ከመተከል ዞን ለተፈናቀሉ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ አልተቻለም

https://gdb.voanews.com/506DED22-8854-4373-BC53-1AE36F211707_cx0_cy21_cw0_w800_h450.jpg

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የፀጥታ ችግር በመፍራት የሰብዓዊ ድጋፍ ለማጓጓዝ ለሰጉ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።

በክልሉ አንድ መቶ ሺህ የሚጠጋ ተፈናቃይ መኖሩንና ከመንግሥትም ሆነ ከረጂ ድርጅቶች ድጋፍ እየተገኘ ቢሆንም በአካባቢው በአለው የፀጥታ ስጋት ምክንያት ከፌደራልም ሆነ በክልሉ ውስጥ ወደ ተለያዪ አካባቢዋች እህል ለማድረስ አለመቻሉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ገልጿል።

ተፈናቃዪቹ ባሉበት ከተማ የሚገኙ ነዋሪዋች ቤታቸውን ለቀው ከ15 እስከ 20 ድረስ በቤታቸው እያስተናገዱ መሆኑን ተፈናቃዪቹ አመስግነዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply