ከመገናኛ አዲሱ ገበያ በሚኒባስ ታክሲ ሲስጥ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ ተደረገ።

ቀደም ብሎ በትራንስፖርት አሰጣጡ ላይ ሲታይ የነበረው ችግር ለመቀረፍ የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ምላሽ መስጠቱን ገልጿል።

በየካ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ከመገናኛ – አዲሱ ገበያ የጉዞ መስመር በሚኒባስ ታክሲ ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎቱ እንዲሰጥ መደረጉን ነው የተገለጸው።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ዳዊት ዘለቀ ህብረተሰቡ ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር በተገናኘ በዋናነትም ከማቆራረጥና ከታሪፍ በላይ ማስከፈል ጋር ተያይዞ በመስመሩ የሚስተዋለውን ችግር ተለይቶ መፍትሔ ተሰቶታል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም አገልግሎቱ በብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ በሆኑት የአደይ አበባ አውቶብስ፣ ቅጥቅጥ አውቶብሶች እንዲሁም የከተማ አውቶብሶችን ጨምሮ በድምሩ 32 የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችን መድቦ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply