ከመቅደላ የተሰረቁ ቅርሶች አብዛኛዎቹ በግለሰብ እጅ ናቸው ተባለ፡፡በቁጥር የሚልቁት ከመቅደላ የተሰረቁ ቅርሶች በግለሰብ እጅ እንደሚኙ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡…

ከመቅደላ የተሰረቁ ቅርሶች አብዛኛዎቹ በግለሰብ እጅ ናቸው ተባለ፡፡

በቁጥር የሚልቁት ከመቅደላ የተሰረቁ ቅርሶች በግለሰብ እጅ እንደሚኙ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
ከኢትዮጵያ የተሰረቁ ቅርሶችን ለማስመለስ አመርቂ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ ያስታወቀው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በእንግሊዝ ወታደሮች ከመቅደላ የተዘረፉት አብዛኛዎቹ ቅርሶች በግለሰብ እጅ እንደሚገኙ አውቄያለሁ ብሏል፡፡
ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያቶች የተዘረፈችውን ቅርስ ላመስመለስ በርካታ እንቅስቃሴ እያደረገች አብደሆነ ያስታወሰው ባለስልጣሉ በእነዚህ ጊዜያትም የአጼ ቴዎድሮስ የጸጉር ሹርባን ጨምሮ በርካታ ቅርሶቿን ማስመለስ ችያለሁ ብሏል፡፡
የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳሬክተር አበባው አያሌው ከመቅደላ አምባ የተዘረፉት ቅርሶች ለማስመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
ከ500 በላይ የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶች ያሉባቸዉ የብራና ጽሑፎች፤ የንጉሣውያን የወርቅ ዘውዶችና ጌጣ ጌጦች፣ እንዲሁም ወደ አስር የሚሆን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ታቦታት በእንግሊዝ የተለያዩ ሙዚየሞች እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
በግለሰብ ደረጃ የሚገኙት የኢትዮጵያ ቅርሶች በግዢ ወይም በተውሶ ሊገኝ ይችላል የተባለ ሲሆን በሀገራት ብሄራዊ ሚዚየሞች የሚገኙትን ደግሞ በዲፕሎማሲ መንገድ እንዲመለሱ ለማድረግ ጥረቱ ይቀጥላል ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ታህሳስ 07 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply