ከመተከል  ዳንጉር ወረዳ ጉብላክ ከተባለች ትንሽ ከተማ ባሏ ሲገደልባት በሽሽት ደብረ ማርቆስ ከተማ ለወራት ችግር ላይ የነበረችው የሶስት ልጆች እናት ድጋፍ ተደረገላት…

ከመተከል ዳንጉር ወረዳ ጉብላክ ከተባለች ትንሽ ከተማ ባሏ ሲገደልባት በሽሽት ደብረ ማርቆስ ከተማ ለወራት ችግር ላይ የነበረችው የሶስት ልጆች እናት ድጋፍ ተደረገላት…

ከመተከል ዳንጉር ወረዳ ጉብላክ ከተባለች ትንሽ ከተማ ባሏ ሲገደልባት በሽሽት ደብረ ማርቆስ ከተማ ለወራት ችግር ላይ የነበረችው የሶስት ልጆች እናት ድጋፍ ተደረገላት አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 05/2013 ዓ.ም ባህር ዳር ከመተከል ዳንጉር ወረዳ ጉብላክ ከተባለች ትንሽ ከተማ ጷግሜ 04 /2012 ዓ.ም ታጣቂዎች በጨለማ የግድያ ጥቃት ሲፈጽሙ 3 ህፃናት ልጆቿን ( እድሜያቸው 5፣ 3 እና 1 የሆኑ) በመያዝ ቡሬ ከተማ ላይ ለልመና ህይወት ተዳርጋ ነበር፡፡ ይህች መፈናቀል ችግር የደረሰባት የሶስት ልጆች እናት በደብረ ማርቆስ ከተማ እና በቡሬ ከተማ መልካም አሳቢ ወጣቶች እነ ቃል ኪዳን አለነ ፤ብሬ ግዮናዊው እና የአማራ ወጣቶች ማህበር በደብረ ማርቆስ አስተባባሪነት እንዲሁም በዋናነት በፌስቡክ ስሙ ‹‹ምስጋናው ዘ ግዮን ›› ምስጋናው በለጠ አስተባባሪነት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር በሚኖሩ ቅን አሳቢዎች ባደረጉት ድጋፍ በቋሚነት እንድትቋቋም ሆኗል፡፡ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ቀና ምላሽ በመስጠት ላደረገው ትብብር የሚመሰገን ሆኖ አግኝተነዋልብለዋ ድጋፉን ያሰባሰቡት እነ ‹‹ምስጋናው ዘ ጊዮን››ምስጋናው በለጠ። ከዚህ በተጨማሪ ያረፈችበት አንድ ክፍል የቀበሌ ቤት ላልተወሰነ ጊዜ እንድትኖርበት የፈቀዱ ሲሆን በቋሚነት ለማቋቋም የስራ ቦታ በእነሱ እገዛ ተመቻችቷል፤ ከበጎ ፈቃደኞች በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ መነሻነት በአጭር ቀናት የገቢ ማስገኛ ስራ ትጀምራለች። ወይዘሮ እመቤትን ለማቋቋም በተደረገው ጥረት ውድ ጊዜያቸውን ፤ገንዘባቸውን፤ጉልበታቸውን ሰውተው በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚገኙ ወገኖች ያለችበትን ሁኔታ በማስረዳት ድጋፍ ያሰባሰቡት እነ ምስጋናው በለጠ፤ብሬ ግዮናዊው ፤ጥላሁን አበጀ፤የአማራ ወጣቶች ማህበር በቡሬ፤የአማራ ወጣቶች ማህበር በደብረ ማርቆስ ላደረጋችሁልኝ ሁሉ ምስጋናዬ ከፍ ያለነው ብላለች ወይዘሮ እመቤት፡፡ ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply