ‹ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ እና ቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሜ ወረዳ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን › በተመለከተ 154ኛ ልዩ መግለጫውን ትላንት ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም ‹‹ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ህደር 14 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት ሶሌ ዲገሉ በተባለ ቀበሌ ውስጥ የተደራጁ ታጣቂ ቡድኖች ወደ ቀበሌው ዘልቀው በመግባት 17 ሰዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን ›› አጋልጧል፡፡

በታጣቂ ቡድኖቹ ከተገደሉት ሰዎች መካከል የ70 ዓመት አዛውንት፣ የ12 ዓመት ታዳጊ፣ የ8 ወር ህጻንእና የ28 ቀን ጨቅላ ህጻን እንዲሁም ነፍሰጡር ሴቶች የሚገኙ ሲሆን ከሟቾች መካከል አብዛኛዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው ብሏል፡፡

በዚህም ‹‹ ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት በታጣቂ ቡድኖች በተፈጸመ ጥቃት 5 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ኢሰመጉ አሳውቋል፡፡

ጉባዔው ይህንን መግለጫውን የጉዳቱ ሰላባዎችን ስም ዝርዝርና ምስላቸውን ጭምር በማያያዝ ይፋ አድርጓል፡፡

ኢሰመጉ በመግለጫው ማጠቃሊያ ፌደራል መንግስት እና የኦሮሚያ ክልል መንግስት በክልሉ በተጋጋሚ በታጣቂ ቡድኖች ማንነትን መሰረት አድርጎ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ ጠይቋል፡፡

‹‹የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልል መንግስት የህዝቡን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት እያለባቸው ይህንን በቸልተኝነት ሳያደርጉ የቀሩ የመንግስት አካላትን በህግ እንዲጠይቁ ›› ሲል አበክሮ አሳስቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply