ከመተከል ተፈናቅለው በጓንጓ እና ቻግኒ ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃዮችን ቁጥር ከ40,000 በላይ እንደሚሆን ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓም አዲስ አበባ…

ከመተከል ተፈናቅለው በጓንጓ እና ቻግኒ ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃዮችን ቁጥር ከ40,000 በላይ እንደሚሆን ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓም አዲስ አበባ ሸዋ የጓንጓ ወረዳ ኮሚኒኬሽን እንደዘገበው የመተከል ተፈናቃዮች በጓንጓ ወረዳ በመንተውሃ አካባቢና በቻግኒ ይገኛሉ። ከታህሳስ 11ቀን 2013 ጀምሮ ከመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ሳስማንደን ቀበሌ የተፈናቀሉ ዜጎች በጓንጓ ወረዳ መንተውሃ ከተማ በሜዳ ላይ እንዲህ ሰፍረዋል ይገኛሉ ብሏል። ይህም ከመተከል ተፈናቅለው በጓንጓ እና ቻግኒ ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃዮችን ቁጥር ከ40,000 በላይ እንደሚሆን የአዊ ብ/አስተዳደር የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ሃላፊ አቶ ደርበው በላይ ገልፀዋል ሲል የጓንጓ ወረዳ ዘግቧል። የኦነግ ሸኔ እና የጉምዝ ታጣቂዎች ከተስፋፊና ፅንፈኛ የመንግስት አካላት ጋር በመሆን በአማራ/አገው ላይ ያነጣጠረ ተደጋጋሚና አሰቃቂ የጅምላ ፍጅት እየፈፀሙ መሆናቸውና ለችግሩም መፍትሄ አለመበጀቱ ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply