You are currently viewing ከማንዱራ ወደ ግልገል በለስ ተወስደው በዞኑ ኮማንድ ፖስት የታሰሩ የአማራ የጸጥታ አካላት ቁጥጥር 35 ደረሰ፤ 22ቱ የአማራ ልዩ ኃይል ሲሆኑ 13ቱ ደግሞ የአማራ ሚሊሾች ናቸው። አማራ ሚዲያ…

ከማንዱራ ወደ ግልገል በለስ ተወስደው በዞኑ ኮማንድ ፖስት የታሰሩ የአማራ የጸጥታ አካላት ቁጥጥር 35 ደረሰ፤ 22ቱ የአማራ ልዩ ኃይል ሲሆኑ 13ቱ ደግሞ የአማራ ሚሊሾች ናቸው። አማራ ሚዲያ…

ከማንዱራ ወደ ግልገል በለስ ተወስደው በዞኑ ኮማንድ ፖስት የታሰሩ የአማራ የጸጥታ አካላት ቁጥጥር 35 ደረሰ፤ 22ቱ የአማራ ልዩ ኃይል ሲሆኑ 13ቱ ደግሞ የአማራ ሚሊሾች ናቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል ህዳር 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ህዳር 1 ቀን 2014 ከሰዓት በኋላ 35 የሚሆኑ የአማራ የጸጥታ አካላት በዞኑ ኮማንድ ፖስት ትዕዛዝ መታሰራቸው ታውቋል። ከመካከላቸውም 22ቱ የአማራ ልዩ ኃይል ሲሆኑ 13ቱ ደግሞ በማንዱራ የሚኖሩ የአማራ የሚሊሻ አባላት መሆናቸውን አሚማ ከሰበሰበው መረጃ ለመረዳት ችሏል። ከቀናት በፊት አንድ የሀይማኖት አባት በግፍ የገደለው በመንግስት መዋቅር ውስጥ በተሰገሰጉ አካላት ድጋፍ ጭምር የተደራጀና የታጠቀ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚነገርለት የጉምዝ ሽፍታ ቡድን ጥቅምት 29 ቀን 2014 ማንዱራ ላይ አንድ አርሶ አደርን መግደሉ ተሰምቷል። በማግስቱ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ደግሞ በማንዱራ ወረዳ ገነተ ማርያም መሀል ከተማ ላይ በጠራራ ጸሀይ በመግባት የተኩስ እሩምታ በመክፈት 3 አማራዎችን ሲገድል ሌላ አንድ አቁስሏል። በወቅቱም በአካባቢው በነበሩ የጸጥታ አካላትም የአጸፋ ምላሽ መሰጠቱ ተገልጧል። ከተኩስ ልውውጡ ጋር በተያያዘ ከተደራጀው እና ዘር እያጠፋ ያለው የጉምዝ ሽፍታ ቡድን አባላትና ከጥፋት ግብረ አበሮቹም የተገደሉ እንዳሉ ተሰምቷል። ከዚህ የአጸፋ እርምጃ ጋር በተያያዘ ነው ስብሰባ ከጠራ በኋላ 35 የአማራ የጸጥታ አካላትን ትጥቅ በማስፈታት ከማንዱራ ወደ ግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ ማሰሩ የተገለጸው። እስሩ የለየለት ማንነት ተኮር እና የጸጥታ መዋቅሩን እንቅስቃሴ ለማዳከም ያለመና ከጁንታው አካሄድ ለይተን የማናዬው እንደሆነ መታወቅ አለበት የሚሉት የመረጃ ምንጮች በአስቸኳይ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይሰጥበታል ብለን እናስባለን ሲሉም አክለዋል። አሚማ ከመተከል ዞን ከማንድ ፖስት ቀደም ሲል ሲያነጋግራቸው ጉዳዩን የሚያጣራ ኮሚቴ አዋቅረን ወደ ማንዱራ ልከናል ሲመለስ ሪፖርቱን የምንገልጽ ይሆናል ሲሉ ለተናገሩት ለሻምበል ተሾመ አመሻሹን የደወለ ቢሆንም በህዝብ ግንኙነት በኩል እንጅ እኔ መረጃ ለመስጠት አልችልም ሲሉ ሳይፈቅዱ ቀርተዋል። እርሳቸው መረጃ ለመስጠት ካልቻሉ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ያሉትን የኮሎኔል ጌትነትን የስልክ አድራሻ እንዲተባበሩን በሚዲያው ተጠይቀው ፍቃደኛ አልሆኑም። ብዙዎች ይህ ሁሉ ኃይል ተሰብስቦ በአንዴ ሲታሰር በአማራውና በሌሎችም ላይ ሌላ ጥቃት እንዳይፈጸም የሚል ከፍተኛ ስጋት ብቻ ሳይሆን በአካሄዱም ቅሬታ አድሮባቸዋል። የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ከገለልተኝነት ጋር በተያያዘ ብዙ ቅሬታዎች ይነሱበታል። በተለይም በየጊዜው በጅምላ ለሚጨፈጨፉት ወገኖች አዝኖ በተደራጀውና በታጠቀው የጉምዝ የሽፍታ ቡድን ላይ ፈጣን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ብዙዎች ውጤት አላመጣም በሚሉት ተሃድሶ ስም ለገዳዮች በሬ እያረደ ይቀልባል በሚል ይወቀሳል። እንዲሁም በመዋቅሩ ያሉ አባላት ጭምር “ግራ ገባን ወይ ለህዝቡ አልደረስን ወይ ራሳችን አላዳን” በማለት በማማረር ለአሚማ ቅሬታ ማቅረባቸውም አይዘነጋም። መተከል ዞን ባሉ ወረዳዎች በተለያዩ ጊዜያት በቀን በመቶዎች ጭምር የተገደሉበትና በእስካባተር ሳይቀር ተቆፍሮ በጅምላ የተቀበሩበት፣ በአማራው ላይ የዘር ማጥፋት በተደጋጋሚ የተፈጸመበት መሆኑ የአደባባይ እውነታ ነው። ከኮማንድ ፖስት ምላሽ የሚሰጠን አካል እንዳገኘን ተጨማሪ መረጃ ይዘን የምንመለስ ይሆናል። ( የተጨመሩ አዳዲስ መረጃዎች)

Source: Link to the Post

Leave a Reply