ከመተከሉ አለመረጋጋት ጀርባ የብሄራዊ ደህነት ስውር እጅ እንዳለበት አሻራ ሰምቷል፡፡ (አሻራ ታህሳስ 28፣ 2013 ዓ.ም) ብሄራዊ ደህነት  አገልግሎት ከለውጡ በፊት በጌታቸው አሰፋ መሪነት…

ከመተከሉ አለመረጋጋት ጀርባ የብሄራዊ ደህነት ስውር እጅ እንዳለበት አሻራ ሰምቷል፡፡ (አሻራ ታህሳስ 28፣ 2013 ዓ.ም) ብሄራዊ ደህነት አገልግሎት ከለውጡ በፊት በጌታቸው አሰፋ መሪነት…

ከመተከሉ አለመረጋጋት ጀርባ የብሄራዊ ደህነት ስውር እጅ እንዳለበት አሻራ ሰምቷል፡፡ (አሻራ ታህሳስ 28፣ 2013 ዓ.ም) ብሄራዊ ደህነት አገልግሎት ከለውጡ በፊት በጌታቸው አሰፋ መሪነት ሙሉ በሙሉ የህወሓት መዋቅር ጉዳይ አስፈፃሚ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በዚህ መስሪያቤት አቶ አንዳርጋቸውን ከየመን ሰንአ አውሮፕላን አፍኖ ለማውጣት ከ100 ሚሊየን ብር ወይም በወቅቱ ምንዛሬ ከ5 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጭ ሆኗል፡፡ ይህ ህወኃትን ለማዳን የተደረገ ፓርቲያዊ መስዕዋትነት ነበር፡፡… በዚህ መስሪያ ቤት በ1984 እስከ 1989 አማራን በማረድ እንዲፈናቀሉ ያደረጉ የህወኃት ተቀጣሪ የኦነግ ታጣቂዎች መረጃ እንዳያወጡ በጅምላ ተገለዋል፡፡ የአማራ መፈናቀልም ሚመራው በዚህ መስሪያቤት ሲሆን የአነ አቶ ሙሉዓለም አበበ፣ የእነ አለማየሁ አቶምሳ ፣የእነ ሀይሎም አርአያ የመሳሰሉት የኢህአዴግ ሰዎች ግድያ የተመራውም በዚህ መስሪያቤት እውቅና ነበር፡፡ ሰው መሰወር፣ ከእንስሳት ጋር ማሰር፣ የጋራ ወሲብ መፈፀም፣ ብልትን መስለብ የመሳሰሉት ጭካኔዎች የሚፈፀሙት በዚህ መስሪያቤት መሆኑ ደህንነት ሲባል ስጋት እንዲሰማ ሆኗል፡፡ ከለውጡ በኃላም ቢሆን አዛዥ የለሹ ጌታቸው አሰፋ የቢሮ ቁልፍ እንኳን አልሰጥም ብሎ በአሜሪካ አደራዳሪነት ቁልፉን ሰጥቷል፡፡ አቶ ጌታቸው ቁልፉን ቢሰጥም ከሞሳድ እና ከሲአይኤ በእርዳታ የተገኙ የስለላ ውድ መሳሪያዎችን ግን ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ በገፍ ተወስደዋል፡፡ በወታደራዊ ብቃቱ የሚታወቀው ፣ቀልደኛ እና ራሱን ቀለል አርጎ የሚኖረው ግን ለብዙዎች የማይገለጠው ጌታቸው አሰፋ ብሄራዊ ደህንነትን እስከ ወረዳ ድረስ በራሱ ቅርፅ መስራቱ ለውጡ እንዲጨናገፍ መሰረት ጥሏል፡፡ ከግድያ እና ከመፈናቀል ጀርባ በጌታቸው አሰፋ የተደራጁ የደህንነት ሰራተኞች አሉበት፡፡ በእርግጥ በምክትል ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የኖሩት በነያሬድ ዘሪሁን መዝገብ ተከሰው ወደ ማረሚያ ወርደዋል፡፡ ከዚያ በታች ያሉ ሰራተኞች ግን ባሉበት ሲሆን፣ መስሪያቤቱ ኢ-መደበኛነት ስለሚበዛበት ለክትትል አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ ብሄራዊ ደህንነቱ ደሞዝ የሚከፍላቸው ነገር ግን ቢሮ የማይገቡ ከ300 በላይ ሰራተኞች ሲኖሩ ፣ምን እንደሚሰሩ እና ለማን መረጃ እንደሚሰጡ በግልፅ አይታወቅም፡፡ ይህን ጀኔራል አደም መሃመድም ሆኑ አቶ ደመላሽ ሀይለሚካኤል ሳያስተካከሉት ያለፉ ሲሆን፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ግን የማስተካከያ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ የቢሻንጉሉ ጉምዙ የደህንነት ሀላፊ አቶ “ጌታቸው ታክሲ” ( የአባቱ ስም ትክክለኛው ብርሃነ ነው) በመተከል ግጭት እጁ እንዳለበት ተደርሶበት ከስራ ታግዷል፡፡ በወለጋ የኦነግ ሸኔ አደራጆችም የብሄራዊ ደህነቱ የሚወጡ ሰዎች እንደሆኑ አሻራ ሰምቷል፡፡ የብሄራዊ ደህንነት የጌታቸው አሰፋ ምልምሎች ዛሬም በብልፅግና ውስጥ ላሉ ውስን ቡድኖች እና ግለሰቦች ሎሌ በመሆን በሀገሪቱ ላይ ግጭት እንደሚቸረችሩ ከሀሜት የዘለለ እውነት ሆኗል፡፡ የደህነት ተቋሙ መሰረታዊ ለውጥ ካላደረገ በስተቀር የሀገሪቱ ችግር ችግር ሆኖ መዝለቁ አይቀሬ ይሆናል፡፡ የብሄራዊ ደህንነቱ ሰዎች በሀገሪቱ ላይ የብሄር ቅራኔን እንደሚያፉፍሙ ሁሉ፣ አማራም በአካባቢ እንዲከፋፈል ይሰራሉ፡፡ የብሄራዊ ደህንነት ተቋሙ ለሴራ ፖለቲካ ምርኮኛ ሆኖ ለሀገራዊ አንድነት እና ለኢትዮጵያ ህዝብ አለመቆሙ ኢትዮጵያ ምን ያህል ተቋም አልባ እንደሆነች ያሳያል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply