ከመቀሌ ውጭ ባሉ የትግራይ አካባቢዎች የባንክ አገልግሎት ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ፡፡

ከመቀሌ ውጭ ባሉ የክልሉ ከተሞች የተቋረጠውን የባንክ አገግሎት ለማስጀመር ወደ ስራ መገባቱ ተገልጿል፡፡አገልግሎቱን ለማስጀመር በቅድሚያ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች መጀመራቸውና አገልግሎት መስጠት በመጀመር ላይ ያሉ ከተሞችም እንዳሉ የመቀለ ከተማ ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለስላሴ ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም የመሠረተ ልማት ያልተሟሉላቸው ቦታዎችን አሟልቶ የባንክ አገልግሎቱን ለማስጀመር ከመብራት ኃይልና ከቴሌ-ኮምኒኬሽን ሠራተኞች ጋር በመሆን ተደራሽ ለማድረግ ስራ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡

ከንቲባው አክለውም የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ ሌሎች ከተሞችም በአጭር ጊዜ ውስጥ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡

********************************************************************

ዘጋቢ፡ክብሮም ወርቁ

ቀን 21/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply