You are currently viewing #ከመስጠት ያልጎደለ ማንነት!          አሻራ ሚዲያ ፣መጋቢት 24/2015 ዓ/ም ፤ባህር ዳር ኢትዮጵያ/ #መሠረት የበጎ አድራጎት ድርጅት#  በባህርዳር ከተማ ከጎዳና ላይ አንስቶ  ያሰለ…

#ከመስጠት ያልጎደለ ማንነት! አሻራ ሚዲያ ፣መጋቢት 24/2015 ዓ/ም ፤ባህር ዳር ኢትዮጵያ/ #መሠረት የበጎ አድራጎት ድርጅት# በባህርዳር ከተማ ከጎዳና ላይ አንስቶ ያሰለ…

#ከመስጠት ያልጎደለ ማንነት! አሻራ ሚዲያ ፣መጋቢት 24/2015 ዓ/ም ፤ባህር ዳር ኢትዮጵያ/ #መሠረት የበጎ አድራጎት ድርጅት# በባህርዳር ከተማ ከጎዳና ላይ አንስቶ ያሰለጠናቸውን አንድ መቶ ዘጠኝ እናቶች እና ህፃናትን አስመረቀ።… ድርጅቱ ላለፉት አራት ወራት በስነ ልቦና; ስራ ፈጠራ እና መሰል ጉዳዮች ዙሪያ ነው ስልጠናውን ሲሰጥ የቆየው። በስልጠናው ተሳታፊ የነበሩ እናቶች እና ህፃናትን ሙሉ ወጫቸዉን ሸፍኖ ላለፉት አራት ወራት ስልጠናውን ሲሰጥ የቆየው ድርጀቱ በዛሬው እለት በፋደል ሆቴል የክብር እንግዶች በተገኙበት አስመርቋል። በዛሬው እለት ስልጠናቸውን ጨርሰው ለተመረቁት እናቶች በፍላጎታቸውን መሰረተት ባደረገ መልኩ የተለያዩ የስራ መጀመሪያ ግብአቶች እና ለእያንዳንዳቸው 5000 ብር በጥሬ ገንዘብ ተሰጥቷቸዋል። በምረቃ በኘሮግራሙ ላይ ሀሳባቸውን የሰጡት ሰልጣኞች የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ከችግር ስላነሳቸው አመስግነው በተሰጣቸው መንቀሳሻ ገንዘብ እና በተፈጠረላቸው የስራ እድል ውጤታማ ለመሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል። የመሰረተ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች እና ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ መሰረት አዛገ ድርጅታቸው በሀገሪቱ የተለያዩ አስራ አንድ ከተሞች ተመሳሳይ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረው በአማራ ክልልም በባህር ዳር የጀመርነውን ስራ ወደ ሌሎች ከተሞች የማስፋፋት ስራ እየሰራን ነዉ ብለዋል።በኘሮግራሙ መጨረሻ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ሴቶች እና ህፃናት ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወ/ሮ የሽሀረግ የድርጅቱን በጎ አላማ ለመደገፍ ሁላችንም በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply